Is this email not displaying correctly? View it in your browser. Date: January 9, 2017

መልእክት ከትምህርት ቦርድ፦ ሰላማዊና እንግዳ ተቀባይ ት/ቤቶች ለሁሉም ተማሪዎች

BOE logo

የተከበራችሁ የMCPS ቤተሰቦች፡-

እንኳን ለኣዲሱ ኣመት ኣደረሳችሁ! 2017ን ስንጀምር፣ ይህን እድል ወስደን ለያንዳንዱ የMCPS ተማሪ ለትምህርት ሰላማዊና ጋባዥ ኣካባቢ ለመስጠት የገባነውን ግዴታ ደግመን ለማረጋገጥ እንፈልጋለን።

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ፣ Montgomery County በህብረተሰቡ ላይ በጥላቻ-የተመሰረቱ ክውነቶች መብዛት ታይቷል፣ የተወሰኑም በት/ቤቶቻችን ተፅእኖ ያስከቱሉትን ያካትታል። እነዚህ ክውነቶች በኛ ካውንቲ ብቻ በተለይ የሚደርሱ ኣይደሉም እናም በሃገሪቱ ከዳር እስከዳር የምናየው ነፀብራቆች ናቸው፣ እነዚህን ክውነቶች ለመቆጣጠር MCPS ከMontgomery County የፖሊስ መምሪያ ጋር ኣብሮ እየሰራ እና ሁሉን ኣስፈላጊ እርምጃዎች በመውሰድ ላይ እንደሚገኝ እባካችሁ ተገንዘቡ። እነዚህ በጥቂት ሰዎች የሚደረጉ በጥላቻ-የተመሰረቱ ክውነቶች፣ የተማሪን ትምህርት ለማረጋገጥ መሰረታዊ ለሆኑት፣ ለእኛ የመከባበርና የፍትህ ዋንኛ እሴቶች ስህተተኛና ግብረገብ የለሽነት ናቸው። Superintendent Jack R. Smith እንዳለው፣ MCPS ይህን ስነ ምግባር ፊት ኣይሰጠውም።

የዲሲፕሊን እርምጃ ት/ቤቶች ለሁሉም ቀጣይ እንግዳ ተቀባይና ሰላማዊ መሆናቸውን ለማረጋገጥ ከሚጠቀምባቸው ታክቲኮች አንዱን ብቻ ነው የሚወክለው። በመማርያ ክፍሎቻችንና በት/ቤቶቻችን ባህላዊ መግባባትን ለማራመድና ኣይነተ-ብዙህነትን ለማክበር MCPS ዝግጁ እርምጃዎችን ይወስዳል። ከእንግሊዘኛ ወደ ማህበራዊ ጥናቶች ወደ ኣካላዊ ትምህርት እና የጤና ትምህርት፣ የMCPS ተማሪዎች ለተለያዩ ኣስተያየቶች/ሀሳቦች ይጋለጣሉ፤ የተለያዩ በስተኋላ ያላቸው ህዝቦችን ባህላዊ እምነቶችና ልምዶችን ያገናዝባሉ፤ ሌሎችን ስለመቀበልና ስለማክበር ይማራሉ፤ እናም ስለ ባህላዊ ግንዝቤና እድናቆት አካል በመሆን ስለ ባህል ይማራሉ። 

ጥናት ክበቦች ፕሮግራሞቻችን ኣማካይነት፣ ለተማሪዎቻችን፣ ሰራተኞችና ወላጆች ስለ ዘር፣ ሃይማኖት እና ባህል የማይመቹ ነገር ግን ወሳኝ ውይይቶች እንዲሳተፉ መገልገያዎች እናቀርብላቸዋለን። እነዚህ ውይይቶች ከራሳችን ይልቅ ስለ ሌሎች የተለያዩ ኣስተያየቶች ለመስማትና ለመማር ያስችሉናል። ከMontgomery County የእምነት ማህበረሰቦች ጋር በመሻረክ፣ MCPS የሃይማኖታዊ ብዙህነት የማክበር መመርያዎች በተጨማሪ ኣዳብሯል። እነዚህ መመርያዎች ሁሉም ተማሪዎቻችን፣ ከኣድልዎ፣ ማሸማቀቅ ወይም ወከባ ነፃ በመሆን የሃይማኖት እምነቶቻቸውንና ልምዶቻቸውን ለመግለፅ፣ መብት ኣላቸው።

[ሃይማኖታዊ ብዙህነት የማክበር መመርያዎችን ኣንብቡ]

የባህላዊ ብቃት ስልጠና ለተማሪዎች መልካም የኣቅባበል ኣካባቢ ለማረጋገጥ የምናደርገው ጥረታችን ቁልፍ ኣካል ነው። ዘርና ባህል በማስተማርና በመማር ላይ ተፅእኖ እንዳላቸው እናውቃለን። በMCPS Equity Initiatives Unit/የፍትህ ተነሳሽነቶች ክፍል ኣማካይነት፣ መምህራኖቻችን ባህላዊ ችሎታቸውን በመገንባት በዘርና በወገን የተመሰረቱ ተበላላጭነቶችን የሚያስወግዱ የመማርያ ክፍል ልምዶችን፣ መዋቅሮችንና ሂደቶችን በስኬት ማወሃሃድ እንዲችሉ እና በሁሉም ኣይነተ-ብዙ የበስተኋላዎች ከፍተኛ ግኝትን የሚያሳድጉ ስኬታማ ግንኝነቶች እንዲገነቡ እናግዛቸዋለን። የMCPS የሰብኣዊ ሃብቶችና እድገት ፅ/ቤት ተማሪዎች በት/ቤቶቻቸው የተለያዩ ኣርኣያ ሞዴሎች እንዲኖሯቸው በታሪክ ውክልና ከተሳናቸው ማህበረሰቦች ኣስቀድሞ በመዘጋጀት ተጨማሪ መምህራኖች በመቅጠር ላይ ይገኛል።

[ስለ እኛ ፍትሃዊ ኣነሳሺነቶች ቪድዮ ተመልከቱ]

ያልተሰነዱ ተማሪዎች ደህንነትን በሚመለከት ያሏችሁን ቅሬታዎችም ሰምተናል። ይህን ግልፅ ላድርገው፣ የስደት ይዘት የፈለገውን ይሁን፣ MCPS ለሁሉም ተማሪዎች ምንጊዜም ጋባዥ ኣካባቢ ይሆናል። ባጠቃላይ አነጋገርም ቢሆን፣ የስደትና የጉምሩክ ኣስከባሪ ት/ቤቶችን መታሰር፣ ቃለመጠይቆች፣ ፍተሻዎችና ቁጥጥሮች የማይካሄዱባቸው ኣሳሳቢ ኣካባቢዎች ብሎ ቢመልከታቸውም፣ የMCPS ኣስተዳዳሪዎች ሁኔታውን በቅርብ ይከታተሉታል። ሰራተኞቻችን በስደት ይዘታቸው ምክንያት ተማሪዎችን የሚያገልሉ ወይም ወደ ማግለል የሚያመሩ ትግባሬዎች እንዳይወስዱ ኣስታውቀናቸዋል፣ ለወደፊትም እንቀጥላለን። ተማሪዎችንና ቤተስቦቻቸውን መደገፍ ለMCPS ተቀዳሚ ተግባር ነው። የMontgomery County ምክር ቤት በዚህ ጉዳይ ላይ በቅርብ ግዜ ውሳኔ ኣስተላልፏል

MCPS በት/ቤቶቻችን ለፍትህና ለእኩልነት ግዴታውን ማጠናከር ይቀጥላል። ለሚመጣው ኣመት የተረቀቀው የስራ ማስኬጃ በጀት፣ የተማሪዎችን ስኬት ለመደገፍ እንደ ሞራላዊ ሰነድ ሆኖ የሚያገለግለው፣ እንደ የኣናሳ ምሁራን ፕሮግራም ለተማሪዎችና የኣድልዎ ስልጠና ለሰራተኞች የመሰሉ፣ ለፍትህ እነሳሺዎች ግዴታ የተገባ ገንዘብ እንዲያንፀባርቅ ተደርጓል።

የ2018ን በጀት ኣመት የስራ ማስኬጃ በጀት ረቂቅ ኣንብቡ

የት/ቤታችን ስርኣት ተልእኮ እያንዳንዱ ተማሪ በኮሌጅና በስራ ስኬታማ ለመሆን የሚያስፈልጓቸው የኣካዴሚ፣ የፈጠራ ፕሮብሌም ፍቺ፣ እና ስሜታዊ ክሂሎቶች እንዲኖራቸው ማረጋገጥ ነው። ይህን ግብ እንዲመቱ ለማገዝ፣ በቅድሚያ ሰላማዊ፣ ጋባዥ ቦታ ለሁሉም ተማሪዎች እንዲማሩ ማቅረብ ኣለብን። የትምህርት ቦርድ የሁሉንም ተማሪዎች ደህንነት የሚጠብቁና ከማንኛውም ኣይነት ወከባ፣ መሸማቀቅ ወይም ኣድልዎ የሚከላከሉ መመርያዎች በሃይል ኣራምዷል ደንግጓልም በዚሁ ይቀጥላልም።

ለእርስዎ እና ለቤተሰብዎ መልካም ኣዲስ ኣመት እመኛለሁ

አክባሪዎ፣
Michael A. Durso ማይክል ዱርሶ
ፕረዚደንት፣ የMontgomery County የትምህርት ቦርድ