Is this email not displaying correctly? View it in your browser. Date: February 22, 2018

mcps logo

English | español | 中文 | français | tiếng Việt | 한국어| አማርኛ

ከ ጃክ አር. ስሚዝ/Jack R. Smith የትምህርት ቤቶች ዋና የበላይ ተቆጣጣሪ/Superintendent የተላለፈ መልእክት
የትምህርት ቤት ደህንነት

የተከበራችሁ የMCPS ማህበረሰብ፦

ይህንን መልእክት የማስተላልፈው፤ በፓርክላንድ፣ ፍሎሪዳ (Parkland, Fla) በቅርቡ በት/ቤት የተፈፀመ የግድያ/ክስተት ምክንያት በርካታ ጥያቄዎችን፣ አስተያየቶችን፣ ስጋቶቻችሁን እና ነቀፌታም ጭምር ስላቀረባችሁልን ላመሰሰግናችሁ እና የትምህርት ቤቶቻችንን ደህንነት ለመጠበቅና ለጠቅላላ ተማሪዎቻችን ሰላማዊ የመማሪያ ስፍራ ሆኖ እንዲቀጥል ተግተን እየሠራን መሆኑን ለማረጋገጥ ነው።

በመላው አገሪቱ፣ የሞንጎመሪ ካውንቲ የህዝብ ት/ቤቶችን (MCPS) ጨምሮ፣ ከፌብሯሪ 14 አሰቃቂ ሁኔታ ወዲህ ማስፈራራት እና ማስጠንቀቂያዎች እየጨመሩ መሄዳቸውን በመገናኛ ብዙሃን ሪፖርቶች ተመልክታችሁ ይሆናል። እነዚህ ዛቻዎች እና ሪፖርቶች የሚሰነዘሩት ከማህበራዊ መገናኛዎች፣ ኢ-ሜይሎች፣ በስልክ ጥሪዎች፣ እና በአካል በሚደረጉ ንግግሮች ነው። ምንም እንኳ አብዛኛዎቹ የማስፈራራት መልእክቶች ትክክለኛ አለመሆናቸው ቢረጋገጥም፣ በእኛ በኩል እያንዳንዱን ሪፖርት በትኩረት እና ጥንቃቄ በመውሰድ ጥብቅ ክትትል እና ምርመራ እንዲደረግ ከሞንጎመሪ ካውንቲ የፖሊስ ዲፓርትመንት ጋር በቅርበት እየሠራን ነው። እባካችሁ ማንም ሰው በ MCPS ትምህርት ቤት ላይ ማስፈራሪያና ዛቻ ሲያደርግ ከተገኘ ወደ ህግ አስከባሪዎች የሚተላለፍ መሆኑን እንድታዉቁ እንወዳለን።

በተጨማሪም በክላርክስበርግ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት (Clarksburg High School) ጥይት የጎረሰ ሽጉጥ ይዞ ስለተገኘው ተማሪ በቁጥጥር ስር የመዋሉን ሁኔታ በአጭሩ ለማህበረሰቡ ለመግለጽ/ኢንፎርሜሽን ለመስጠት እፈልጋለሁ። የክላርክስበርግ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ርእሰ መምህር ኤድዋርድ ኦዉሱ/Clarksburg High School Principal Edward Owusu ባለፈው ሳምንት ለት/ቤት ማህበረሰብ እንደገለጹት፤ ተማሪው በት/ቤት ንብረት ውስጥ ሽጉጥ ይዞ መገኘቱን ሪፖርት እንደተደረገ፣ የት/ቤት ንብረት የጥበቃ መኰንን በአቸኳይ የተማሪውን ሽጉጥ በመውረስ ተማሪው እንዲታሰር ተደርጓል። በተጨማሪም፣ የሞንጎመሪ ካውንቲ የፖሊስ ዲፓርትመንት በመገናኛ ብዙሃን፣ የሰጠው መግለጫ ከተማሪው የተገኙት ዶኩመንቶች ስለማስራራትም ይሁን ዛቻን በተመለከተ ወይም ሌላ በት/ቤት በማንም ላይ ጉዳት የማድረስ ቃል እንዳልተገኘ ገልፀዋል።

እነዚህ ሁኔታዎች በትምህርት ቤቶች ደህንነት፣ በተማሪዎቻችን፣ በቤተሰቦች እና በሠራተኞች ላይ በመላ አገሪቱ ፍራቻ እና ስጋት መፍጠራቸውን እናውቃለን። በት/ቤቶቻችን የሁሉም ተማሪዎች ደህንነት አስተማማኝ መሆኑን MCPS በቁርጠኝነት ያረጋግጣል። የትምህርት ቤቶቻችን እና የተማሪዎቻችንን አካላዊ ደህንነት/ሰላም ለማረጋገጥ MCPS የአስቸኳይ ሁኔታ ዝግጁነት እና የተዘጋጀ የደህንነት አጠባበቅ ሥርአት/security protocols አለው። የአእምሮ ህመምን ለመርዳት፣ የ MCPS ካውንስለሮች፣ ሳይኮሎጂስቶች እና ሌሎችም መገልገያዎች በአገርአቀፍ እና በአካባቢ ደረጃ በሚሆኑ ነገሮች ተማሪዎችን ለመርዳት እንዲያስችላቸው ለት/ቤቶች እና ለሠራተኖች ተመድበዋል።

አንዳንዶቹ ተማሪዎች ይህንን ኢንፎርሜሽን የሚያራምዱት በትምህርት ቤት ውስጥ ሌላ ግድያ እንዳይፈጠር ለመከላከል የሚያስችል ህግ እንዲሰፍን ድምፃቸውን ለማሰማትና ለማቀንቀን ነው። በሚሰማቸው ጉዳይ ላይ የዜግነት ሀሳባቸውን በጥልቅ ስሜት በመግለጽ የሚሳተፉ ተማሪዎችን MCPS ይደግፋል። ብዙዎቹ የመካከለኛ ደረጃ እና የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች ከርእሰ መምህራኖቻቸው ጋር በትምህርት ቀን ድምፃቸውን ከፍ አድርገው ለማሰማት ሠዓት እንዲሰጣቸው በመነጋገር አድርገዋል። ይህ የሚያረጋግጠው ተማሪዎች ድጋፍ ባለው ሁኔታ እና ሰላማዊ አካባቢ ላይ ሃሳባቸውን ለመግለጽ መቻላቸውን ነው።

ሆኖም ግን፣ በትላንትናው ቀን በርካታ የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች ወደ ዩ.ኤስ ካፒቶል (U.S. Capitol) በመሄድ ሃሳባቸውን ለማስተጋባት/ለማቀንቀን ት/ቤት ለቀው ሄደዋል። ተማሪዎች ሃሳባቸውን አጠንክረው መግለፃቸውን የሚደገፍ ቢሆንም፣ ከት/ቤት ግቢ ውጪ ለቆ መውጣት በተለይም በት/ቤቶች ላይ ማስፈራት እየጨመረ በሄደበት ወቅት ከባድ የደህንነት ስጋት ሊያስከትል ይችላል። ተማሪዎች በት/ቤት ክልል ግቢ ውስጥ ካልሆኑ በስተቀር የተማሪዎችን ደህንነት ለመጠበቅና ለማረጋገጥ MCPS ሠራተኞች እና መገልገያዎች አይኖሩትም። በተጨማሪም፣ ት/ቤቶች ለቀው እንዲወጡ/evacuate የሚያስደርግ ሁኔታ ቢፈጠር ት/ቤት ባለመገኘታቸው ምክንያት የትኛው ተማሪ እንዳለ/እንዳለች ወይም እንደሌለ /እንደሌለች ተቆጣጥሮ ለማወቅ በጣም አስቸጋሪ ይሆናል።
በዚህ አስቸጋሪ ወቅት፣ ተማሪዎችን በማረጋጋት፣ በማበረታታት እና በማጽናናት የሚተጉ ሠራተኞቻችንን ለማመስገን እፈልጋለሁ። ከመምህራን፣ ከድጋፍ ሰጪ ሠራተኞች እና ከአስተዳዳሪዎች የሚሰጡ መልካም የማበረታቻ ቃሎች መልካም ለውጥ እንደሚያመጡ እተማመናለሁ። እየጨመረ የመጣውን ማስፈራሪት ለመመከት በምናደርገው ጥረት ህግ አስከባሪዎችም በቅርብ ከእኛ ጋር አብሮ በመሥራት አጋሮቻችን በመሆናቸው ለማመስገን እወዳለሁ። ለጥያቄዎቻችን የሚሰጡት ትኩረት እና ፈጣን ምላሽ እጅግ ጠቃሚ አለኝታችን ነው።

ዓላማችን ትምህርት ነው፣ ደህነት/ሰላም ምንጊዜም ቅድሚያ የምንሰጠው ትኩረታችን ነው። ሠራተኞች፣ ተማሪዎች እና ቤተሰቦች  አጠራጣሪ ነገር ካያችሁ፣ ማሳወቅ አለባችሁ/“see something, say something.” የሚለውን መርህ በንቃትና በመጠበቅ የተማሪዎቻችን ደህንነትና ሰላም የተረጋገጠ እንዲሆን እንጠይቃለን።

ከማክበር ሰላምታ ጋር፣

Jack R. Smith
Superintendent of Schools
ጃክ አር. ስሚዝ
የት/ቤቶች ዋና የበላይ ተቆጣጣሪ