‌ ‌ ‌ ‌ ‌ ‌ ‌ ‌ ‌ ‌ ‌ ‌ ‌ ‌ ‌ ‌ ‌ ‌ 
All In blog by MCPS Superintendent Dr. Jack R. Smith

"ልጆቻችን ከህዝባችን 20 ፐርሰንት ናቸው፣ ነገር ግን የወደፊታችን 100 ፐርሰንት ናቸው።"
—የቀድሞው የትምህርት ኃላፊ ሪቻርድ ራይሌ-Former Secretary of Education Richard Riley

ከአራት ዓመት በፊት የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ የሱፐርኢንተንደንትነት ሥራ በጀመርኩበት ቀን፣ ከፊትለፊቴ እጅግ ከባድ ኃላፊነት እንደሚጠብቀኝ አውቅ ነበር። ተልእኮው ግልጽ ነበር። ለሁሉም ተማሪዎች የትምህርት ተደራሽነትን፣ እና የትምህርት እድሎችን በየደረጃው በማስፋት፣ በተለይም ከለር ተማሪዎችን፣ በድህነት ያሉ ተማሪዎችን፣ እና ስፔሻል ኢጁኬሽን የሚያገኙ ተማሪዎች እና ከሌላ ቋንቋ ተናጋሪዎች የእንግሊዝኛ ቋንቋ (ESOL) ተማሪዎችን ሁሉ የሚያካትት የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) የረዥም ጊዜ የልቀት ታሪክ መጠበቅ እንዳለበት የትምህርት ቦርድ እና እኔ ተስማምተናል። ይህንን የትምህርት ሲስተም የረዥም ዘመናት መለያ የሆነውን የትግበራ እና የትምህርት ልቀት እየጠበቅን ስንሠራ ቆይተናል።

ከ 2016-2017 የትምህርት ዓመት ጀምሮ፣ ሁለት የመካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችን እና ሁለት የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችን ከፍተናል። በተጨማሪም፣ አንድ መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት፣ ሦስት የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት፣ እና ቶማስ ኢድሰን የቴክኖሎጂ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት-Thomas Edison High School of Technology እንደገና አደራጅተናል፣ አሻሽለናል፣ አስፋፍተናል። በ 2020-2021 የትምህርት ዓመት፣ ሦስት የኤለመንተሪ ትምህርት ቤቶችን፣ ሁለት ስፔሻል ኢጁኬሽን ትምህርት ቤቶችን፣ አንድ የመካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እና አንድ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የማሻሻል፣ የማስፋፋት፣ እና የማደራጀት ሥራ ይጠናቀቃል። የእኛ ከ K–12 ምዝገባ ቁጥር በ 5,897 ተማሪዎች ጨምሯል። 660 ተማሪዎች ከግማሽ ቀን ወደ ሙሉ ቀን ፕሮግራሞች ተሸጋግረዋል፣ እና አምስት የቅድመ ምዋእለ ህፃናት ትምህርቶችን እና ሁለት "early childhood" የትምህርት ማእከላትን—MacDonald Knolls የጨመርን ሲሆን፣ ይህም 118 ተማሪዎችን እና በ Emory Grove የሚገኘው "Upcounty Early Childhood Center" 80 ተማሪዎችን ጭምር ያገለግላል። አምስት የጥንድ-ቋንቋ ፕሮግራሞችን፣ እና ሁለት የኤለመንተሪ ትምህርት ቤቶችን የጨመርን ሲሆን፣ ሮስኮ አር. ኒክስ እና አርኮላ (Roscoe R. Nix and Arcola) ከተለመደው የ 182 የትምህርት ቀኖች ይልቅ የ210 ቀናት የትምህርት ዓመት ካለንደር በመጠቀም ሁለተኛ ዓመታቸውን ጀምረዋል።

በተጨማሪ፣ የኤለመንተሪ እና የመካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የዳበረ ፕሮግራም በመምረጥ ሒደት በርካታ መመዘኛዎችን በመጠቀም ከመሻሻሉም በላይ፣ ለኤለመንተሪ ት/ቤት ተማሪዎች የዳበረ ትምህርት ማእከል ከ189 በላይ መቀመጫዎች ተጨምረዋል። በ 37 የመካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ሁለት የዳበሩ ኮርሶች ተጨምረዋል። ለሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ሦስት አዳዲስ የሪጅናል "International Baccalaureate" ማእከሎች ተጨምረዋል፣ እና ባለፉት ሦስት ዓመታት 32,311 አዳዲስ ተማሪዎች "Advanced Placement ወይም International Baccalaureate" ኮርሶችን ወስደዋል። ከእነዚህ ተማሪዎች መካከል ከ 48.3 ፐርሰንት በላይ አፍሪካን አሜሪካንስ፣ ሂስፓኒክ እና/ወይም በድህነት ወለል ከሚገኙ ከሁሉም አይነት ዘር ናቸው።

በሞንትጎመሪ ኮሌጅ (Montgomery College) በጥንድ የሚወሰድ ትምህርት ምዝገባ እና ቅድመ ኮሌጅ ፕሮግራሞች ተፈጥረዋል ሰፍተዋልም። በ 2020 ተመራቂ ተማሪዎች ላይ 44 የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ዲፕሎማ እና የአሶሽየት ሳይንስ ዲግሪ በአንድ ላይ ያገኙ ተማሪዎች ተጨምረዋል። አሁን ባለው ምዝገባ ላይ በመመስረት፣ ይህ ቁጥር በ 2023 ከ1,100 ተመራቂዎች በላይ እንደሚጨምር የሚጠበቅ ሲሆን፣ አሶሽየት ኦቭ ሳይንስ፣ አሶሽየት ኦቭ አርትስ፣ እና አሶሽየት ኦቭ አፕላይድ ሳይንስ ዲግሪዎችን በ 15 የተለያዩ ፓዝዌይስ ይጨምራል።

ባለፉት ሁለት ዓመታት፣ ለተማሪዎች በ "aviation, cybersecurity, network operations, biomedical sciences, fire science and rescue, law enforcement, construction management and hospitality management" በመሣሠሉት አዳዲስ ፈጣን እና ጠንካራ የሙያ ዝግጅት እና በኢንዱስትሪ-ተቀባይነት ያለው ሠርተፊኬት የሚያስገኙ ፕሮግራሞች ከፍተኛ ተፈላጊነት ባላቸው የሙያ ዘርፎች የሥራ ግብረኃይል ለማዘጋጀት ጥረት ተደርጓል።

ባለፉት አራት ዓመታት፣ የሠራተኞችን ቁጥር በመጨመር እያደገ የሄደውን የተማሪዎች ቁጥር ግምት ውስጥ በማስገባትና እያንዳንዱን ተማሪ በመርዳት የተማሪዎቻችንን ከፍተኛ ፍላጎት ያማከለ አገልግሎት ለመስጠት ያለንን ቁርጠኝነት አሳይተናል። ከ150 በላይ የሙሉ ጊዜ የስፔሻል ኢጁኬሽን ባለሙያዎች የተጨመሩ ሲሆን፣ ከ102 በላይ የ ESOL ሠራተኞም አሉን። 35 ፐርሰንት ወይም ከዚያ በላይ በድህነት ወለል ያሉ ተማሪዎች ለሚገኙባቸው የኤለመንተሪ ትምህርት ቤቶች፣ 25 ፐርሰንት ወይም የበለጠ የድህነት ወለል ለሚገኙባቸው የመካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች፣ እንዲሁም 20 ፐርሰንት ወይም የበለጠ የድህነት ወለል ላይ ለሚገኙ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ትኩረት የሚሰጡ አስተማሪዎች ተጨምረዋል። ከዚህም በላይ፣ የተማሪዎችን አካላዊ፣ ማህበራዊ እና ስነልቦናዊ ደህንነት ለመደገፍ-ለመርዳት ከ75 በላይ የትምህርት ቤት ካውንስለሮች፣ ተማሪዎችን የሚረዱ ሠራተኞች፣ ሶሻል ዎርከሮች፣ የ ESOL ትራንዚሽን ካውንስለሮች፣ ሳይኮሎጂስቶች እና የወላጆችና የማህበረሰብ አስተባባሪ ሠራተኞች ተጨምረዋል።

ይህ ሥራ መከናወን የቻለው አስፈላጊነቱን-አስቸኳይነቱን በመገንዘብ እና በሠራተኞቻችን ጥረት ነው። መምህራን፣ የቢሮ ሠራተኞች፣ ፓራኢጁኬተሮች፣ አስተዳዳሪዎች እና ሌሎች የሥራ ባልደረቦች ግንኙነት ገንብተዋል፣ እድሎችን አስፍተዋል እና የተማሪዎችን የማይገደብ ችሎታ በትምህርት ትኩረት እንዲውል አድርገዋል። ውጤቶችን ማየት ጀምረናል።

ይህ ሊከናወን የቻለው ስለሁሉም ተማሪዎች የመማር አስፈላጊነት መሠረታዊ መረጃ-ኢንፎርሜሽን፣ የግንዛቤ መጨመር እና በ ፍትሃዊነት-ሚዛናዊነት እና የስኬት ማእቀፍ ላይ በመመስረት ነው ። በዚህ ማእቀፍ ውስጥ በዘረኝነት፣ ባህል፣ በገቢ መጠን ማነስ፣ በስንክልና እና በቋንቋ ልዩነት ምክንያት ያለማቋረጥ የቀጠሉ ልዩነቶችን መፍትሔ ለመሻት ይረዳናል። በአንዳንድ ሁኔታዎች ዙርያ ጥሩ የመሻሻል እርምጃ ያሳየን ቢሆንም፣ "add one pager link here" ገና ብዙ የሚሠሩ ነገሮች ይቀራሉ። የተሻለና የበለጠ ተደራሽነት እና ሚዛናዊነትን ለማስፈን ትጥቅ እንዲሆኑን ማስረጃ እና መረጃ-Data and evidence በጣም ወሳኝነት አላቸው። ተማሪዎቻችን በሙሉ በትክክል እየተማሩ መሆናቸውን ለማረጋገጥ በርካታ መስፈርቶችን መጠቀም ይኖርብናል። በትኩረት መቀጠል አለብን።

ከ 2019–2020 የትምህርት ዓመት 75 ፐርሰንቱን ያህል፣ በማስተማሪያ ክፍሎቻችን እና በትምህርት ቤቶቻችን ውስጥ ይህንን ሥራ እየሠራን ነበር። ማርች 16፣ ተማሪዎች ወደ ትምህርት ቤት ህንፃዎች መምጣት ያቆሙበት ቀን ሲሆን—ሁላችንም በስጋት—ጁን 15 የትምህርት ዓመቱ ከመጠናቀቁ በፊት ለመመለስ አልቻልንም። አሁን፣ ለተማሪዎቻችን እንደገና በማለም እና የትምህርት ቤት መሠናዶ በማድረግ ዳግመኛ ተጋፍጠናል። ነገር ግን ዳግም ማሠናዳቱ እና ዳግም ትልማችን በሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ ለእያንዳንዱ ተማሪ ፍትህ እና ሚዛናዊነት እንዲሰፍን እና ትምህርትን በከፍተኛ ጥራት ላለመስጠት ምክንያት ሊሆኑ አይችሉም። ተማሪዎቻችን በእኛ ይመካሉ። እኛስ ለእነርሱ አለንላቸው?

ይህንን ሃላፊነት በጀመርኩበት ጊዜ ለእያንዳንዱ(ዷ) ተማሪ ትምህርት እና እድሎችን ለመፍጠርና ለማስፋት ቃል የገባሁትን ኃላፊነት ዛሬም ከአራት ዓመት በኋላ፣ ይህንኑ ከፍተኛ ኃላፊነት በመቀበል ቀጥያለሁ። ከእኔ ጋር ይሆናሉ?

Take care and be well,
Jack Smith

 
Montgomery County Public Schools

View as a Web Page

Montgomery County Public Schools
850 Hungerford Drive, Rockville, MD, 20850
Call: 240-740-3000 | Spanish Hotline: 240-740-2845