በሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ውስጥ ተቋማዊ ዘረኝነትን ለመፈተሽ እና ለመፍታት የፀረ ዘረኝነት ኦዲት

February 2, 2022

ለተከበራችሁ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ማህበረሰብ፦

ይህንን ደብዳቤ የጻፍንበት ምክንያት በ MCPS ውስጥ የዘር እና ስርዓት አቀፍ መሰናክሎችን ለመፍታት የዲስትሪክታችንን ቀጣይ ስራ እና ቁርጠኝነት በተመለከተ ወቅታዊ መረጃ ለመስጠት ነው።

የማህበረሰብ አባላት ጣቶቻቸውን በመቀሳሰር ወደ ወገንተኝነት ሲያዘነብሉ በአገሪቱ ዙሪያ ያሉ የትምህርት ቤት ዲስትሪክቶች እነዚህን መሰናክሎች በመጋፈጥ አስቸጋሪ ውይይቶችን በማድረግ እየታገሉ ቆይተዋል። ይህ የእኛ መረጃየቅርብ ጊዜ ተሞክሮዎችን የመረዳት አስፈላጊነት እና ኮቪድ-19 ማህበረሰቡን እንዴት እንደጎዳው ያለውን ልዩነት መረዳት የዚህን ስራ አስፈላጊነት አጽንኦት ተሰጥቶታል።

ይህንን አስፈላጊነት ከግምት ውስጥ በማስገባት ባለፈው ዓመት "የፀረ-ዘረኝነት ስርዓት አቀፍ መሰናክል ኦዲት" የተባለውን የዲስትሪክታችንን ፖሊሲዎችና ተግባራት መገምገም ጀምረናል። ባለፉት ጥቂት ወራት፣ በኦዲት ላይ አስተያየት ለማግኘት እና ስጋቶችን እና ጥያቄዎችን ለመስማት ከተማሪዎች፣ ቤተሰቦች፣ ሰራተኞች እና የማህበረሰብ አባላት ጋር ተገናኝተናል። አንዳንዶች ኦዲቱ የት/ቤት ዲስትሪክቱ ማድረግ ያለበትን ገደብ እያለፈ ነው ብለዋል። ሌሎች ደግሞ ብዙ ርቀት እንዳልሄድን ገልጸውልናል። ስለ ድርጊቱ እምነት ማግኘት ጊዜ የሚወስድ በመሆኑ ኦዲቱ ምን ማለት እንደሆነ እኛ የምናምንበትን ነገር ማስረዳት እንፈልጋለን።

Antiracist Audit 1 Pager
Click to View Full PDF
  • ኦዲቱ አጠቃላይ እና ዲስትሪክት አቀፍ የአሰራሮቻችን እና የፖሊሲዎቻችን ግምገማ ነው። የተለያዩ የኦዲት ጭብጦችን ለማንበብ እዚህ ጠቅ ያድርጉ
  • ኦዲቱ የሚካሄደው እውነተኛ/ተጨባጭ መረጃ ፍለጋ ነው። የተገኘውን የኦዲት ውጤት መሰረት በማድረግ መወሰድ ያለበት እርምጃ ይወሰናል።
  • ኦዲት የሚደረገው በማንም ላይ ጣት ለመቀሰር አይደለም። ሌሎች በፈጸሙት ድርጊት ምክንያት ማንንም፣ የትኛውንም ቡድን መውቀስ ወይም ማዋረድን በቸልታ ዝም አንልም።

የሚቀጥለው የኦዲት ምዕራፍ ከሁሉም ባለድርሻ አካላት በዳሰሳ ጥናት ከትኩረት ቡድኖች መስማት ነው። ስለ ተማሪ፣ ሰራተኞች እና የቤተሰብ ዳሰሳዎች እንዲሁም ስለመጪው የማህበረሰብ ውይይቶች መረጃ ለማግኘት እባክዎ በስተቀኝ ያለውን ግራፊክ ይመልከቱ። እባክዎን ተጨማሪ ዝርዝሮችን ለማግኘት ይከታተሉ። የኦዲት ግኝቶችን ጁን 2022 ለመላው ማህበረሰብ የምናጋራ ሲሆን ሁሉም የ MCPS ትምህርት ቤቶች እና ጽ/ቤቶች በመጪው ሠመር የተግባር እቅድ ያዘጋጃሉ። ወቅታዊ የድርጊት መረጃዎች በዚህ ድረ-ገጽ ላይ ይፋ ይሆናሉ።

ይህ ደብዳቤ የተጻፈው ከ MCPS ዋና መስሪያ ቤት፥ ካርቨር የትምህርት አገልግሎት ማዕከል መሆኑ ይታወቃል። ይህ ታሪካዊ ቦታ ከሞንትጎመሪ ካውንቲ የሚመጣ እያንዳንዱ ጥቁር የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪ የትም ይኑር የትም እየመጣ(ች) የሚማርበት - የምትማርበት ትምህርት ቤት ነበር። ይህ እውነታ ዘረኝነት በዋና መዋቅሮቻችን ውስጥ እንዴት ስር የሰደደ እንደነበረ ያስታውሰናል። ይሁን እንጂ እኛ የዲስትሪክት መሪዎች እንደመሆናችን በአሁኑ ወቅት በአገሪቱ ውስጥ ካሉት እጅግ በጣም ስብጥር ያለው እና ስኬታማ ከሆኑት ዲስትሪክቶች አንዱ በሆነው በዚህ ሕንፃ ውስጥ እንገኛለን። ሁሉም ተማሪዎች፣ ቤተሰቦች እና ሰራተኞች ደህንነት የሚሰማቸው፣ የሚከበሩበት፣ የሚታዩበት፣ የሚደመጡበት እና ስኬታማነት የሚሰማቸው የት/ቤት ዲስትሪክት እንደሆነ እንዲሰማቸው ለማድረግ ይህንን ኦዲት ልንጠቀምበት እንደምንችል ተስፋ እናደርጋለን።

ከልብ የሆነ

Dr. Monifa McKnight
Interim Superintendent
Montgomery County Public Schools 



Email us: ASKMCPS@mcpsmd.org

Montgomery County Public Schools