MCPS 2021-22 Fall Reopening Guide

Montgomery County Public Schools
2021-2022 እንደገና የመክፈት መመሪያ

August 13, 2021

በፎል እንደገና ስለመክፈት ድረ -ገፅ ያንብቡ

የሞንትጎመሪ ካውንቲ የትምህርት ቦርድ እና የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ተማሪዎቻቸውን ማኅበራዊ፣ ስሜታዊ እና ትምህርታዊ ፍላጎቶቻቸውን በማሟላት የሚገባቸውን ዓለም አቀፍ ደረጃ የጠበቀ ትምህርት ለመስጠት ቁርጠኝነት አላቸው። ይህ ቁርጠኝነት በአስተማሪዎች፣ በአስተዳዳሪዎች፣ በአገልግሎት ድጋፍ ሰጪ ሠራተኞች፣ በወላጆች እና በማህበረሰቡ በጋራ የሚከናወን ነው።

የተማሪዎቻችን እና የሰራተኞቻችን ጤና እና ደህንነት ቅድሚያ ትኩረት ሊሰጣቸው ይገባል። ምንም እንኳን፣ COVID-19 ከእኛ ጋር የሚቆይ ቢሆንም፣ MCPS ለሁሉም ተማሪዎቻችን በሳምንት ለአምስት ቀናት በአካል ትምህርት ለመስጠት የገባውን ቃል ለመፈጸም ይጥራል። ወደ ት/ቤት በሰላም መመለስን ለማረጋገጥ እቅድ አውጥተናል እና በየጊዜው የሚለዋወጡ ሁኔታዎችን ለመቋቋም በንቃት እንቀጥላለን። ከዚህ በተጨማሪ የዚህ ዕቅድ ስኬት በግለሰባዊ ድርጊቶች ላይ የሚመረኮዝ ነው፣ ስለሆነም የትምህርት ዓመት ከመጀመሩ በፊት ክትባት መውሰድ የሚችል እያንዳንዱ ሰው ክትባት እንዲወስድ አጥብቀን እናበረታታለን።

ባለፈው የትምህርት ዓመት ከዚህ በፊት ታይቶ የማይታወቅ ተግዳሮቶች ገጥመውናል፣ ነገር ግን ለተማሪዎቻችን ደህንነቱ በተጠበቀ ሁኔታ ከፍተኛ ጥራት ያለው ትምህርት ለመስጠት ከመቼውም ጊዜ በላይ ቆርጠን ተነስተናል። ተማሪዎቻችንን፣ መምህራኖቻችንን፣ ሰራተኞቻችንን እና ማህበረሰቡን ለመጠበቅ የሚከተሉትን እርምጃዎች እንወስዳለን፦

  • የክትባት ሁኔታ ምንም ይሁን ምን በሁሉም የትምህርት ቤት ሕንፃዎች፣ በት/ቤት አውቶቡሶች ውስጥ እና የ MCPS ፋሲሊቲዎች/ተቋማት ውስጥ የፊት መሸፈኛዎችን መጠቀም-መልበስ አስፈላጊ ነው
  • ሰራተኞች የክትባት ማስረጃ እንዲያቀርቡ ወይምበየሳምንቱ በ COVID-19 ምርመራ እንዲሳተፉይጠበቅባቸዋል
  • ጭምብል መጠቀም ለማያስፈልጋቸው ትምህርታዊ፣ የመዝናኛ እና ማህበራዊ እንቅስቃሴዎች ተማሪዎቻችን ከቤት ውጭ የሚገኙ ቦታዎችን እንዲጠቀሙ እናበረታታለን
  • በኳራንቲን ምክንያት በአካል ተገኝተው መማር ለማይችሉ ተማሪዎች በያሉበት የትምህርት አገልግሎቶችን ቀጣይነት እናመቻቻለን
  • በተደጋጋሚ እጅ መታጠብን በመሳሰሉ የመከላከል ጥንቃቄ እርምጃዎችን በንቃት እንዲተገብሩ ለግለሰቦች እድል ይሰጣቸዋል
  • የ COVID-19 ምልክቶች በሚታይባቸው ጊዜ ተማሪዎች እና ሰራተኞች ቤት መቆየት እንዳለባቸው ተከታትለን እናስታውሳቸዋለን
  • የትምህርት ቤት መገልገያዎች በመደበኛነት ንፅህናን፣ የፅዳት አቅርቦቶችን እና የአየር ማናፈሻ እና የአየር ጥራት ቁጥጥርን እናረጋግጣለን
  • ዕድሜያቸው ከ 12 ዓመት በታች የሆኑ ተማሪዎች ክትባቱን ለመቀበል ብቁ ባለመሆናቸው ከቅድመ መዋዕለ ሕጻናት እስከ 6ኛ ክፍል ላሉ ተማሪዎች የዘፈቀደ ናሙናዎች COVID-19 ምርመራ በትምህርት ቤት ውስጥ ይሰጣል።
  • መረጃ በሚኖርበት ጊዜ ከቤተሰብ እና ከሠራተኞች ጋር ግልጽና አጭር ወቅቱን የጠበቀ መልክት በመቀባበል ግንኙነት ይደረጋል
  • ተማሪዎቻችን በትምህርታቸው ላይ ትልቅ መስተጓጎል እንዳይገጥማቸው ለተለዋዋጭ ሁኔታዎች ተገቢ ምላሽ ይሰጣል

በትብብር አብረን በመስራት፣ ተማሪዎቻችን ወደ ትምህርት ቤት ሲመለሱ በደህና መማር እና ማደግ እንደሚችሉ ማረጋገጥ እንችላለን። እነርሱ በአገሪቱ ውስጥ ከፍተኛ እውቀት የተካኑ እና ቁርጠኝነት ያላቸው የትምህርት ባለሙያዎች የሚረዷቸው ስለሆነ፣ እኛም የእነዚህን ባለሙያዎች ቁርጠኝነትና ጥረታቸውን ማድነቃችንን እንቀጥላለን። ለመላው የ MCPS ማህበረሰብ የገባነው ቃል ለሁሉም ተማሪዎች መልካም የትምህርት ዘመን እንዲሆን ስኬታማ ጅማሮን ለማሳካት ወሳኝ እርምጃዎች ናቸው።

በፎል እንደገና ስለመክፈት ድረ -ገፅ ያንብቡ

እንደገና ስለመክፈት መመሪያውን ያንብቡ

ከሰላምታ ጋር

ብረንዳ ዎልፍ፥ የሞንትጎመሪ ካውንቲ የትምህርት ቦርድ ፕሬዚደንት

ሞኒፋ ቢ. መክኒይት (ዶ/ር) ጊዜያዊ የትምህርት ቤቶች ሱፐርኢንተንደንትEmail us: ASKMCPS@mcpsmd.org

Montgomery County Public Schools