የትምህርት ቤት የጤና እና የጤንነት እንቅስቃሴ ማእከላት በሠመር ወራት የአእምሮ ጤና አገልግሎት ይሰጣሉ

July 19, 2022

ውድ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ቤተሰቦች

የሞንትጎመሪ ካውንቲ የጤና እና የሰብአዊ አገልግሎት ዲፓርትመንት (DHHS) በካውንቲው 14 የMCPS ትምህርት ቤቶች የጤና እና የደህንነት ማዕከላት ውስጥ አገልግሎት ይሰጣል። አጠቃላይ የበሽታ መከላከል የጤና እንክብካቤ፣ የታማሚዎች ህክምና፣ የአእምሮ ጤና፣ ማህበራዊ አገልግሎቶች እና ሌሎች በተለመደ እና ለቤተሰብ ተስማሚ በሆነ አካባቢ አዎንታዊ የወጣቶች እድገትን የሚያበረታቱ አገልግሎቶች ይሰጣሉ። አንዳንድ አገልግሎቶች ዓመቱን ሙሉ እና ሌሎች ደግሞ ትምህርት ባለበት ወቅት የሚሰጡ ናቸው።

የተማሪ የአእምሮ ጤና አገልግሎቶች (ዓመቱን በሙሉ አገልግሎት ይሰጣሉ)

  • አዎንታዊ የወጣቶች እድገት
  • ከትምህርት በኋላ ፕሮግራሞች
  • የአእምሮ ጤና አገልግሎት
  • ኬዝ ማኔጅመንት (ጉዳይ የማስፈጸም) አገልግሎት
  • ለተማሪዎች የምርመራ አገልግሎት
  • የልጅ / የቤተሰብ ሕክምና
  • መከላከል/ክህሎት ማዳበር/ለተማሪዎች የምክር አገልግሎት ቡድኖች

የተማሪ የአካል ጤንነት አገልግሎቶች (በትምህርት አመቱ የሚሰጡ አገልግሎቶች)

  • ስፖርት የአካል ብቃት ምርመራ - MCPS የአትሌቲክስ ቅጾች (ኦገስት ላይ የእርስዎን የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የአካላዊ ደህንነት ማእከልን ያግኙ)
  • የማየት እና የመስማት ምርመራዎች
  • የመለስተኛ/አጣዳፊ/ ሥር የሰደደ የጤና ችግሮች ምርመራ እና ሕክምና
  • የአባላዘር በሽታ (STI) መከላከል፣ ምርመራ እና ምክር
  • የእርግዝና መከላከያ ምክር
  • የላብራቶሪ ምርመራ
  • የህፃናት ክትባቶች (VFC)-ብቁ ተማሪዎች
  • ለሁሉም ተማሪዎች የኮቪድ-19 ፈጣን/ PCR ምርመራ እና ክትባቶች
  • ህክምናዎች
  • የጥርስ ህክምና ተደራሽነት (የጥርስ ቫርኒሽ እና የጥርስ ህክምና አገልግሎት ሪፈራል ይሰጣል)
  • የጤና ትምህርት እና የምክር አገልግሎት በግለሰብ፣ በክፍሎች፣ የጤና ትርኢቶች ወይም በሰለጠኑ የጤና ባለሙያዎች ይሰጣል
  • የቤተሰብ ፍላጎት ዳሰሳ

ሁሉም ቦታዎች ከጠዋቱ 9፡00 a.m. እስከ 6፡00 p.m., ክፍት ናቸው፡ አንዳንዶቹ ረዘም ያለ ሰአት ይኖራቸዋል (ስለ ሰዓቱ ልጅዎ የተመዘገበ(ች)በትን ትምህርት ቤት የጤንነት ማእከል ያነጋግሩ)

ጠቃሚ-ማሳሰቢያ፦

ወላጆች ልጆቻቸው አገልግሎቶችን እንዲያገኙ በጽሁፍ ፈቃድ መስጠት አለባቸው። ሁሉም ቦታዎች በምዝገባ ሂደት ሊረዱ ይችላሉ። በዚያ ቦታ አገልግሎቶችን ለማግኘት ብቁ የሚሆኑት በት/ቤቱ የሚማሩ ተማሪዎች፣ ኢንሹራንስ የሌላቸው ወንድሞች እና እህቶች እና በት/ቤቱ የጤንነት ማእከል የተመደቡ እንክብካቤ የሚደረግላቸው ልጆች እና ተማሪዎች ብቻ ናቸው።

የትምህርት ቤት የጤና ማዕከሎች

ቦታ የስልክ ቁጥር እና አድራሻ

ጌትስበርግ አንደኛ ደረጃ ት/ቤት
Gaithersburg Elementary School

301-926-1628
35 North Summit Avenue, Gaithersburg, MD 20877

ሀርሞኒ ሂልስ አንደኛ ደረጃ ት/ቤት
Harmony Hills Elementary School

240-740-0780
13407 Lydia Street, Silver Spring, MD 20906

ሀይላንድ አንደኛ ደረጃ ት/ቤት
Highland Elementary School

240-740-1758
3100 Medway Street, Silver Spring, MD 20902

ጆአን ለለክ አንደኛ ደረጃ ት/ቤት አት ብሮድ አከርስ
JoAnn Leleck Elementary at Broad Acres

240-740-1902
710 Beacon Road, Silver Spring 20903

ኒው ሃምፕሻየር ኢስቴት አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት
New Hampshire Estates Elementary School

240-740-1570
8720 Carroll Ave., Silver Spring, MD 20903

ሮሊንግ ተሬስ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት
Rolling Terrace Elementary School

240-740-1950
705 Bayfield St., Takoma Park, MD 20912

ሱሚት ሆል አንደኛ ደረጃ ት/ቤት
Summit Hall Elementary School

301-284-4162
101 West Deer Park Road, Gaithersburg, MD 20877

ቬርስ ሚል አንደኛ ደረጃ ት/ቤት
Viers Mill Elementary School

240-740-1000
11711 Joseph Mill Road, Silver Spring, MD 20906

ዌለር ሮድ አንደኛ ደረጃ ት/ቤት
Weller Road Elementary School

301-287-8677
3301 Weller Road, Silver Spring MD 20906

የትምህርት ቤት የጤና ማዕከሎች

ኖርዝውድ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት
Northwood High School

240-740-6988
919 University Blvd. W., Silver Spring, MD 20901

ጌትስበርግ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት
Gaithersburg High School

301-284-4500
101 Education Blvd., Gaithersburg, MD 20877

ዋትኪንስ ሚል ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት
Watkins Mill High School

301-284-4420
10301 Apple Ridge Road, Gaithersburg, MD 20879

ዊትን ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት
Wheaton High School

301-321-3310
12401 Dalewood Dr., Silver Spring, MD 20906

ሴኔካ ቫሊ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት
Seneca Valley High School

240-740-6400
19401 Crystal Rock Dr., Germantown, MD 20874

ከተማሪ ጤንነት ጋር የተያያዙ አስፈላጊ ቅጾች፡ እዚህ በብዙ ቋንቋዎች ይገኛሉ።

ተጨማሪ አገልግሎቶች ይሰጣሉ

የትምህርት ቤቶች ዲስትሪክቱ MCPS ተማሪዎችን እና በችግር ውስጥ ያሉ ቤተሰቦችን ለመደገፍ የተቋቋመ፣ የረዥም ጊዜ ፈጥኖ ደራሽ ፕሮቶኮል አለው። የዲስትሪክቱ መሪዎች፣ ሲነገራቸው፣ ወዲያውኑ የአእምሮ ጤና አገልግሎት ሰጪዎችን አገልግሎት ከሚያስፈልገው MCPS ተማሪ ጋር ያገናኛሉ። እነዚህ ድጋፎች የሚሰጡት ከ DHHS፣ ከካውንቲ ቀውስ ማእከል እና ከሌሎች የካውንቲ የአእምሮ ጤና ክሊኒኮች ጋር በተደረጉ የትብብር ስምምነት የተገኙ ናቸው።

በሠመር ወቅት ስለ አካል የጤና አገልግሎቶች የበለጠ መረጃ ለማግኘት ወደ ብሬንዳ ሩሶ (Brenda Russo) በስልክ ቁጥር 240-777-4492 ለአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የጤና ማዕከል ወይም ወደ ሻሮን ክራው (Sharon Crowe) በስልክ ቁጥር 240-777-4803 ለሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የጤንነት ቁመና ማዕከላት ይደውሉ።


988 Suicide & Crisis Lifeline


Email us: ASKMCPS@mcpsmd.org

Montgomery County Public Schools