ኮቪድ-19 የማህበረሰብ አደጋ ተጋላጭነት ደረጃ ለውጥ  ውድ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ቤተሰቦች

ማክሰኞ፣ ጁላይ 26 ላይ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ወደ ከፍተኛ የኮቪድ-19 የማህበረሰብ አደጋ ተጋላጭነት ደረጃ ተሸጋግሯል፤ ይሄም በኮቪድ-19 የማህበረሰብ ደረጃ መለኪያዎች በየበሽታ መቆጣጠሪያ እና መከላከያ ማዕከሎች (CDC) በተቀመጠው መሰረት ነው። ይሄ የተቀናጀ የአደጋ ተጋላጭነት መለኪያ ሰዎች በማህበረሰባቸው ውስጥ ስለሚፈጠሩ ነገሮች የበለጠ ግንዛቤ እንዲኖራቸው የሚረዳው የማህበረሰብ ስርጭት ደረጃዎችን እና አሁን ላይ ኮቪድ-19 በጤና ጥበቃ ስርዓት ላይ ያለውን ተፅዕኖ ግምት ውስጥ በማስገባት ነው። 

የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ ከካውንቲው እና ከክልሉ የማህበረሰብ ጤና ባለስልጣኖች ድጋፍ በአካባቢው የሚገኘውን መረጃ በቅርበት እየተከታተለ የማህበረሰቡን የመከላከል ስትራቴጂዎች ለማሳወቅ እና ለማሳደግ መስራቱን ቀጥሏል።   በዚህ ከፍተኛ በሆነ የአደጋ ተጋላጭነት ደረጃ ላይ በት/ቤቶቻችን እና በማህበረሰቡ የኮቪድ-19 ተፅዕኖን ለመቀነስ፣ አሁን ላይ MCPS  በጥብቅ የሚመክረው፦

  1. የኮቪድ-19 ክትባቶች እና የሚመከሩ ቡስተሮችን በየጊዜው እየተከታተሉ ማወቅ
  2. ሰዎች በሚበዙበት በቤት ውስጥ ሲሆኑ እንዲሁም የ MCPS የሰመር/ክረምት ፕሮግራሞችን ሲካፈሉ ተገቢ የሆነ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ማድረግ።
  3. ቤት መቆየት እና ምልክቶች እየባሱ መምጣታቸውን መመርመር

የኮቪድ-19 የማህበረሰብ አደጋ ተጋላጭነት ደረጃ ከፍተኛ ሲሆን የማህበረሰብ አባላት የ CDC በግለሰብ እና በቤተሰብ-ደረጃ በበሽታው የመያዝ አደጋ ተጋላጭነት ለመቀነስ የሚመክራቸውን የመከላከያ ስትራቴጂዎን እንዲመለከቱ ይበረታታሉ። ለፅኑ በሽታ ከፍተኛ ተጋላጭ የሆኑ ግለሰቦች፣ እድሜያቸው የገፋ አዋቂዎችን፣ እርጉዝ የሆኑትን ወይም ሌላ በሽታ ያለባቸው፣ እንዲሁም የኮቪድ-19 ክትባትን ያልወሰዱ ግለሰቦች የጤና ጥበቃ አገልግሎት ሰጪን ማማከር ሊፈልጉ ይችሉ ይሆናል።

የአፍና አፍንጫ መሸፈኛዎች እና የቤት-ውስጥ ምርመራዎች በሁሉም የ MCPS የሰመር ፕሮግራም ቦታዎች እና  በአካባቢው የሚገኙ ቤተ-መፅሀፍት ይገኛሉ። እድሜያቸው የደረሰ ልጆች የኮቪድ-19 ክትባትን  በት/ቤት-የሚገኙ ክሊኒኮች የተመዘገቡ መሆናቸው ግምት ውስጥ ሳይገባ ማግኘት ይችላሉ። በማህበረሰቡ ውስጥ የምርመራ እና የክሊኒክ ክትባት እድሎች  ላይ ተጨማሪ መረጃዎች በሞንትጎመሪ ካውንቲ የጤና እና የሰው አገልግሎቶች ክፍል ይገኛሉ።

በ MCPS የሰመር ፕሮግራሞች ቦታው ላይ ተገኘተው የሚሳተፉ ሰራተኞች እና ተማሪዎች በMCPS COVID-19 Reporting Form ላይ በሽታው እንዳለባቸው የሚያሳይን የምርመራ ውጤት ሪፓርት ማድረግ አለባቸው። ተመርምረው ኮቪድ ያለባቸው ሌሎች የማህበረሰብ አባላት የምርመራ ውጤታቸውን ለሜሪላንድ የጤና ክፍል የአንድ-መስኮት መተግበሪያ ላይ ሪፓርት ማድረግ አለባቸው።

የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ  Montgomery County Public Schools 



Email us: ASKMCPS@mcpsmd.org

Montgomery County Public Schools