ለተከበራችሁ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ማህበረሰብ፦
ወደ ኖቨምበር እና ቀዝቃዛ የአየር ሁኔታ ስንቃረብ፣ ስለ ጤና፣ ሃሎዊን ደህንነትን መጠበቅ እና በዚህ አመት ቀዝቃዛ አየር የኢንፍሎዌንዛ መረጃን ማካፈል እፈልጋለሁ፦
ኢንፍሉዌንዛ፣ RSV እና ሌሎች የመተንፈሻ አካላት ኢንፌክሽኖች
በሜትሮፖሊታን ክልላችን የኢንፍሉዌንዛ (ፍሉ) ሁኔታዎችን ጨምሮ የመተንፈሻ አካላት በሽታዎች መበራከታቸውን በትኩረት እየተከታተልን ነው። በዚህ ሳምንት፣ የቨርጂኒያ ጤና ጥበቃ መምሪያ በከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ውስጥ ከፍተኛ የጉንፋን ወረርሽኝ ከተከሰተ በኋላ (የብሔራዊ ትኩረትን ጭምር የሳበ) ነዋሪዎች ለተጨማሪ የመተንፈሻ አካላት ህመሞች እንዲዘጋጁ አሳስቧል። የመተንፈሻ አካላት ሲሳይያል ቫይረስ "Syncytial Virus (RSV)" ሌላው በከፍተኛ ደረጃ እየጨመረ የሚሄድ ኢንፌክሽን ሲሆን የታማሚዎች ቁጥር መጨመር የህፃናት ሆስፒታሎችን አቅም እየጠበበ ነው። ሁለቱም ኢንፍሉዌንዛ እና አርኤስቪ በአብዛኛዎቹ ሰዎች ላይ ቀላል የአተነፋፈስ ችግር ምልክቶችን የሚያስከትሉ ቫይረሶች ናቸው፥ ነገር ግን በጣም ትንንሽ ልጆች፣ ትልልቅ ሰዎች ወይም አንዳንድ የጤና እክሎች ላለባቸው ሰዎች አደገኛ ሊሆኑ ይችላሉ።
የጀርሞችን ስርጭት ለመከላከል መሰረታዊ የጤና ንፅህና አጠባበቅ ልምዶችን መተግበር/እርምጃ መውሰድ፣ሲታመሙ ቤት መቆየት፣ ሳል እና ማስነጠስ ሲኖር መሸፈን እና እጅን በደንብ መታጠብ ከመቼውም ጊዜ ይበልጥ አስፈላጊ ነው። እነዚህን እርምጃዎች መውሰድ ከኮቪድ-19 በተጨማሪ ጉንፋን፣ RSV እና ሌሎች የመተንፈሻ አካላት በሽታዎችን ለመከላከል ይረዳሉ የፍሉ ክትባቱ በጉንፋን የመያዝ እድልን እና የጉንፋንን ኢንፌክሽን ይቀንሳል። ከ 6 ወር እድሜ በላይ ለሆነ ማንኛውም ሰው ነጻ ነው፣ እና በተለይ የጉንፋን ችግሮች ተጋላጭ ለሆኑ ሰዎች አስፈላጊ ነው።
በአሁኑ ጊዜ RSV መከላከያ የሚሆን ክትባት የለም። ለከባድ በሽታ የተጋለጡ (በጣም ያለጊዜው የተወለዱ ሕፃናት ወይም የልብ ወይም የሳንባ በሽታ ላለባቸው) ለተወሰኑ ሕፃናት መከላከያ መድኃኒት አለ። RSV ኢንፌክሽን ተጋላጭ የሆኑ ሰዎችእና የቤተሰብ አባሎቻቸው በተለይ የመተንፈሻ አካላት ኢንፌክሽንን ለመከላከል ጥንቃቄ ማድረግ አለባቸው። የመተንፈሻ አካላት ምልክቶች ካጋጠማቸው የጤና እንክብካቤ ባለሙያን ምክር ይጠይቁ።
ተጨማሪ ሪሶርሶች ከአሜሪካ የሕፃናት ሕክምና አካዳሚ/American Academy of Pediatrics:፦
RSV፡ ከጉንፋን በላይ በሚሆንበት ጊዜ/RSV: When It’s More than Just a Cold
ኢንፍሉዌንዛ/ፍሉ - ወላጆች ማወቅ ያለባቸው ነገር/The Flu - What Parents Need to Know
በሃሎዊን ጊዜ ደህንነትን መጠበቅ
ሃሎዊን ከቤት ውጭ ከጓደኞች እና ጎረቤቶች ጋር ለመሆንና ጊዜ ለማሳለፍ ጥሩ ጊዜ ሊሆን ይችላል። ይሁን እንጂ ጉዳት ለማድረስም በጣም አደገኛ ጊዜ ነው። በሃሎዊን ተግባራት ላይ ባትሳተፉም እንኳን፣ የአካባቢያችንን ደህንነት ለመጠበቅ እርምጃ መውሰድ ትችላለህ፦
MCPS ከማህበረሰብ ጤና ጥበቃ አጋሮቻችን ጋር የጤና አዝማሚያዎችን መከታተል እና ለህብረተሰቡ ስለ ጤና አጠባበቅ የማሳወቅ ተግባሩን ይቀጥላል። ለተማሪዎቻችን እና ለሰራተኞቻችን ጤንነት እና ደህንነት ላሳዩት ቁርጠኝነት እናመሰግናለን።
ከልብ
Patricia Kapunan, M.D., M.P.H.
MCPS Medical Officer
Email us: ASKMCPS@mcpsmd.org