ለሐሙስ ኖቨምበር 3 ማወቅ ያለብን ስድስት ጉዳዮች

የሐሙስ ኖቨምበር 3 መታወቅ ያለባቸው ስድስት ጉዳዮችን እነሆ! መጪዎቹ ስለ በጀት ውይይት መድረኮች መረጃ፣ የስምንተኛ ክፍል ተማሪዎች ለሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ፕሮግራሞች እንዴት ማመልከት እንደሚችሉ፣ ስለ 2023-2024 የትምህርት ዘመን አቆጣጠር እንዴት አስተያየት መስጠት እንደሚችሉ፣ በዚህ ሳምንት መጨረሻ STEAM አውደ ርእይ፣ በሚቀጥለው ትምህርት በማይኖርበት ቀን ልጅዎ ማድረግ ያለበ(ባ)ት ነገር፣ “The Washington Commanders Charitable Foundation” ከዋሽንግተን ኮማንደርስ የበጎ አድራጎት ድርጅት የሚያስገርም ልግስና እና ማሳሰቢያዎች ናቸው።

 1. October is National Principals Month!

  1. 2023–2024 የትምህርት ቤት የቀን መቁጠሪያ ላይ የእርስዎን ሃሳብ/አስተያየት ይስጡ

  እባኮትን ስለቀጣዩ አመት የትምህርት ቤት የቀን መቁጠሪያ ሃሳብዎን ያካፍሉን። ይህ ፈጣን የዳሰሳ ጥናት ለ 2023-2024 የትምህርት ዘመን በተዘጋጁ የቀን መቁጠሪያ ሁኔታዎች ላይ የማህበረሰቡን አስተያየት ለማወቅ ይረዳል። ማክሰኞ ዲሰምበር 6 በሚካሄደው የትምህርት ቦርድ ስብሰባ ላይ የእርስዎ ድምፅ እንዲሰማ ከእርስዎ የተገኘውን ግብረመልስ ሠራተኞች የመጨረሻ ምክረሃሳብ/recommendation ላይ በማካተት ጥቅም ላይ የሚውል ስለሆነ እስከ ሰኞ፥ ኖቨምበር 30 ሃሳብ አስተያየትዎን ያቅርቡ።
  የዳሰሳ ጥናቱን ይድረሱ..

 2. first day

  2. የሪጅን/የካውንቲ አቀፍ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ፕሮግራሞች ማመልከቻዎች የሚቀርቡበት ጊዜ እስከ አርብ፥ ኖቨምበር 11 ተራዝሟል።

  በብዙ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለሚሰጡ የስፔሻል ፕሮግራሞች ፍላጎት ያላቸው የስምንተኛ ክፍል ተማሪዎች እስከ አርብ፥ ኖቨምበር 11 ድረስ ማመልከት አለባቸው። እነዚህ ፕሮግራሞች የሚጀምሩት 9ኛ ክፍል ነው፣ ነገር ግን ተማሪዎች አሁን ማመልከት አለባቸው። ተማሪዎች ሁሉንም አማራጮች StudentVUE ውስጥ ማየት ይችላሉ። ማመልከቻዎች ParentVUE በኩል ከቀነገደቡ በፊት መቅረብ አለባቸው።ጥያቄ ካለዎት የመካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ካውንስለርዎን ያነጋግሩ።

 3. first day

  3. “Kids Day Out” ለአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ትምህርት ቤት በማይኖርበት ጊዜ ቦታ ይሰጣል

  ሰኞ፥ ኖቨምበር 7 ትምህርት ቤት በማይኖርበት ጊዜ ለልጅዎ አንድ ነገር ከፈለጉ የሞንትጎመሪ ካውንቲ የመዝናኛ ዲፓርትመንት "Montgomery County Recreation Department" በተለያዩ የመዝናኛ ስፍራዎች ቁጥጥር በሚደረግባቸው ቦታዎች አስደሳች ጊዜ እንዲያሳልፉ ይፈቅዳል። ለመመዝገብ activemontgomery.org ይመልከቱ። የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ቤተሰቦች ሙሉ የነፃ ትምህርት ዕድል ለማግኘት MCPSkid2022 የኩፖን ኮድ ማመልከት ይችላሉ።  የወደፊት “Kids Day Out” ዝግጅቶች ለጃንዋሪ 27፥ ማርች 31፥ እና ኤፕሪል 21 ታቅደዋል።

 4. 4. የስራ ማስኬጃ በጀት የማህበረሰብ ውይይት መድረኮች ተጀምረዋል።

  MCPS ኖቨምበር 12 ከሶስቱ የማህበረሰብ የበጀት ውይይት መድረኮች የመጀመሪያውን ያስተናግዳል። ስብሰባው በ Mid-County Regional Services Center, 2425 Reedie Drive, 2nd Floor, Wheaton, MD 20902 ከ 11 a.m.–12:30 p.m በአካል ይካሄዳል። የሚቀጥለው የመድረክ መድረክ፡ ሰኞ፥ ኖቨምበር 28 (6፡30 - 8 p.m.) ቨርቹወል ይካሄዳል።

 5. first day

  5. ተማሪዎች የሳይንስ፣ የቴክኖሎጂ፣ የምህንድስና፣ የስነ ጥበብ እና የሂሳብ ስራዎችን ለማሳየት

  STEAM ፌስቲቫል አውደርዕይ ቅዳሜ፣ ኖቨምበር 5 ከቀኑ 10 a.m. to 1 p.m. በኖርዝዉድ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት (Northwood High School) ይካሄዳል። MCPS እና የትምህርት አጋሮች STEAM እድሎችን (ሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ፣ ምህንድስና፣ ስነጥበብ እና ሂሳብ) በተግባራዊ እንቅስቃሴዎች እና ማሳያዎች ያቀርባሉ። ዝግጅቱ ነፃ እና ለሁሉም የ MCPS ቤተሰቦች እና ተማሪዎች ክፍት ነው። አድራሻ፦ Northwood is located at 919 University Blvd., West in Silver Spring

 6. 6. የዚህ ሳምንት ማሳሰቢያዎች፦

  • ሰኞ፥ ኖቨምበር 7 እና ማክሰኞ፥ ኖቨምበር 8 ለተማሪዎች ትምህርት ቤት የለም።
  • የቀን ብርሃን ቁጠባ ጊዜ እሁድ፣ ኖቨምበር 6 የሚያበቃ ስለሆነ ሰዓትዎን አንድ ሰዓት ወደኋላ መመለስ እንዳይርሱ።
  • የዊንተር 2022 መለስተኛ ደረጃ ት/ቤት አትሌቲክስ የኦንላይን የሴቶች እና የወንዶች የቅርጫት ኳስ ምዝገባ አሁን ParentVUE Portal ላይ በቀጥታ ማመልከት ይችላሉ። ስለ ማሪዎች ምዝገባ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት MCPS Tech Shorts ይመልከቱ።
 7. የነፃ (ኮምፕሊመንተሪ) የፉትቦል ትኬቶች! "Washington Commanders Charitable Foundation" የዋሽንግተን ኮማንደርስ በጎ አድራጎት ፋውንዴሽን ከ "MCPS Educational Foundation, Inc." ጋር በመተባበር ዋሽንግተን ኮማንደርስ ከሚኒሶታ ቫይኪንጎች (The Washington Commanders against the Minnesota Vikings) ጋር በዚህ እሑድ፥ ኖቨምበር 6 በ 1 p.m. FedEx ሜዳ ላይ ለሚደረገው የግጥሚያ ጨዋታ 1,000 የነፃ ትኬቶችን ለሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ተማሪዎች እና ለቤተሰቦቻቸው ይሰጣል። ቲኬቶቹ መጀመሪያ ለመጡት እንደየአመጣጣቸው ቅድሚያ ይሰጣቸዋል "first come, first served"። ትኬቶችን እዚህ ያግኙ።.

 8. ተከታታይ ማሳሰቢያዎች፦

  • • ከባድ የአየር ሁኔታ በሚከሰትበት ወቅት ከ MCPS ጋር ግንኙነት ይኑርዎት
   ከባድ/መጥፎ የአየር ሁኔታ በሚኖርበት ጊዜ MCPS ስለ ተማሪዎ ትምህርት ቤት መዘጋት፣ ስለ ት/ቤት ዘግይቶ መከፈት እና ተማሪዎች ከመደበኛው ሠዓት ቀደም ብለው ስለሚሰናበቱበት ሁኔታዎች ለማሳወቅ ብዙ መንገዶችን ይጠቀማል። ስለ አየር ሁኔታ ውሳኔዎች እና ከ MCPS ጋር እንዴት መገናኘት እንደሚችሉ Stay Connected የአደጋ ጊዜ መረጃን እንዴት እንደሚቀበሉ ለማወቅ እዚህ የበለጠ ይረዳሉ።

የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ
Montgomery County Public SchoolsEmail us: ASKMCPS@mcpsmd.org

Montgomery County Public Schools