1. 2023-2024 ለሞንትጎመሪ ቨርቹዋል አካዳሚ ለማመልከት አሁን ክፍት ነው
የሞንትጎመሪ ቨርቹዋል አካዳሚ (MVA) 2023–2024 የትምህርት ዓመት ማመልከቻ ከአሁን እስከ ፌብሩዋሪ 2 ድረስ ክፍት ነው። MVA ከመዋእለ ህጻናት እስከ 12ኛ ክፍል ላሉ ተማሪዎች የሙሉ ጊዜ ቨርቹዋል ትምህርት ፕሮግራም ነው። ትኩረቱ ደህንነቱ የተጠበቀ፣ አካታች የኦንላይን ትምህርትን ማሳደግ ሲሆን ሰራተኞች የተማሪዎችን ግላዊ ፍላጎቶች የሚያሟላ የትምህርት ሁኔታን ለመለየት እና ፍላጎታቸውን የሚያውቁበት እንዲሁም የላቀ ትምህርት ሲቀስሙ የማየት እድል የሚሰጥ ነው። እንደሌሎች የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) አማራጭ ፕሮግራሞች ተማሪዎች "ParentVue" በመጠቀም ማመልከት ይችላሉ።
2. የስፕሪንግ ወቅት እና የመጀመሪያ ሴሚስተር የተማሪ አገልግሎት ትምህርት (SSL) ሰዓቶች አርብ፣ ጃኑወሪ 6 ይጠናቀቃል።
በሠመር ወቅት እና በመጀመሪያ ሴሚስተር የተማሪ አገልግሎት ትምህርት (SSL) ሰዓቶችን ያጠናቀቁ ተማሪዎች ቅጾቹን እስከ አርብ ጃንዋሪ 6 ለት/ቤታቸው SSL አስተባባሪ እንዲያቀርቡ ይበረታታሉ። ተማሪዎች ለመመረቅ 75 የ SSL ሰዓቶች ማግኘት አለባቸው።ተማሪዎች በአካል ተገኝተው የተለያዩ መደበኛ እና ቨርቹወል/የርቀት ትምህርት እድሎችን MCPS SSL ድረ-ገጽ ላይ ማግኘት ይችላሉ።
3. ማሳሰቢያ፡ የሳምንት መጨረሻ የክትባት ክሊኒኮች ክፍት ናቸው።
ወደ አዲሱ አመት ሲገቡ፣ ነጻ የኮቪድ-19 ቡስተር ክትባት ዕድሜያቸው 6 ወር እና ከዚያ በላይ ለሆኑ ግለሰቦች በትምህርት ቤት ክሊኒኮች ላይ ቅዳሜና እሁድ ይሰጣል።የቢቫለንት/bivalent ቡስተሮች ተላላፊ በሽታን ለመከላከል በጣም የተሻሉ ተደርገው የተነደፉ ናቸው።
4. ትኩረት የሳበ ተማሪ
5. MCPS በዘገባዎች ላይ
አራት የ MCPS አሰልጣኞች ዘ ዋሽንግተን ፖስት/The Washington Post—ላይ Peg Keiller፣በኩዊንስ ኦርቻርድ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት (Quince Orchard High School) የልጃገረዶች እግር ኳስ 2022 ምርጥ አሰልጣኞች ተብለዋል። ኬሊ ሬድመንድ/Kellie Redmond በቶማስ ኤስ. ውተን ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት/Thomas S. Wootton High School የልጃገረዶች አገር አቋራጭ አሰልጣኝ ፣ ፕራሳድ ጄራርድPrasad Gerard፣ የፑልስቪል ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የወንዶች ሀገር አቋራጭ አሰልጣኝ ፣ እና ማይክል ሀንሲከር-ብሌር/Michelle Hunsicker-Blair፣በፑልስቪል ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የሴት ልጆች ጎልፍ አሰልጣኝ ናቸው።
For the latest news and information, visit: MCPS News Center.
Montgomery County Public Schools
Email us: ASKMCPS@mcpsmd.org