አምስት መታወቅ ያለባቸው ነገሮች

MCPS Things to Know

ሐሙስ፣ ፌብ. 2


1. MCPS Stronger Student / ጠንካራ የተማሪ አዕምሮ ጤና እና የደህንነት መተግበሪያ አሁን ይገኛል

ነፃ የሆነው የ MCPS Stronger Student ሞባይል መተግበሪያ አሁን በአፕል (Apple) እና ጎግል ፕሌይ (Google Play) መደብሮች ይገኛል። ፕሮጀክቱን የመሩት ተማሪዎች ናቸው፣ ይዘቱን በመቅረፅ፣ በመገንባት እና በመምረጥ። መተግበሪያው የመድልዎ ክስተቶችን ሪፖርት ማድረግን ጨምሮ የችግር ድጋፍ ምንጮችን እና ሌሎች የአዕምሮ እና የአካል ጤና እና ደህንነት ፍላጎቶችን ያቀርባል። ማንነት የማይገልፅ እና ሚስጥራዊ ነው። ተጨማሪ መረጃ


Free SAT Prep for High School Students Available Now

2. የሰመር ራይዝ / Summer Rise 2023 ምዝገባ ለተማሪዎች እና ለአዘጋጆች ክፍት ነው

የSummer RISE 2023 አካል የመሆን እድልን ለማግኘት ዛሬውኑ ይመዝገቡ። Summer RISE ለመጀመሪያ አመት እና ለመጨረሻ አመት ተማሪዎች ተግባራዊ፣ በሙያ ላይ የተመሰረቱ የትምህርት ልምዶችን ይሰጣል እና አሰሪዎች የተሰጥኦ ማግኛ መስመር እንዲያዳብሩ ይረዳል። ፕሮግራሙ ለአምስት ሳምንታት ይካሄዳል፣ ከጁን 26-ጁላይ 28። የተማሪዎች ምዝገባ እዚህ ይገኛል። በተጨማሪም ምዝገባ ክፍት የሆነው ለሞንትጎመሪ ካውንቲ ንግድ ስራዎች፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች እና በጎ አድራጎት ድርጅቶች ለፕሮግራሙ እንደ አዘጋጅ ሆነው እንዲሳተፉ ነው። የአዘጋጅ ምዝገባ የሚዘጋው አርብ፣ አፕሪል 14 ነው።


Kids Day Out Set for Jan. 27

3. የጥቁር ታሪክ ወር፦ “እምቢተኛዋ አብዮተኛ፣ ዶ/ር ቤቲ ሆልስተን ስሚዝ (Betty Holston Smith)” በMCPS ተማሪ ጋዜጠኞች

በዚህ የጥቁር ታሪክ ወር፣ የተማሪ ጋዜጠኞች ቤኔት ጋልፐር (Bennett Galper)፣ ጋቤ ገብረክርስቶስ (Gabe Gebrekristose) እና ካትሪን ጆንስ (Katherine Jones) ከ Bethesda Chevy-Chase 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ለዶ/ር ቤቲ ሆልስተን ስሚዝ ለተማሪው መጽሔት The Amplifier ተራኪ ዘገባ ቃለ መጠይቅ አድርገዋታል። 
“ጁን 1956 ላይ፣ የቤቲ ሆልስተን አባት ወደ ሮክስቪል ውስጥ ወደ የሚገኘው ካርቨር (Carver)፣ “የጥቁሮች” / “colored” 2ተኛ ደረጃ ት/ቤት እንደማትመለስ ነግሯታል። ከዚህ ይልቅ በ B-CC ትማራለች፣ ይሄም ከቤቷ አንድ ማይል ርቀት ላይ የሚገኝ 2ተኛ ደረጃ ት/ቤት ነው። መጀመሪያ ላይ፣ ቤቲ ይሄ ሀሳብ አስጠልቷት ነበር። በመጀመሪያው አመት መጨረሻ ላይ፣ ማንም (እና ማንም ማለታችን ነው) እዛ ቦታ መሆን እንደማይገባት እሷን ማሳመን አይችልም ነበር። ፅሁፉን ያንብቡ።  የዚህን ወር እትም ነጻ ቅጂ ይዘዙ።


Community Conversations on the MCPS Antiracist System Audit

4. ፌብሩዋሪ ሀገር አቀፍ የሙያ ቴክኒካል ትምህርት ወር ነው።

የሙያ እና ቴክኒካል ትምህርት (CTE) ፕሮግራሞች ጠንካራ ትምህርቶችን ከቴክኒካል ክህሎቶች እና ከነባራዊው አለም ተሞክሮዎች ጋር በማጣመር ለተማሪዎች ለኮሌጅ እና ለስራ ስኬት ተወዳዳሪ የሚያደርግ ጥቅም ይሰጣሉ። ፌብሩዋሪ የ CTE ወር ነው፣ የእነዚህን ፕሮግራሞች ዕሴት ለማስተዋወቅ ሀገራዊ የህዝብ ግንዛቤ መፍጠሪያ ዘመቻ። MCPS በ12 የስራ ስብስቦች ውስጥ 51 የሙያ ዝግጁነት ፕሮግራሞች አሉት። እነዚህ የፈጠራ ፕሮግራሞች ከተለዋዋጭ ኢኮኖሚ ጋር የሚጣጣሙ እና የድህረ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት እና ስልጠናን በማጣመር ተማሪዎችን እየተለወጠ ለሚገኝ የሰው ሃይል አቅርቦት በማዘጋጀት ረገድ ወሳኝ ሚና ይጫወታሉ። የማስታወቂያ ቪድዮ ይመልከቱ።


Students and Staff Spotlight This Week

5. ለእኛ ታላላቅ ተማሪዎች እና ሰራተኞች ትኩረት መስጠት

በ2022 ሰባ አስተማሪዎች የብሔራዊ ቦርድ ማረጋገጫ ሰርተፍኬትን አሳኩ

በ2022 ሰባ MCPS አስተማሪዎች የብሔራዊ ቦርድ ማረጋገጫቸውን ሰርተፍኬትን በማሳካት አግኝተዋል። ሌላ 90 ሰዎች ደግሞ ሰርተፍኬታቸውን በተሳካ ሁኔታ አስጠብቀዋል። የብሔራዊ የቦርድ ሰርተፍኬት የሚከናወነው በብቃት የተካኑ መምህራን ማወቅና መሥራት የሚችሉትን ለመለካት በተዘጋጀ የግምገማ ሂደት ነው። በዚህ ሳምንት ሰራተኞች ውስጥ ተጨማሪ የምስራች ያንብቡ ማስታወቂያ/ Bulletin ።

የተማሪ-አትሌቶች የብሔራዊ ልጃገረዶችን እና ሴቶችን በስፖርት ቀን አድምቀዋል

ብሄራዊ ልጃገረዶችን እና ሴቶችን በስፖርት ቀን የሚያከብረው በተማሪ-አትሌቶች አመራር ምክር ቤት የተዘጋጀ PSA ይመልከቱ። ይህ ቀን ለሴት አትሌቶች፣ ለውጤቶቻቸው፣ ሴቶች በስፖርት ውስጥ በመካተት ያስመዘገቡትን አወንታዊ ተፅእኖ እና ለሴቶች እና ለሴቶች ፍትሃዊ የስፖርት ተደራሽነት እንዲኖር ለሰሩ ሁሉ እውቅና ይሰጣል።


ወቅታዊ መረጃዎችን እና ዘገባዎችን ለማግኘት MCPS News Center ይጎብኙ።


Montgomery County Public Schools



Email us: ASKMCPS@mcpsmd.org

Montgomery County Public Schools