አምስት መታወቅ ያለባቸው ነገሮች

MCPS Things to Know

ሐሙስ፣ ፌብ. 9


1. የትምህርት ቦርድ የ 2024 በጀት አመት የስራ ማስኬጃ በጀት የስራ መርሀ ግብርን አጠናቋል

ዛሬ፣ ሀሙስ ፌብሩዋሪ 9፣ የትምህርት ቦርድ የመጨረሻውን የስራ ማስኬጃ በጀት ስራ መርሀ ግብር ከ MCPS አስተዳደር ጋር አካሂዷል። የታቀደው በጀት ማንበብና መፃፍ እና ሂሳብን ለማሻሻል፣ የተለያዩ እና ከፍተኛ ጥራት ያላቸውን ሰራተኞች ለመቅጠር እና በስራቸው ለማቆየት፣ እና ትምህርት ቤቶችን ደህንነታቸው የተጠበቀ እና የሚጋብዙ/የሚስቡ እንዲሆኑ ለማድረግ ነው የተዘጋጀው። በበጀቱ ላይ ቁልፍ ማስተካከያዎች የሚያካትቱትም፦

  • የተማሪ መማርን እና የአስተማሪ ውጤታማነትን ለመደገፍ በማንበብና መፃፍ እና በሂሳብ ላይ ባለሙያ የሆኑ የሰራተኛ አባላትን መጨመር
  • ለአዲስ መምህራን እና አማካሪዎች ድጋፎች
  • አላማ ያደረገ የሙያ እድገት
  • የድህንነት ሰራተኞችን መጨመር

በቀጣይ፣ ቦርዱ በጊዜያዊነት የቀረበውን በጀት ለማፅደቅ እና ለመቀበል ድምፅ ይሰጣል፣ እና ወደ የካውንቲ ስራ አስፈፃሚ/ካውንቲ ምክር ቤት. ይልካል። ከኤፕሪል ጀምሮ በካውንቲ የህዝብ ችሎቶች ላይ መገኘት ይችላሉ።


Free SAT Prep for High School Students Available Now

2. ቀጣይ የቤተሰብ ፎረም በፌንታኒል (Fantanyl) እና ህይወት አዳኝ ናርካን (Narcan) ስልጠና ላይ ለፌብሩዋሪ 25 ተዘጋጅቷል

ከMontgomery Goes Purple ጋር በመተባበር፣ MCPS ቅዳሜ ፌብሩዋሪ 25 ላይ ቤተሰቦችን በፌንታኒል (Fantanyl) ላይ ለሚደረገው ዝግጅት እና ውይይት እንዲመጡ ይጋብዛል። ተወያዮች በህገ-ወጥ መንገድ የተሰራውን የፋንታኒል (Fantanyl) አደጋ እና ስርጭት፣ የመከላከያ መሳሪያዎች እና ለተማሪዎች የመከላከያ ሁኔታዎች፣ እና አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ለህክምና ግብአቶች ጠቃሚ መረጃን ያካፍላሉ። ዝግጅቱ ጠዋት ከ9፡30 am እስከ 11፡30 am በኖርዝዉድ (Northwood) ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አዳራሽ፣ 919 University Blvd W. በ Silver Spring ይካሄዳል። ለተማሪዎች እና ለወላጆች/ተንከባካቢዎች እና ተማሪዎች ልዩ ልዩ ውይይቶች፣ የሀብት/ግብዓት አውደ ርዕይ፣ የኮቪድ-19 ክትባቶች እና መዝናኛዎች ይኖራሉ።


Kids Day Out Set for Jan. 27

3. "የዓመቱ መምህር" ለተሰኘ ውድድር ሶስት የመጨረሻ እጩዎች ተሠይመዋል

ሦስት አስተማሪዎች የ2023-2024 የ MCPS የአመቱ ምርጥ መምህር የመጨረሻ ዙር እጩዎች ተብለዋል። እነሱም፡- ሜጋን አንደርሰን (Megan Anderson)፣ በ ቼቪ ቼስ (Chevy Chase) አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የአምስተኛ ክፍል አስተማሪ፤ ኢዩንጁ (ኤፕሪል) ሙን (Eunju (April) Moon)፣ በሪጅቪው (Ridgeview) መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የስድስተኛ ክፍል የእንግሊዝኛ አስተማሪ፤ እና ሻነን ማኬንዚ (Shannon McKenzie) በ ክላርክስበርግ (Clarksburg) ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የልጅ እድገት አስተማሪ ናቸው። አሸናፊው/ዋ በመቀጠል ለሜሪላንድ የዓመቱ ምርጥ መምህር ሽልማት ለመወዳደር ያልፋል/ታልፋለች።

ስለ የመጨረሻ ዙር እጩዎች ተጨማሪ አንብቡ


Community Conversations on the MCPS Antiracist System Audit

4. የጥቁር ታሪክ ወር የMCPS ታሪኮች፦ ሃዋርድ ቤል (Howard Bell)፣ የካርቨር (Carver) ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የቀድሞ ተመራቂ፣ 1956 - 1959

በሴፕቴምበር 1951፣ የጆርጅ ዋሽንግተን ካርቨር (George Washington Carver) ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በሞንትጎመሪ ካውንቲ ውስጥ ለጥቁር ተማሪዎች የተሰራ ብቸኛው የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ተቋም ሆኗል። አሁን ላይ ሕንፃው በሮክቪል (Rockville) ውስጥ እንደ የMCPS ማዕከላዊ ቢሮ ሆኖ ያገለግላል። ከካርቨር (Carver) ተመራቂ ሃዋርድ ቤል (Howard Bell) ጋር ጥቁርና ነጭን በመለየት እና በኋላ ውህደት ወቅት ወደ ትምህርት ቤት የመሄድ ልምድ እና እንደ ካውንቲ ምን ያህል እንደደረስን በሚመለከት ቃለ መጠይቅ አድርገናል።

ቃለ መጠየቁን ይመልከቱ


5. ለእኛ ታላላቅ ተማሪዎች እና ሰራተኞች ትኩረት መስጠት

Students and Staff Spotlight This Week
የኪንግስቪው (Kingsview) መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት አማካሪ ኬቲ ሜንዴልሰን (Katie Mendelson) የሜሪላንድ ስቴት መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የአመቱ ምርጥ አማካሪ ተብላ ተመርጣለች። በፌብሩዋሪ 6 በብሔራዊ ትምህርት ቤት አማካሪ ሳምንት የመጀመሪያ ቀን ላይ በትምህርት ቤቱ ማስታወቂያ ላይ በተነገረው ዜና ተገርማለች።

Students and Staff Spotlight This Week
የፔይንት ብራንች (Paint Branch) ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ረዳት ርዕሰ መምህር ሪካርዶ ሄርናንዴዝ (Ricardo Hernandez) የሜሪላንድ ስቴት 2ኛ ደረጃ ት/ቤት የዓመቱ ረዳት ረዳት ስለተሸለሙ እንኳን ደስ አላችሁ። አሁን ደግሞ የሜሪላንድ ግዛትን በመወከል በብሔራዊ ውድድር ላይ በመቀጠል ይወዳደራል

Students and Staff Spotlight This Week
ባለፈው ሳምንት በተለያዩ ሻምፒዮናዎች ለተሳተፉ ተማሪዎቻችን እንኳን ደስ አላችሁ።

ቦክሴ (Bocce) - የካውንቲ ሻምፒዮናዎች

  • ኖርዝውድ (Northwood) - (በትምህርት ቤት ታሪክ 1ኛ!)

ፖምፖንስ (Pompons) - የካውንቲ ሻምፒዮናዎች

  • ዲቪዚዮን I - ዋልት ዊትማን (Walt Whitman)
  • ዲቪዚዮን II - ቤተፃዳ- ቼቪ ቼስ (Bethesda-Chevy Chase)
  • ዲቪዚዮን III - ክላርክስበርግ (Clarksburg)

ዋና እና ዳይቪንግ ዲቪዚዮን ሻምፒዮናዎች

  • ዲቪዚዮን I - ዋልተር ጆንሰን / Walter Johnson (በሴቶች) እና ዊንስተን ቸርችል / Winston Churchill (በወንዶች)
  • ዲቪዚዮን II - ሪቻርድ ሞንጎመሪ / Richard Montgomery (በሴቶች) እና ኩዊንስ ኦርቻርድ / Quince Orchard (በወንዶች)
  • ዲቪዚዮን III - Col. ዞዳክ ማግሩደር / Zadok Magruder (በሴቶች) እና ሮክቪል / Rockville (በወንዶች)
  • ዲቪዚዮን IV - ጄምስ ኸርበት ብሌክ / James Hubert Blake (በሴቶች) እና ኖርዝውድ / Northwood (በወንዶች)

For the latest information and news, visit the MCPS News Center.
Para Español Noticias de MCPS.


Montgomery County Public Schools



Email us: ASKMCPS@mcpsmd.org

Montgomery County Public Schools