አምስት መታወቅ ያለባቸው ነገሮች

MCPS Things to Know

ሐሙስ፣ ፌብ. 23


1. ስለ ፌንታኒል እና ህይወት አድን ናርካን ስልጠና ስለሚሰጥ በዚህ ቅዳሜ የቤተሰብ ውይይት ፎረም ላይ ለመሣተፍ ይምጡ

Montgomery Goes Purple ጋር በመተባበር የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) በሚያዘጋጀው ስለ fentanyl ጎጂነት የውይይት ዝግጅት ላይ ቅዳሜ፥ ፌብሩዋሪ 25 ቤተሰቦች እንዲገኙ ተጋዘዋል። የመድረክ ውይይት አቅራቢዎቹ በህገወጥ መንገድ የተሰራውን የፈንታኒል/fentanyl አደጋ እና ስርጭት፣የመከላከያ መሳሪያዎች እና የተማሪዎች የመከላከል ዘዴዎችን እና አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ለህክምና ግብአት የሚውሉ ጠቃሚ መረጃዎችን ያካፍላሉ። ዝግጅቱ ከ9፡30–11፡30 a.m. በኖርዝዉዉድ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አዳራሽ፣ Northwood High School auditorium, 919 University Blvd. West in Silver Sprin ይካሄዳል። ለተማሪዎች እና ለወላጆች/ለተንከባካቢዎች እና ለተማሪዎች ልዩ ልዩ የውይይት ክፍለጊዜዎች የሚኖሩ ሲሆን፣ የሪሶርስ ትርኢት፣ የኮቪድ-19 ክትባቶች እና መዝናኛዎች ይኖራሉ። የመድረክ ውይይት እና የቡድን ክፍለ ጊዜዎች በእንግሊዝኛ እና በስፓኒሽኛ ቋንቋዎች ይካሄዳሉ።

ይመዝገቡ/RSVP

ስለ ፈንታንይል ጠቃሚ ሪሶርሶች/Fentanyl Resources


Free SAT Prep for High School Students Available Now

2. ተማሪ የትምህርት ቦርድ አባልነት የመጨረሻ እጩዎች ተመርጠዋል

በሪቻርድ ሞንትጎመሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ጁኒየር ተማሪ Sami Saeed፣ እና በስፕሪንግብሩክ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ጁኒየር ተማሪ Yoseph Zerihun ለ46ተኛው ተማሪ የትምህርት ቦርድ አባልነት (SMOB) የመጨረሻ እጩ ሆነዋል። አቶ ሰኢድ እና አቶ ዘሪሁን ከ12 ተወዳዳሪዎች መካከል ከ400 በላይ ድምጽ በሰጡ የመለስተኛ እና ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተወካዮች አማካይነት ተመርጠዋል። ምርጫ የሚካሄደው ኤፕሪል 19 ነው።

ስለ እጩዎቹ የበለጠ ያንብቡ።


Kids Day Out Set for Jan. 27

3. በMCPS ውስጥ የአእምሮ ጤና መርጃዎችን እና ድጋፎችን እንዴት ማግኘት እንደሚቻል

በሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ዋናው በይነመረብ ገጽ እና በእያንዳንዱ የትምህርት ቤት ድረ-ገጽ ላይ ለተማሪዎች፣ ለሰራተኞች እና ለቤተሰቦች ጠቃሚ የሆኑ በዲስትሪክት ውስጥ አገልግሎት የሚሰጡ መረጃዎችን እና የማህበረሰብ አገልግሎት መስጫ ቦታዎችን በቀላሉ ማግኘት ይችላሉ። MCPS ከ 160,000 ለሚበልጡ ተማሪዎቹ እና ከ24,000 በላይ ለሚሆኑ ሰራተኞቹ አካላዊ፣ ማህበራዊ እና ስነልቦናዊ ጤንነትና ደህንነት ቁርጠኛ ነው።


Community Conversations on the MCPS Antiracist System Audit

4. MCPS እየቀጠረ ነው!

MCPS ለአለም ቋንቋዎች እና የመድብለ ቋንቋ/world languages and language immersion አስተማሪዎች በአካል በመገኘት የመረጃ ልውውጥ ክፍለ ጊዜ እያዘጋጀ ነው። ፕሮግራሙ ሰኞ፣ ፌብሩዋሪ 27 ቀን ከሠዓት በኋላ 5-7 p.m. በሮክቪል 15 W. Gude Drive in Rockville ይካሄዳል። MCPS በሜሪላንድ ውስጥ ትልቁ እና የተለየ የትምህርት ስርዓት የሚያካሄድ ተቋም በመሆኑ ተወዳዳሪ ማካካሻ እና ጥቅማጥቅሞችን ይሰጣል። ዲስትሪክቱ 2023-2024 የትምህርት አመት ከፍተኛ ብቃት ያላቸውን ባለሙያዎች በአስተማሪነት የስራ ግብረኃይሉን እንዲቀላቀሉ ይፈልጋል። MCPS በሚከተሉት ዘርፎች መምህራንን ለመቅጠር ይፈልጋል፦

  • የዓለም ቋንቋዎች፡ ስፓኒሽኛ፣ ፈረንሳይኛ እና ማንዳሪን/World Languages: Spanish, French and Mandarin
  • መድብለ ቋንቋ፡ ስፓኒሽኛ፣ ፈረንሳይኛ እና ማንዳሪን/Language Immersion: Spanish, French and Mandarin

ይመዝገቡ/RSVP

በዚህ ድረገጽ ላይ በማናቸውም ጊዜ ስለ ክፍት የሥራ ቦታ ማግኘት ይችላሉ፦ MCPS Careers.


5. ለምርጥ ተማሪዎች እና ሰራተኞች ትኩረት መስጠት

Community Conversations on the MCPS Antiracist System Audit

ለሜሪላንድ ትምህርት ቤት የዓመቱ ምርጥ ባለሙያነት ውድድር ሁለት የ MCPS ሚዲያ ስፔሻሊስቶች የመጨረሻ እጩዎች ሆነዋል። ከሰቨን ሎክስ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት (Seven Locks Elementary School) የሚዲያ ስፔሻሊስት ሜርዲዝ ሂክማን/Meredith Hickman እና በካቢን ጆን መለስተኛ ደረጃ ት/ቤት (Cabin John Middle School) የሚዲያ ባለሙያ የሆኑት ዶ/ር ሸሪ ማሴ/Dr. Sheri Massey በስቴት ደረጃ እውቅና ከሚሰጣቸው 14 ተወዳዳሪዎች ውስጥ የመጨረሻ እጩዎች ሁለቱ ናቸው። በዚህ ሳምንት የሰራተኞች መጽሔት ውስጥ የበለጠ ያንብቡ.

Community Conversations on the MCPS Antiracist System Audit

● ከታሪካዊ ጥቁር ኮሌጆች እና ዩኒቨርሲቲዎች (HBCU) ጋር በመቶዎች የሚቆጠሩ ተማሪዎች፣ አስተማሪዎች፣ አስተዳዳሪዎች፣ የማህበረሰብ አባላት፣ ተንከባካቢዎች እና HBCU ተወካዮች በዚህ አመት HBCU ትርኢት ላይ ተሳትፈዋል። ተማሪዎች HBCUs የሚሰጣቸውን በርካታ ጠቃሚ መረጃዎችን የማወቅ እድል አግኝተዋል። በዚህ አመት በቦታው ላይ በተካሄደ የኮሌጅ መግቢያ ሂደት ተቀባይነት ላገኙ የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ሲንየር ተማሪዎች እንኳን ደስ አላችሁ እንላለን!


For the latest information and news, visit the MCPS News Center.
Para Español Noticias de MCPS.


Montgomery County Public Schools



Email us: ASKMCPS@mcpsmd.org

Montgomery County Public Schools