አምስት መታወቅ ያለባቸው ነገሮች

MCPS Things to Know

ሀሙስ፣ ማርች 16


1. ስለ የፈንታኒል "Fentanyl" አደገኛነት ቀጣዩ የቤተሰብ ውይይት መድረክ/ ፎረም ማርች 25 ይካሄዳል።

Montgomery Goes Purple ከሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ጋር በመተባበር ስለ Fantanyl አደገኛነት ሶስተኛውን የቤተሰብ ውይይት መድረክ/ፎረም ቅዳሜ፣ ማርች 25 ቀን ከጠዋቱ 9 a.m.–noon/እስከ እኩለ ቀን ድረስ በፓይንት ብራንች ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ያስተናግዳል። ይህ የቤተሰብ ውይይት መድረክ የሚያተኩረው በደርዘን የሚቆጠሩ ጥልቅ ግንዝቤ የሚገኝባቸው ክፍለ ጊዜዎች፣ እንዲሁም ስለ ናርካን አጠቃቀም ስልጠና/Narcan training፣ የመርጃ ሰንጠረዦች እና የአካል ብቃት እድሎች ያሉበት ነው። የውይይት መድረኩ ለወጣቶች እና ለአዋቂዎች በየግል እና በጋራ በእንግሊዝኛ እና በስፓኒሽኛ ቋንቋዎች ክፍለ ጊዜዎች ይኖሩታል። የውይይት ርዕሶች የሚከተሉትን ያካትታሉ፦

  • ከልጅዎ ጋር ውይይት መጀመር
  • ከወላጅ ጋር ውይይት መጀመር
  • የአእምሮ ጤና እንክብካቤ
  • የሪሶርስ ምንጮችን መፈለግ እና ማግኘት፣ ከጓደኞች ጋር ጤናማ የግንኙነት ድንበር እና ሌሎችም ብዙ ጠቃሚ ርእሶች ይኖራሉ

አድራሻ፦ Paint Branch is located at 14121 Old Columbia Pike in Burtonsville

ይመዝገቡ/RSVP


2. Prekindergarten/Head Start Registration Now Open

ለ 2023-2024 የትምህርት ዓመት የቅድመ መዋዕለ ሕፃናት እና ሄድ ስታርት ምዝገባ አሁን ክፍት ነው። በሴፕቴምበር 1፣ 2023 ወይም ከዚያ በፊት ልጆች 4 አመት የሆናቸው መሆን አለባቸው፣ እና ቤተሰቦች ለማመልከት ከሚያገኙት ገቢ አንጻር ብቁ መሆን አለባቸው። ቤተሰቦች ልጆቻቸውን በኦንላይን ወይም በአካል ማስመዝገብ ይችላሉ። በአካል ማስመዝገብ ለሚፈልጉ ቤተሰቦች፣የማስመዝገቢያ ቦታዎች እስከ ማርች 31 ድረስ በሳምንቱ የሥራ ቀናት እና የሳምንት መጨረሻ ቀን ክፍት ናቸው። ለአሁኑ 2022-2023 የትምህርት ዓመትም ለማስመዝገብ እስካሁን ክፍት ነው።

ስለ ብቁነት መመሪያ፣ ስለ አስፈላጊ ሰነዶች እና በኦንላይን እንዴት ማስመዝገብ እንደሚችሉ የበለጠ መረጃ ለማግኘት 240-740-4530 ይደውሉ ወይም MCPS ድረ ገጽ ይመልከቱ።.

መቼ እና የት እንደሚመዘገቡ፣ 2023-2024


3. "Game Changer Mentoring Conference" ጨዋታ ቀያሪ የትምህርት ምክር አገልግሎት ኮንፈረንስ አሁን ይመዝገቡ

ይህ ነፃ የትምህርት ማማከር ኮንፈረንስ "The Universities at Shady Grove (USG)" የሚካሄድ ሲሆን ከ4ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ላሉ ጥቁር ወይም አፍሪካዊ አሜሪካዊያን እና ላቲኖ ወይም ሂስፓኒክ ወንድ ተማሪዎች ላይ ያተኮረ ነው። የወላጆች አውደጥናቶች/ወርክሾፖች 9 a.m. እና 11 a.m. ይካሄዳሉ። ተሳታፊዎች በቅድሚያ እንዲመዘገቡ ይጠየቃሉ።.

ተማሪዎች በዚህ የኮንፈረንስ ርእስ “The World is Shifting! ላይ ተመስረተው 300 ቃላት ድርሰት ጽፈው እንዲያቀርቡ እናበረታታለን። ስለ ወደፊት ትኩረት ማድረግ ጨዋታ ይቀይራል/Being Focus Forward Is a Game Changer.” የድርሰት ጽሁፉ የሚከተሉትን ጥያቄዎች መመለስ አለበት፡ እንዴት የላቀ ብቃትን ትጎናፀፋለህ/ትጎናፀፊያለሽ? ይህ በቤት ውስጥ፣ በትምህርት ቤት እና በማህበረሰብ ውስጥ ስኬታማ ለመሆን አስፈላጊ የሚሆነው ለምንድነው? በድርሰት ውድድር ላይ የሚሳተፉ ተማሪዎች ፅሑፎቻቸውን ከሐሙስ፣ ማርች 23, 2023 በፊት በዚህ ኢሜል aimhighinlife@aol.com ማቅረብ አለባቸው።

አድራሻ፦ USG is located at 9630 Gudelsky Dr. in Rockville.
ምዝገባ


4. 51 ዓመታትን (በእርግጥ 52) ያስቆጠረው የሼርዉድ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የሮክ 'ን ሮል ሪቫይቫል "Sherwood High School’s Rock ’n Roll Revival" አሁንም እንደተነቃቃ ነው

አሁን በ52ኛ ዓመቱ የሼርዉድ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ሮክ 'ን ሮል ሪቫይቫል ከ1971 ጀምሮ በኮቪድ ምክንያት 2021 ቨርቹዋል ከተደረገው በስተቀር እስካሁን ዝነኛነቱን እንደያዘ ያለማቋረጥ እየተካሄደ ሲሆን ። በዚያ ዓመት የቀጥታ ስርጭት አፈጻጸም ዕድል ስላልነበረ፣ ሮክ 'ን ሮል 50ኛ ዓመቱን በምትኩ Rock ‘n Roll 49.5 ተባለ። ታሪኩን በፎተግራፍ ይመልከቱ።.


5. በዶክመንተሪ ፊልም ውድድር የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ተማሪዎች ትልቁን ሽልማት አሸናፊዎች ሆነዋል።

ዶ/ር ማርቲን ሉተር ኪንግ ጁኒየር መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤትየስድስተኛ ክፍል ተማሪዎች የሆኑት ፓሪም ሻህ እና ኒማይ ሻርማ/Parim Shah and Nimay Sharma፣ በዚህ አመት C-SPAN 2023 StudentCam ዘጋቢ ፊልም ውድድር ትልቁን ሽልማት አሸንፈዋል። “Where’s My Data? ለተሰኘ ዶክመንተሪ ፊልማቸው $5,000 ዶላር ያገኛሉ። የግል መረጃ/ውሂብ እና የሚያሳድረው ትክክለኛ ተጽእኖ/Data Privacy and its Real World Impact” “አዲስ የኮንግረስ አባል ብትሆን(ኚ) የትኛው ጉዳይ የመጀመሪያው ስራህ(ሽ)/ትኩረትህ(ሽ) ይሆን ነበር እና ለምን?” “If you were a newly elected member of Congress, which issue would be your first priority and why?” በሚል መሪ ቃል ተማሪዎች ዘጋቢ ፊልም እንዲሰሩ ተጠይቀው ነበር። ሁለተኛ ደረጃ፣ ሶስተኛ ደረጃ እና የክብር ሽልማቶችን ላሸነፉ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ተማሪዎች በሙሉ እንኳን ደስ አላችሁ።

አሸናፊውን ዶክመንተሪ ይመልከቱ።.
የአሸናፊዎች ሙሉ ዝርዝር


For the latest information and news, visit the MCPS News Center.
Para Español Noticias de MCPS.


Montgomery County Public Schools



Email us: ASKMCPS@mcpsmd.org

Montgomery County Public Schools