አምስት መታወቅ ያለባቸው ጉዳዮች

MCPS Things to Know

ማክስኞ፣ ሜይ 18

narcan

1. MCPS ተማሪዎች ናርካን በትምህርት ቤት ናርካን መያዝ እንዲችሉ የሚፈቅደውን አዲስ መመሪያ ተግባራዊ ያደርጋል
የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) በት/ቤቶች ውስጥ ለሚከሰቱ ኦፕዮይድ ከመጠን በላይ በመውሰድ ለተጠረጠሩ ድንገተኛ አደጋዎች የሕክምና እርዳታ ለመስጠት አዲስ መመሪያ አውጥቷል።

አዲሱ ደንብ ናሎክሶን/naloxone (በብራንድ ስሙ ናርካን (Narcan) በመባልም ይታወቃል) በሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ትምህርት ቤቶች ውስጥ አጠቃቀሙን እና ተደራሽነቱን በተመለከተ ዝርዝር መመሪያን ያካትታል። ናርካን (Narcan) ኦፒዮይድ (opioid) ከመጠን በላይ መውሰድ የሚያስከትለውን ውጤት በጊዜያዊነት ፋታ የሚሰጥ ህይወትን የሚያድን መድሃኒት ነው። በአዲሱ መመሪያ መሠረት ተማሪዎች የዲሲፕሊን እርምጃ ሳይፈሩ በትምህርት ቤቶች እና በትምህርት ቤት በሚደገፉ እንቅስቃሴዎች ናርካን መያዝ/መጠቀም ያስችላቸዋል። በት/ቤት ግቢ ውስጥ እያሉ የሕክምና እርዳታ የሚያስፈልገው ድንገተኛ አደጋ ሲያጋጥም ተማሪዎች ከትምህርት ቤት ወይም ከጤና ክፍል ሰራተኞች እርዳታ መጠየቃቸውን መቀጠል አለባቸው።

ስለ ናርካን እና ስለሌሎች የትምህርት ግብአቶች በሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) የጤና እና ደህንነት አውደርእይ ቅዳሜ፣ ሜይ 20 ከጠዋቱ 9 a.m. እስከ እኩለ ቀን በሴኔካ ቫሊ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት፣ Seneca Valley High School, 19401 Crystal Rock Drive in Germantown ተገኝተው የበለጠ መማር ይችላሉ።

ይመዝገቡ/RSVP

ይበልጥ ያንብቡ

የፀረ-ዘረኝነት ኦዲት የድርጊት መርሃ ግብር አሁን ይገኛል።


audit

 

2. የፀረ-ዘረኝነት ስርዓትአቀፍ የድርጊት መርሃ ግብር ሐሙስ፣ ሜይ 11 ለትምህርት ቦርድ ቀርቧል። የዲስትሪክቱ የድርጊት መርሃ ግብር የተነደፈው የዘር እኩልነት ራዕይን በተሳካ ሁኔታ ስለመተግበር የተሰጡትን አምስት ምክረሃሳቦች በውጤታማነት ለማከናወን ነው። እነዚህ ወሳኝ ጉዳዮች ወጥነት፣ ተጠያቂነት፣ ፍትሃዊነትን ማዕከል ያደረገ የአቅም ግንባታ፣ ቀጣይነት ያለው መረጃ መሰብሰብ እና አስተማማኝ ግንኙነት ናቸው።

የድርጊት መርሃ ግብሩ በሦስት ክፍሎች የተከፋፈለ ነው

  1. የስርዓትአቀፍ-ደረጃ እርምጃዎች
  2. ጎራ-ተኮር እርምጃዎች
  3. በትምህርት ቤት ደረጃ የሚወሰዱ እርምጃዎች

 

የድርጊት መርሃ ግብሩ በጣም የተገለሉ ተማሪዎችን የሚነኩ የዋናው ጽ/ቤትን እና የትምህርት ቤቶችን ፀረ-ዘረኝነት ድርጊቶችን እና እንቅፋቶችን የሚወገዱበትን ሁኔታ ለመምራት የተዘጋጀ ነው።

የበለጠ ለማወቅ እና ሙሉውን የኦዲት ሪፖርት ለማንበብ የፀረ-ዘረኝነት ኦዲት ድረ ገጽ ይጎብኙ።

የወላጅ አካዳሚ ቨርቹዋል ወርክሾፖች "Parent Academy TO GO Virtual Workshops" አሁንም ይካሄዳሉ።


parent academy

 

3. የወላጅ አካዳሚ ቱ ጎ "Parent Academy TO GO" የተነደፈው ቤተሰቦች በልጆቻቸው ትምህርት እንደ ደጋፊ እና አጋሮች መሆናቸውን ለማሳወቅ እና ለማበረታታት ነው። ወርክሾፖች/አውደጥናቶች የልጆቻቸውን አካዴሚያዊ እና ስሜታዊ ደህንነት ለመደገፍ ጠቃሚ መረጃዎችን እና ግብዓቶችን ይሰጣሉ፥ እንዲሁም ለኮሌጅ እና ለስራ ዝግጁ እንዲሆኑ ይረዳቸዋል። ንቁ ወላጅነት፣ የኮሌጅ መግቢያ ሂደትን መረዳት፣ ራስን መንከባከብ እና ሌሎችንም ትምህርት ሰጪ የሆኑ አውደጥናቶች እስከ ጁን 6 ድረስ ይካሄዳሉ። ጥያቄ ከቀረበ የቋንቋ ማስተርጎም አገልግሎት ሊኖር ይችላል።
ምዝገባ


dual enrollment

 

4. የሚፈለጉ SSL ቅጾችን ለማቅረብ የመጨረሻ ቀን አርብ፥ ጁን 2 ነው።

የተማሪ አገልግሎት ትምህርት (SSL) ቅጾችን ለማቅረብ የመጨረሻው ቀን አርብ፣ ጁን 2 ነው። ከጁን 1, 2022 በኋላ የተጠናቀቁ SSL አገልግሎት ሰአታት ለዚህ የትምህርት አመት እንዲያዝላቸው ለመካከለኛ ደረጃ ወይም ለሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት SSL አስተባባሪዎች እስከ ጁን 2, 2023 ድረስ መቅረብ አለባቸው።

እባክዎ ያስታውሱ ሁሉም የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ተማሪዎች ከሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ለመመረቅ 75 SSL ሰዓቶች ማግኘት አለባቸው። የሠመር ዕረፍት ለተማሪዎች SSL እድሎችን በማግኘት የሚሳተፉበት ግሩም ጊዜ ነው።5. የዚህ ሳምንት ጉልህ ክንዋኔዎች


ተማሪዎች በጣምራ/ድርብ-ምዝገባ ሥነ ሥርዓት ላይ አክብሮት ተሠጥቷቸዋል
በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ላይ በሼዲ ግሮቭ ዩኒቨርሲቲዎች በተካሄደው የጥምር ምዝገባ እውቅና ስነ ስርዓት ላይ ከ200 በላይ ተማሪዎች ተሸልመዋል። እነዚህ ተማሪዎች በሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) እና በሞንትጎመሪ ኮሌጅ በጣምራ ተመዝግበው ሲማሩ የቆዩ ናቸው። አብዛኛዎቹ ተማሪዎች ከሞንትጎመሪ ኮሌጅ አሶሽዬት ዲግሪ ያገኛሉ። እውቅና የተሰጣቸው ተማሪዎችን ዝርዝር ይመልከቱ።

spelling bee

የሰቨን ሎክስ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት/Seven Locks Elementary School ተማሪ የኖርዝኢስት ሪጅን "History BEE" ሻምፒዮን ስያሜ ተሰጥቷታል።

የአምስተኛ ክፍል ተማሪ አቫ ጌርሰን/Ava Gerson የ 2023 "Who Was?" History Bee የኖርዝኢስት ሪጅን ሻምፒዮን።

በጃኑዋሪ ወር ከሰቨን ሎክስ አንደኛ ደረጃ ት/ቤት (Seven Locks Elementary School) ከ 200 በላይ የሦስተኛ፣ አራተኛ እና አምስተኛ ክፍል ተማሪዎች ከ "Penguin Press’ "Who Was?" ስለ ሰዎች እና የተለያዩ ክስተቶች በቀረበላቸው የመጀመሪያ ዙር የምርጫ ጥያቄዎች ላይ ተወዳድረዋል። ተከታታይ ታሪክ። ከዚያም በእያንዳንዱ ክፍል ውስጥ ከፍተኛ ነጥብ ያገኙ ሁለት ሁለት ተማሪዎች በመደበኛ " bee assembly" ስብሰባ ላይ ተወዳድረዋል። አቫ/Ava 17 ተማሪዎችን በማሸነፍ ወደ ተናጠል የድርሰት ውድድር ተሸጋግራለች። ስራዋ ለኖርዝኢስት ሪጅን በአሸናፊነት ተመርጧል።Email us: ASKMCPS@mcpsmd.org

Montgomery County Public Schools