1. የትምህርት ቦርድ ለ2024 የበጀት ዓመት 3.165 ቢሊዮን ዶላር የሥራ ማስኬጃ በጀት አፀደቀ
የሞንትጎመሪ ካውንቲ የትምህርት ቦርድ ለ 2024 የበጀት ዓመት $3.165 ቢሊዮን የሥራ ማስኬጃ በጀትን በአንድ ድምፅ አፅድቋል፣ ይህም ካለፈው ዓመት $245 ሚሊዮን ዶላር ወይም 8.4 በመቶ ጭማሪ አለው። የጸደቀው በጀት MCPS የተማሪዎች ምዝገባ እድገትን እና የተማሪ አካዳሚያዊ ፍላጎቶችን ለመደገፍ ኢንቨስት እንዲያደርግ ያስችለዋል፣ ለሰራተኞች የደሞዝ ጭማሪ በመስጠት ከፍተኛ ብቃት ያላቸውን መምህራንን፣ አስተዳዳሪዎችን እና የድጋፍ አገልግሎት ሰራተኞችን በብቃት ለመቅጠር እና ለማቆየት ያስችላል።
2. ለዓመታዊው ወደ ትምህርት ቤት የመመለስ ትርዒት የቀን መቁጠሪያዎን ምልክት ያድርጉ
MCPS ዓመታዊውን ወደ ትምህርት ቤት የመመለስ ትርዒት ቅዳሜ፣ ኦገስት 26 ከ10፡00 a.m. እስከ 1 p.m. በዊተን ዌስትፊልድ የገበያ ማዕከል/Westfield Wheaton mall ያስተናግዳል። ዝግጅቱ ቤተሰቦች ስለ ትምህርት ቤቶች ስርዓትአቀፍ መረጃ እና የካውንቲ ፕሮግራሞችን እና አገልግሎቶችን እንዲያውቁ ጥሩ አጋጣሚ ነው። ለቤተሰብ ተስማሚ የሆኑ እንቅስቃሴዎች፣ መዝናኛዎች፣ የበሽታ መከላከል ክትባት ክሊኒክ እና ሌሎችም ይኖራሉ። አድራሻ፦ Westfield Wheaton is located at 11160 Veirs Mill Road. በሠመር ወቅት በሙሉ ወቅታዊ ጉዳዮችን ለማግኘት ድረ-ገጻችንን ይከታተሉ።
3. በዚህ ሠመር ለልምምድ፣ለመዘጋጀት እና ለክለሳ ነፃ የኦንላይን ሪሶርሶች/መርጃዎች አሉ።
ነጻ የኦንላይን መርጃዎች/ሪሶርሶች በሠመር ትምህርት የማስጠናት ፕሮግራም ወይም በሠመር ትምህርት ቤት ለማይሳተፉ ተማሪዎች ድጋፍ ይሰጣል። ይህ ሰነድ 2023–2024 የትምህርት አመት ነፃ የትምህርት መርጃዎችን እና የአንደኛ ደረጃ፣ መካከለኛ ደረጃ እና ሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች የትምህርት ይዘታቸውን ለመገምገም፣ ችሎታቸውን ለማዳበር መለማመድ እና ለ 2023–2024 የትምህርት ዘመን የሚያዘጋጁ ተግባሮችን ያካትታል።
4. በብሉፕሪንት ህግ ተነሳሽነት እና ፕሮግራሞች ላይ የእርስዎን አስተዋጽኦ ግብአት እንፈልጋለን
MCPS ስለ እንቅስቃሴዎች እና ፕሮግራሞች መስፋፋት የሜሪላንድ ብሉፕሪንት ተግባራዊ በሚደረግበት ጊዜ ሁሉንም ተማሪዎቻችንን፣ ወላጆችን፣ አጋሮቻችንን እና ማህበረሰቡን ይነካል።
የሜሪላንድ የወደፊት ብሉፕሪንት 2021 ላይ የጸደቀ ወሳኝ ህግ ነው፣ ይኼውም በሜሪላንድ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤቶችን እና የልጅነት አጠቃላይ ለውጦችን ያካትታል። በተጨማሪ የትምህርት ባጀት ድጋፍ፣ ብሉፕሪንት የተማሪን ውጤታማነት ያፋጥናል፥ እና በሜሪላንድ ውስጥ ያለውን አጠቃላይ የትምህርት ጥራት ያሻሽላል።
MCPS ለባለድርሻ አካላቱ እና ለማህበረሰቡ አክብሮት ይሰጣል። እባክዎ የብሉፕሪንት ዳሰሳውን ለማጠናቀቅ ጥቂት ደቂቃዎችን ይውሰዱ እና አስተያየትዎን ይስጡን። ከእርስዎ ለመስማት እንፈልጋለን።
በሌሎች ቋንቋዎች ዳሰሳ፦
English / español / 中文 / français / Português / 한국어 / tiếng Việt / አማርኛ
5. የዚህ ሳምንት ጉልህ ክንዋኔዎች
MCPS በጨረፍታ፡ 2023 የምረቃ ፕሮግራሞች
የትምህርት ቦርድ ለአመቱ ምርጥ ካውንስለሮች/አማካሪዎች አክብሮት ይሰጣል።
ሶስት ሰራተኞች 2022–2023 የአመቱን የምርጥ ካውንስለርነት/አማካሪነት ሽልማት አግኝተዋል። ማኬዳ ሶሪያኖ፣ ከሞንትጎመሪ ብሌየር ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት (Makeyda Soriano, Montgomery Blair High School)፣ ዮላንዳ ፌርበር፣ ከዌስትብሩክ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት (Yolanda Faerber, Westbrook Elementary School)፣ እና ኒኮል ዋልተር፣ ከሮቤርቶ ክሌሜንቴ መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት (Nicole Walter, Roberto Clemente Middle School) እንኳን ደስ አላችሁ!
Montgomery County Public Schools
Email us: ASKMCPS@mcpsmd.org