ወደ ትምህርት ቤት ሲመጡ እና ከትምህርት ቤት ሲመለሱ፣ ከትምህርት ቤት በኋላም የተማሪዎችንን ደህንነት ለመጠበቅ በአብሮነት መቆም

ለተከበራችሁ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ማህበረሰብ፦

በዚህ ሳምንት፣ "ወደ ት/ቤት በእግር እና በብስክሌት የሚጓዙበት ሣምንት" ላይ "በአብሮነት ስለ መቆም" ቁርጠኝነታችንን ሙሉ ለሙሉ የማየት እድል ነበረኝ። ይህ አጋጣሚ ተማሪዎች ወደ ትምህርት ቤት የሚደርሱበትን ሠላማዊና አስተማማኝ ሁኔታ ለመፍጠር ሁላችንም የምናደርገውን ጥረት የምናከብርበት በዓል ነው። በእርግጥም በደህና ወደ ትምህርት ቤት መድረስ ጥሩ የትምህርት ቀን ለማሳለፍ የመጀመሪያው እርምጃ ነው።

ወደ ትምህርት ቤት በእግር የመሄድ ቀን ከትምህርት ቤቶቻችን፣ ከተማሪዎቻችን እና ከደህንነታቸው ጎን በአብሮነት ስንሰበሰብ ልንፈጥራቸው የምንችላቸውን አስደናቂ ተሞክሮዎች የሚያሳይ ሌላ ታላቅ ምሳሌ አሳይቷል። ስለሆነም በትምህርት ቤቶቻችን ማህበረሰብ ውስጥ በተለያዩ መንገዶች ኢንቨስት ያደረጋችሁትን ላመሰግናችሁ እፈልጋለሁ።

ለምሳሌ፦ በግሌን ሄቨን አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት (Glen Haven Elementary School) ርእሰ መምህር ታራ ስትሪን (Tara Strain)፣ የአካል ማጎልመሻ ትምህርት መምህርት ሜሪ ጆ ስቶልቴ (Mary Jo Stolte)፣ እና ካውንስለር ርብቃ ኤች ዊሊስ (Rebecca H. Willis) በአካባቢው በሚገኝ መናፈሻ ውስጥ ማህበረሰቡን ሰብስበው ሁሉም ሰው በሰላም አብረው ወደ ትምህርት ቤት እንዲጓዙ ጥረት አድርገዋል፣ በመንገዶቹ ላይ ተገቢውን ጥንቃቄ ማድረጋቸውን ለማረጋገጥ በፖሊስ አጋሮቻችን በኩል ድጋፍ ተደርጓል።

ወደ ትምህርት ቤት እየሄድኩ ሳለ፣ ሁለት የመዋዕለ ሕፃናት ተማሪዎች በእግራቸው እየተጓዙ እንዲሳተፉ ትምህርት ቤቱ ባዘጋጀላቸው "scavenger hunt" ረድቻቸዋለሁ። እንዲሁም ወደ ትምህርት ቤቱ እንደደረስኩ፣ ተማሪዎች የግሌን ሄቨን ትምህርት ቤትን ሙዚቃ ሲዘምሩበት በነበረው ሁኔታ ተደስቻለሁ—ይህም በኬቲ ፔሪ “ማንቧረቅ/Roar” የተቀረጸው፣ ተማሪዎችን “እንዲነቃቁ” የሚያበረታታ ነው።

ከዚያም፣ በዊተን ውድስ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት (Wheaton Woods Elementary School) የካውንቲያችን ፖሊስ፣ የእሳት አደጋ መከላከያ ቡድን፣ የመጓጓዣ በጎ ፈቃደኞች ወላጆች፣ እና የመዝናኛ አጋሮች ተማሪዎችን በሙዚቃ እና በባሉን ፊኛዎች ተቀብለዋቸዋል። ይህ አይነት ትብብርና አጋርነት ሁሉም ተማሪዎች እንዲበለጽጉ የሚያስፈልጋቸውን ማነቃቂያ ተደራሽነት እንዲኖራቸው በርእሰ መምህር ኖራ (ሊዝ) ኮሊንስ (Principal Nora (Liz) Collins) አማካይነት የታቀፈው በማህበረሰብ ትምህርት ቤቶች ፕሮግራም በኩል የተቀናጀ ጥረት አካል ነው።

በትምህርት ቤቶች ውስጥ በየቀኑ ሙዚቃ እና ዳንስ ማድረግ ባንችልም እነዚህ ልዩ አጋጣሚዎች ተማሪዎቻችን ወደ ትምህርት ቤት ሲመጡ ዋጋ የሚሰጣቸው እና እንዲካተቱ ለማድረግ ሰራተኞቻችን እና ማህበረሰባችን የሚያደርጉትን ሁሉ ለማስታወስ የሚረዱ እንቅስቃሴዎች ናቸው። እናም እንደዚህ እንዲሰማቸው ለመርዳት መላው ማህበረሰባችን ከተማሪዎቻችንን ጎን እንዲሰባሰቡ ያስፈልጋል።

ከትምህርት በኋላ ደህንነት፡

ደጋግመን እንደምናሳስበው፥ የሠላምና ደህንነት ጉዳይ በአንደኛ ደረጃ ት/ቤቶች፣ በመካከለኛ ደረጃ ት/ቤቶች፣ እና እስከ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶቻችን ሁሉ ይዘልቃል። ከትምህርት ቀን በኋላም ይዘልቃል - የመላውን ማህበረሰባችንን መተጋገዝ ይፈልጋል። የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶቻችን ማህበረሰቦች በአትሌቲክስ ውድድሮቻችን ወቅት ሠላምና ደህንነትን እንዴት እንደምናስጠብቅ እያረጋገጡ ናቸው። 

በትላንትናው የማህበረሰብ መልዕክት ላይ እንደተጠቀሰው፣ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) የአትሌቲክስ ደህንነት ጥበቃ እቅድ በፕሮግራም የተያዙ ስራዎቹን ይቀጥላል። የቫርሲቲ ፉትቦል ጨዋታዎች በዚህ ጊዜ በደረጃ 1 ውስጥ ይቀጥላሉ፣ የደረጃ 2 ጨዋታዎች በተናጠል ሊተገበሩ ይችላሉ። ለእያንዳንዱ ደረጃ የውሳኔ አሰጣጥ መመሪያዎች በደህንነት እቅድ ውስጥ ተዘርዝረዋል። ለሌሎች ስፖርቶች፣ የአከባቢ ትምህርት ቤቶች የሚፈልጉትን የደረጃ 1 ገደቦች፣የመግቢያ ሂደቶችን በመሳሰሉት ላይ ማሻሻያ እያደረጉ ተገቢውን መስተንግዶ መስጠት ይችላሉ።

የሰራተኞቻችንን እና የተማሪዎቻችንን ደህንነት ለመጠበቅ ስለምታደርጉት ጥረት ሁሉ እናመሰግናለን።

ከወዳጅነት ጋር
Monifa B. McKnight
Superintendent of Schools



Email us: ASKMCPS@mcpsmd.org

Montgomery County Public Schools