ከሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) የትምህርት ቤቶች ጤና አጠባበቅ ባለሙያ/ኦፊሰር የተላለፈ ጠቃሚ መልእክት


ለተከበራችሁ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ማህበረሰብ፦

ባለፈው ሳምንት በትምህርት ክፍሎች የኮቪድ-19 ወረርሽኝ መጨመሩን አይተናል። በ CDC ሪፖርት መሠረት አጠቃላይ የኮቪድ-19 የማህበረሰብ ስጋት ደረጃ ዝቅተኛ ቢሆንም በሞንትጎመሪ ካውንቲ የኮቪድ-19 ስርጭትን፣ ኢንፍሉዌንዛ እና RSV ጨምሮ ሌሎች የመተንፈሻ አካላትን የሚጎዱ ቫይረሶችን መከላከል እና በንቃት በመከታተል ትኩረት ማድረግ አለብን። በትምህርት ቤቶቻችን ማህበረሰብ ውስጥ የጤና አጠባበቅን ለማዳበር ልናደርጋቸው የምንችላቸው ጥቂት ነገሮች አሉ።

  1. መሰረታዊ የጤና አጠባበቅ ንፅህና ልምዶችን ይቀጥሉ። በደንብ እጅ መታጠብን፣ የአተነፋፈስን ሃይጂን መጠበቅ (ሳል ወይም ማስነጠስ ሲኖር መሸፈን)፣ የጋራ ቦታዎችን ማጽዳት እና በጀርሞች እንዳይበከል መጠበቅ እና ሲታመሙ ቤት መቆየትን ያካትታል። ወደ ቀዝቃዛ ወቅት እና ፍሉ የሚበዛበት ጊዜ ላይ ስንሻገርና ብዙ ጊዜ ቤት ውስጥ ስናሳልፍ እነዚህን ጥንቃቄዎች ማድረግ ከመቼውም ጊዜ ይበልጥ አስፈላጊ ናቸው።
  2. ለመጪው የጉንፋን ወቅት መዘጋጀት ያስፈልጋል። በዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ በኢንፍሉዌንዛ በሽታ የመያዝ ሁኔታዎች እየተከሰቱ ናቸው። ኤክስፐርቶች ከባለፈው አመት ጋር ሲያነፃፅሩ ከፍ ያለ በፍሉ/በጉንፋን የመያዝ ሁኔታዎችን ይተነብያሉ፣ ኮቪድ-19 ለመከላከል የሚወሰዱ እርምጃዎች ጉንፋንን ጭምር ለመከላከልም ጠቃሚ ስለነበሩ በጥቂቱም ቢሆን ጉንፋንን የመከላከል አቅም እንዲኖረን አስችሎን ነበር። መሰረታዊ የጤንነት ንፅህና አጠባበቅ ልምዶች ጉንፋንን ለመከላከል ይረዳሉ። የፍሉ ክትባቱ በጉንፋን የመያዝ እድልን እና የጉንፋን ኢንፌክሽንን ይቀንሳል። እድሜው(ዋ) ከ 6 ወር በላይ ለሆነ ማንኛውም ሰው በነጻ የሚሰጥ ነው፣  በተለይ ለጉንፋን ችግሮች ተጋላጭ ለሆኑ ሰዎች አስፈላጊ ነው።
  3. በትምህርት ቤታችን ማህበረሰብ ውስጥ የኮቪድ-19 ስርጭትን ለመከላከል የሚያደርጉትን እገዛ ይቀጥሉ።
    • ክትባቱ አሁንም ከባድ ችግሮችን፣ ሆስፒታል መተኛትን ወይም በኮቪድ-19 ምክንያት ሞትን ለመከላከል በጣም ውጤታማ መሳሪያችን ነው። አዲሶቹ የኮቪድ-19 ቡስተሮች/boosters በቅርብ ጊዜ የተከሰቱትን Omicron ተዋስያን ለመከላከል የተዘጋጁ ሲሆኑ በካውንቲ ስፖንሰር በሚደረጉ ክሊኒኮች በትምህርት ቤቶች ክትባት በሚሰጡ ክሊኒኮች ሁሉ ይገኛሉ፣ ወይም በግል ፋርማሲዎችና በሌሎች አካባቢዎችም ይገኛሉ። የክትባቶች በሽታን የመከላከል ጥቅም ከጊዜ ወደ ጊዜ እየቀነሰ ሊሄድ ስለሚችል፣ ቡስተሮች (boosters) በተለይ ለኮቪድ-19 የመጋለጥ እድላቸው ከፍተኛ ለሆነ ሰዎች በጣም አስፈላጊ ናቸው።
    • ሰራተኞች እና ተማሪዎች የኮቪድ-19 ምልክቶች ከታዩ፣ ወይም በኮቪድ-19 የተያዘ ሰው ጋር የቅርብ ግንኙነት ከተፈጠረ፣ ከተጠራጠሩ፣ ወይም እርግጠኛ ከሆኑ የኮቪድ-19 ምርመራ ማድረግ አለባቸው። እባክዎትን የ MCPS ሰራተኞች እና ተማሪዎች ሁሉንም ፖዚቲቭ የምርመራ ውጤቶች ኦንላይን ሪፖርት ያድርጉ እንዲሁም ራስን ስለማግለል እና ለወረርሽኙ እንዳይጋለጡ  CDC መመሪያዎችን ይከተሉ ።
    • በአሁኑ ወቅት በሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ህንፃዎች እና ፋሲሊቲዎች ውስጥ ጭምብል ማድረግ እንደ አማራጭ ነው፣ ኳራንቲን መቆየት እና ራስን የማግለል መመሪያ ላይ አስፈላጊ ካልሆነ በስተቀር። በትምህርት ቤት ውስጥ የወረርሽኝ ስርጭት በሚከሰትበት ጊዜ ተጨማሪ ስርጭትን ለመከላከል ቤት ኳራንቲን ከማቆየት ይልቅ በጊዜያዊነት ጭንብል መጠቀም እና ምርመራ ማድረግን እንደ አማራጭ እንተገብራለን ። በእነዚህ ሁኔታዎች ግለሰቦች ደህንነቱ በተጠበቀ ሁኔታ ወይም በተከታታይ ጭምብል ማድረግ በማይችሉበት ጊዜ ሌሎች አማራጮችን ማጤን እንቀጥላለን። እንዲሁም እያንዳንዱ ግለሰብ በማንኛውም የአደጋ ደረጃ ላይ ለራሳቸው የጤና ምክንያቶች ጭምብል ለመጠቀም ወይም የሌሎች ሰዎችን ደህንነት ለመጠበቅ የሚያደርጉትን ውሳኔ እናከብራለን።

ከሕዝብ ጤና ጥበቃ አጋሮቻችን ጋር በካውንቲው እና በዲስትሪክት ደረጃ የጤና መረጃዎችን አዝማሚያዎች በቅርበት መከታተል እንቀጥላለን። የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ማህበረሰባችንን ጤንነት ትኩረት በመስጠት በአካል የመማር እድል በመፍጠር አኳያ በአብሮነት የሚያስደንቅ የትምህርት አመት እንዲቀጥል ስለሚረዱን እናመሰግናለን።

ከልብ
Patricia Kapunan, MD, MPH
MCPS Medical Officer



Email us: ASKMCPS@mcpsmd.org

Montgomery County Public Schools