ውድ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ቤተሰቦች

ይህ መልእክት ሰኞ፣ ኤፕሪል 22 ለሁሉም ተማሪዎች አንድ አይነት ተመሣሣይ የመማሪያ ቀን እንዳልሆነ ለማሳወቅ ነው። ቀኑ በ 2023-2024 መደበኛ የትምህርት ቀናት አቆጣጠር/ካላንደር ላይ በተገለፀው መሠረት ለመምህራን የሙያ ማዳበር እለት ከመሆኑም በላይ ለተማሪዎች የትምህርት ማካካሻ ቀን ተብሎ ተቀምጧል። ተማሪዎች በትምህርት ላይ የሚሳተፉ ሲሆን ማጠናቀቅ ያለባቸውን የትምህርት ስራ ተመሳሳይ ባልሆነ ጊዜ ያጠናቅቃሉ።

አንድ ላይ ተመሣሣይ ያልሆነ የትምህርት ሠአት ለተማሪዎች ቴክኖሎጂን ተጠቅመው ወይም ሳይጠቀሙ ያልተጠናቀቁ የትምህርት ስራዎችን እንዲያጠናቅቁ ያስችላቸዋል። ተጨማሪ የትምህርት ሥራዎችን ማጠናቀቂያ ጊዜ የሚሰጠው ተማሪዎች በተለያዩ አዳጋች ምክንያቶችና ተግዳሮቶች ወይም ባልተጠበቁ ሁኔታዎች ማከናወን ያልቻሉትን የተመደበላቸውን የትምህርት ሥራ እንዲያጠናቅቁ ነው።

የዲስትሪክቱ መሪዎች እና የማእከላዊ ጽ/ቤት አገልግሎት ሰራተኞች ኤፕሪል 22 ለሚደረገው ያልተመሳሰለ የትምህርት ሠዓት/ቀን ዝግጅትን በተመለከተ ከት/ቤት መሪዎች ጋር እያቀዱ እና እየተነጋገሩ ሰንብተዋል።

ትምህርት ቤቶች ማርች አጋማሽ ላይ ተመሳሳይ ባልሆነ ሰአት ስለሚካሄደው ቨርቹዋል የማስተማሪያ ዕቅዶቻቸው ተጨማሪ ዝርዝሮችን፣ ግብዓቶችን እና ተጨማሪ አገልግሎቶችን እንዴት ማግኘት እንደሚችሉ አቅጣጫ ይሰጣሉ።

ይህ ቀን በራስ የመመራት ትምህርት እና እቅድ ውስጥ ለሚሳተፉ አስተማሪዎች የሙያ ማዳበር መማሪያ ቀን ሆኖ ይውላል። ቴሌ ዎርክ/ሥራ ይፈቀዳል። በተጨማሪም፤ መምህራን ሚዛናዊ በሆነ የማስተማር እና የመማር ማዕቀፍ ላይ በማተኮር ተመሣሣይ ባልሆነ ሰአት የሙያ ማበልፀግ ትምህርት ሞጁል ላይ ለመሳተፍ ጊዜ ይኖራቸዋል። ለሰራተኞች ተጨማሪ መረጃ በሚቀጥሉት ሳምንታት ውስጥ ይሰጣል።

2023-2024 የትምህርት አመት ውስጥ —ጃኑዋሪ 16፣ ጃኑዋሪ 17፣ እና ጃኑዋሪ 19 በአስቸጋሪ የአየር ሁኔታ ምክንያት ሶስት የትምህርት ቀናት ት/ቤቶች ዝግ ነበሩ። የሜሪላንድ ስቴት የትምህርት ዲፓርትመንት (MSDE) ከባድ የአየር ሁኔታ ቀናትን እና የሰራተኞች የሙያ ማዳበር ትምህርት ቀናትን ጨምሮ የተወሰኑ ቀናትን በቨርቹዋል የትምህርት ቀናት ተክተን እንድንጠቀም ይደነግጋል።

MCPS የሦስተኛውን የስቸኳይ ሁኔታ ጊዜ ትምህርት ቤት የተዘጋበትን ቀን ለማካካስ የሚያስፈልጉ በአደጋ ጊዜ ትምህርት ቤቶችን መዘጋት የሚያስችል ሁለት ቀናት የትምህርት ማካካሻ ጊዜ እቅድ አለው።

*ማሳሰቢያ፦ የኢኖቬሽን ትምህርት ቤቶች፣ የአርኮላ እና የሮስኮ R. ኒክስ አንደኛ ደረጃ ት/ቤቶች ሰኞ፣ ኤፕሪል 22, 2024 የትምህርት ቀን መቁጠሪያ/ካላንደር አይቀየርም። ለተማሪዎች ትምህርት የሌላቸው ቀን ሲሆን ለአስተማሪ ሰራተኞች የሙያ ማበልፀግ ትምህርት ቀን ይሆናል።


ኢሜል ይላኩልን: ASKMCPS@mcpsmd.org