የማህበረሰብ መልእክት

Senior Assassins Game

ሜይ 9

ውድ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ቤተሰቦች

ይህንን የምንጽፍልዎት ከሞንትጎመሪ ካውንቲ ፖሊስ ዲፓርትመንት ከፖሊስ የተላለፈውን መልእክት ይመለከቷል፥ በካውንቲው ውስጥ ያሉ ወጣቶች "Senior Assassins'' በሚባለው ጨዋታ ላይ ሲሳተፉ የሚፈጠሩ ስጋቶችን ለማሳወቅ ነው። ይህ በቪዲዮ የተቀረጸ እና በማህበራዊ ሚዲያ ላይ የሚለጠፍ የውሃ ሽጉጥ በመጠቀም ሲንየሮች የሚጫወቱት ጨዋታ ነው። አንድ ተማሪ ከተረጨ ከጨዋታው ውጪ ይሆናል/ትሆናለች ማለት ነው። በጨዋታው ውስጥ እስከመጨረሻው ያልተረጨበ(ባ)ት ተማሪ እንደ አሸናፊ ይቆጠራል/ትቆጠራለች፣

ይህንን ጨዋታ የሚጫወቱ ተማሪዎች ጥንቃቄ የጎደለው መኪና ማሽከርከር እና አለመግባባቶችን በመሳሰሉ አደገኛ ባህሪያት ውስጥ ሊገቡ እንደሚችሉ ሪፖርት ተደርጓል፡ አንዳንድ ታዳጊ ወጣቶችም የውሃ ጠመንጃ የመሳሰሉ መሣሪያዎችን ይዘው በህዝብ የመኪና ማቆሚያ ስፍራዎች እንደሚዘዋወሩ ተገልጿል። የውሃ ጠመንጃዎችን መጠቀማቸው ልክ እንደ ጦር መሳሪያ ስለሚመስላቸው ድንጋጤ ሊያስከትል እና አንዳንድ ሰዎች ፍርሃት ስለሚሰማቸው ወደማይፈለጉ ሁኔታዎች ሊያመራ ይችላል።

ሪፖርት የተደረጉት ክስተቶች በየትኛውም የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ ያልተከሰቱ ቢሆንም፣ይህ አይነት ባህሪ በማንኛውም MCPS ካምፓስ ውስጥ በጥብቅ የተከለከለ መሆኑን ልናስታውስዎት እንፈልጋለን። ሁኔታውን በቅርበት የምንከታተል ስለሆነ፣ ከተከሰተ ወዲያውኑ ምላሽ ለመስጠት ሙሉ በሙሉ ዝግጁ ነን። 

ወላጆች/አሳዳጊዎች ሁለት ነገሮችን እንዲያደርጉ እናበረታታለን፦

  • ከጨዋታው ጋር ተያይዘው ሊከሰቱ ስለሚችሉ አደገኛ ባህሪያት እና አስከፊ ውጤቶች እና በጨዋታው ውስጥ እንዳይሳተፍ/እንዳትሳተፍ ከተማሪዎ ጋር ተነጋገሩ።
  • በማህበረሰቡ ውስጥ በዚህ ጨዋታ ምክንያት የተከሰቱ አጋጣሚዎችን ካዩ እባክዎን ወዲያውኑ ለፖሊስ ያሳውቁ።

ይህንን መረጃ በቁም ነገር እንደሚወስዱ እና ለተማሪዎቻችን ደህንነቱ የተጠበቀ አካባቢ እንድንጠብቅ እንደሚረዱን ተስፋ እናደርጋለን።

ሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ Montgomery County Public Schools


ኢሜል ይላኩልን: ASKMCPS@mcpsmd.org