ከሞንትጎመሪ ካውንቲ የትምህርት ቦርድ ፕሬዝዳንት ካርላ ሲልቬስትረ
እና ዶ/ር ሞኒክ ፌልደር፣ ጊዜያዊ ሱፐርኢንተንደንት፣ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ
2025 የትምህርት በጀትን በተመለከተ
የተሰጠ መግለጫ

ሜይ 24, 2024


የሞንትጎመሪ ካውንቲ የትምህርት ቦርድ እና የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ለተማሪዎች ቅድሚያ የሚሰጥ የባጀት ቀመር የማዘጋጀት፣የማቅረብ እና በመጨረሻም የማጽደቅ ሃላፊነት እንዳለባቸው ይታወቃል። የባጀታችን ቀመር ቁጥር ብቻ ሳይሆን የማህበረሰባችን ጉዳይ በመሆኑ ይህንን ግዴታችንን በጣም ክብደትና ትኩረት እንሰጠዋለን።

ቀደም ሲል ለካውንቲው ካውንስል አባላት፣ ሰራተኞቻችንን ወክለው ለሚደራደሩ ማህበራት እና ለማህበረሰብ አጋሮቻችን ካውንቲያችን እያጋጠመው ያለውን ከፍተኛ የገንዘብ እጥረት ችግር ለመፍታት መወሰድ ስላለባቸው አስፈላጊና ከባድ የሆኑ ውሳኔዎች አጋርተናል/ገልፀንላቸዋል። ትምህርት ቤቶች ማለት በመሠረቱ ሰዎችን የሚመለከት በመሆኑ፤ ይህ የባጀት ጉዳይ እና ሊሆኑ የሚችሉ የባጀት ቅነሳዎች በአገልግሎታቸው ቁርጠኛ በሆኑ የሰው ሃይላችን፣ በተማሪዎች እና በቤተሰቦች ላይ የሚያሳድረውን ከፍተኛ ተጽእኖ እንገነዘባለን።

ጁን 11 ቦርዱ በጀቱን እስኪያፀድቅ ድረስ የመጨረሻ ውሳኔ አይደረግም። ቦርዱ እና የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) አመራር በሜይ ወር ከካውንቲው ካውንስል ጋር የተጋሩበትን የበጀት ማስተካከያዎች ጭምር መገምገማቸውን የሚቀጥሉ ሲሆን፦

  • ከማዕከላዊ ቢሮ ቅነሳ የማይመለከታቸው (ለትርፍ ሰዓት ብቁ ያልሆኑ) እና የሚመለከታቸው (ለትርፍ ሰዓት ብቁ የሆኑ) ሠራተኞች።

  • ቅነሳ የሚመለከታቸው የመካከለኛ እና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የሰራተኞች ሙያ ማዳበር አስተማሪዎች (SDT) 0.4 FTE ምድብ ላይ ያሉትን ሲሆን፣የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት SDT ምድብ ላይ የሚሠሩትን ቅነሳ አይመለከትም። 

  • የመማሪያ ክፍል መመሪያው የተማሪ ብዛት በ1ተማሪ ይጨምራል። ይሄ ከ 100 እስከ 150 የስራ መደቦችን ቅነሳ ሊያስከትል ይችላል። ከእነዚህ ቅነሳዎች መካከል አንዳንዶቹን በጡረታ እና ሌሎች በሚጠበቁ ክፍት የሥራ ቦታዎች ልንወስድ እንደምንችል እንገምታለን። 

  • የሞንትጎመሪ ቨርቹዋል አካዳሚ መወገድ። 

  • በቅድመ መዋዕለ ሕጻናት ማስፋፋት መዘግየት ምክንያት ተጨማሪ የቅድመ-መዋእለ ህጻናት የሙሉ ቀን ትምህርት ክፍሎችን መፍጠር ለሌላ ጊዜ ይተላለፋል፣

  • በአንዳንድ የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች ተጨማሪ የኮሌጅ ትራክ ካውንስሊንግ አገልግሎቶች ይቀነሳሉ፣

  • ታይትል አራት (Title IV) ላይ ያለውን ባጀት በማስተካከል ቴራፒዩቲካል የአእምሮ ጤና ድጋፍ መስጠት፣(የተማሪዎች ድጋፍ እና የአካዳሚክ ማበልጸጊያ) Title IV እርዳታ እነዚህን የሚፈቀዱ አገልግሎቶችን በቅንጅት መስጠት።

  • በርካታ የኮንትራት ሥራዎችን የሚመለከቱ አገልግሎቶች ይቀነሳሉ።

  • በድህነት ለተጎዱ ትምህርት ቤቶች የሚሰጠውን የሙዚቃ መሳሪያ ጥገና አገልግሎት መቀነስ።

በቅርብ ጊዜ ለካውንቲው ካውንስል እና ሰራተኞችን ወክለው ለሚደራደሩ ማህበራት አመራሮች በተሰጠው ዝርዝር ውስጥ ያልተካተቱ ወደ $13.7 ሚሊዮን ዶላር የሚያስፈልግ የኮንትራት አገልግሎትን የሚመለከት ህዝባዊ ውይይት ተደርጓል። ዝርዝሩ ስለ ዋና ዋና ኮንትራቶች መረጃ ለመለዋወጥ እና ኮንትራቶችን የሚመለከት ባጀት በምድብ ለይቶ ለማሳየት የታሰበ ነበር። ግንዛቤ ለመፍጠር፣ MCPS ሙሉውን የኮንትራት አገልግሎት በጀት በዝርዝር ያቀረበ ሲሆን፥ አጠቃላይ ዝርዝሩ ለካውንቲው ካውንስል እና ሰራተኞችን በመወከል ድርድር ለሚያደርጉ ማህበራት አመራሮች ይቀርባል።

የፋይናንስ መረጋጋትን ለማረጋገጥ የግዳጅ ቅነሳ (RIF) ማድረግ አስፈላጊ ስለሚሆን በአንድ የመማሪያ ክፍል የተማሪዎችን ቁጥር መጨመር ሊያስከትል ይችላል። RIF አፈጻፀሙ በሁሉም የሰራተኛ ቡድኖች ላይ ተጽእኖ ስለሚኖረው፣ ከሰራተኛ ማህበራት - የአገልግሎት ሰራተኞች አለም አቀፍ ህብረት (አንቀጽ 21፣ ገጽ 45)፣ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ትምህርት ማህበር ጋር በተደረገው ድርድር ላይ በተገለጹት ሂደቶች መሰረት ተግባራዊ ይሆናል። (አንቀጽ 30፣ ገጽ 63)፣ እና የሞንትጎመሪ ካውንቲ የአስተዳዳሪዎች እና ርእሰ መምህራን/የሞንትጎመሪ ካውንቲ የቢዝነስ እና ኦፕሬሽን አስተዳዳሪዎች ማህበር (አንቀጽ 25፣ ገጽ 52) መሠረት ተግባራዊ ይሆናል።

የእነዚህ ውሳኔዎች ክብደት እና የሚያስከትሉትን ተግዳሮቶች እንረዳለን። እነዚህ እርምጃዎች የሰራተኞቻችን ቁርጠኝነት ወይም የስራ ጥራት ነጸብራቅ እንዳልሆኑ አጽንኦት ልንሰጥ እንፈልጋለን። ሰራተኞቻችን የሚቀጥሉትን ሳምንታት እንዲቃኙ ለመርዳት ግብዓቶችን እና እገዛ ለማድረግ ቁርጠኞች ነን።

በእነዚህ ፈታኝ ሁኔታዎች ውስጥ እንኳን ቢሆን፣ ለእያንዳንዱ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ተማሪ ምርጥ ትምህርት ለመስጠት ያለን ቁርጠኝነት የፀና ነው።



ኢሜል ይላኩልን፦ ASKMCPS@mcpsmd.org