መታወቅ ያለባቸው ጉዳዮች

MCPS መታወቅ ያለባቸው ጉዳዮች

ሐሙስ፣ ኤፕረል 18, 2024


1. ማሳሰቢያ፡ ሰኞ ኤፕሪል 22 በተናጠል የሚከናወን የትምህርት ቀን ነው።

ሰኞ፣ኤፕሪል 22 በተናጠል የሚካሄድ የመማሪያ ቀን ስለሆነ ለተማሪዎች ማካካሻ የትምህርት ቀን ይሆናል። ተማሪዎች ራሳቸውን ችለው እንዲያጠናቅቁ ከተመደበላቸው የቤት ሥራ ጋር ወደ ቤታቸው ይላካሉ። ዲጅታል በይነመረብ ላይ የሚሰጥ ትምህርት አስተማሪዎች በቀጥታ የሚሰጡት ትምህርት ሳይሆን ወይም ቴክኖሎጂን ሳይጠቀሙ ተማሪዎችን በትምህርት ላይ የሚያሳትፉ ትምህርታዊ እንቅስቃሴዎችን እና የተመደበላቸውን የትምህርት የቤት ስራዎችን ይገልጻል። ተማሪዎች በእለቱ በትምህርት ላይ መገኘታቸውን ለማረጋገጥ የተመደበላቸውን የቤት ስራዎች ማጠናቀቅ አለባቸው።
ይበልጥ ያንብቡ / en español


2. ፕራኔል ሱቫርና/Praneel Suvarna የቦርዱ ቀጣይ ተማሪ የቦርድ አባል (SMOB) ሆኖ ተመርጧል።

በክላርክስበርግ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ጁኒየር የሆነው ፕራኔል ሱቫርና 2024-2025 የትምህርት አመት ተማሪ የትምህርት ቦርድ አባል (SMOB) ሆኖ ተመርጧል። የአቶ ሱቫርና የአገልግሎት ዘመን የሚጀምረው ጁላይ 1, 2024 ነው።

ኤፕሪል 17 በተደረገው ምርጫ ከ 58,927 በላይ የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች ድምጽ ሰጥተዋል።
ይበልጥ ያንብቡ / en español


3. የትምህርት ቦርድ (BOE) ስለ እንግሊዝኛ ቋንቋ ተማሪዎች ትምህርት አስተያየት ይፈልጋል

የትምህርት ቦርድ ፖሊሲ IOD፣ ጀማሪ የብዝሃ ቋንቋ ተማሪዎች/"Education of Emergent Multilingual Learners" ማሻሻያዎች ላይ አስተያየት ይፈልጋል። ለህዝብ አስተያየት መስጫ ገፅ የቋንቋ ትርጉሞች እየተዘጋጁ ስለሆነ እንደደረሰን ወዲያውኑ ይለጠፋሉ። ይበልጥ ያንብቡ.

ቦርዱ በፖሊሲ IKB፣ የቤት ስራ እና ፖሊሲ GEA ስለ MCPS መሪዎች በቦርድ የሚሰጥ ሹመት በቀረቡት ማሻሻያዎች ላይ የህዝብ አስተያየት ይፈልጋል።
ይበልጥ ያንብቡ / en español


4. ስለ ጉልበተኝነት፣አድልዎ፣ ጥላቻ እና ትንኮሳ የተማሪዎች PSA

የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ተማሪዎች ቡድን ስለ ጉልበተኝነት፣ ትንኮሳ፣ እና የጥላቻ አድሎአዊ ተጽእኖ ግንዛቤን ለማስፋት ስብሰባ አካሂደዋል። ይህ በተማሪዎች የሚመራ የቪዲዮ ዘመቻ እኩዮቻቸውን እና የትምህርት ቤቱን ማህበረሰብ ችግር ለመፍታት እና ለማገዝ እየተካሄደ ያለው ስራ አካል ነው።
ይበልጥ ያንብቡ / en español


5. በቅርቡ የሚከናወኑ ዝግጅቶች፣ ማሳሰቢያዎች እና መገልገያዎች/ሪሶርሶች

ስለ ደህንነት ቀን ሜይ 11 የሚቀርብ ዝግጅት ላይ ለመሳተፍ ቀኑን ይቆጥቡ

ሜይ 1 በልጆች ዝግጅት ላይ ስለ ሻምፒዮኖች ይከታተሉ

ረቡዕ፣ ሜይ 1 የሞንትጎመሪ ካውንቲ የአመቱ ምርጥ መምህር በቀጥታ ስርጭት ስናስተዋውቅ ከእኛ ጋር ይሁኑ። ጄኒ ኤርሌ (Janie Earle) በፑልስቪል አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የመዋዕለ ህጻናት መምህርት፤ ካሪ ክራይናክ (Carrie Kraynak) በፍላወር ሂል አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የእንግሊዝኛ ቋንቋ ማዳበር መምህር፣ሞርጋን ፓቴል (Morgan Patel) የሞንትጎመሪ ብሌየር ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የማህበራዊ ጥናት መምህር፣ እና ሜሊሳ ፖርተር ፓርክስ (Melissa Porter Parks) በጌትስርበርግ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የእንግሊዘኛ ቋንቋ ማዳበር መምህር 2024–2025 የአመቱ ምርጥ መምህር የመጨረሻ እጩዎች ናቸው። 

የዘንድሮው በዓል ከቀኑ 6፡30 p.m. ስለሚሠራጭ MCPS ድረገጽላይ ይከታተሉ። የቀጥታ ስርጭቱን እዚህ መመልከት ይችላሉ።

ይበልጥ ያንብቡ / en español

ቀኑን ይቆጥቡ፡ ሜይ 11 ለሚከናወነው የደህንነት ቀን

ቀኑን ይቆጥቡ፡ ሜይ 11 ለሚከናወነው የደህንነት ቀን

የሞንትጎመሪ የትራንስፖርት መምሪያ ሁሉንም የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ቤተሰቦች ቅዳሜ ሜይ 11 በካርቨር የትምህርት አገልግሎት ማእከል (CESC) ሮክቪል የመኪና ማቆሚያ ቦታ ላይ ስለ ደህንነት ቀን ዝግጅት ላይ እንዲገኙ ይጋብዛል። ስለ ደህንነት ግንዛቤ ቀን በአዝናኝ እና በበዓላት አከባቢ ህብረተሰቡ ስለ ትራፊክ ደህንነት የበለጠ ግንዛቤ እንዲኖረው ማህበረሰቡን በአንድ ላይ ያሰባስባል። አድራሻ፦ CESC is located at 850 Hungerford Drive
ይበልጥ ያንብቡ / en español

ቀኑን ይቆጥቡ፡ ሜይ 11 ለሚከናወነው የደህንነት ቀን ያስታውሱ

ስለ ኮቪድ-19 ማሳሰቢያ፡ ከኤፕሪል 15, 2024 ጀምሮ፣ MCPS ስለ ኮቪድ-19 እና የሌሎች ቫይረሶችን ወረርሽኝ በሚመለከት የሜሪላንድ የጤና መምሪያ የበሽታ መቆጣጠሪያ እና መከላከያ ማእከል ወቅታዊ መመሪያ። ለበለጠ መረጃ MCPSCovid Information Portal ይጎብኙ።


6. መልካም ዜና

አምስት ተማሪዎች የአማዞን የወደፊት መሐንዲስ ስኮላርሺፕ አሸንፈዋል

አምስት ተማሪዎች የአማዞን የወደፊት መሐንዲስ ስኮላርሺፕ አሸንፈዋል

አምስት የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ተመራቂ ተማሪዎች በኮምፒውተር ሳይንስ ወይም ምህንድስና ዲግሪ ለመከታተል በአራት ዓመት ውስጥ እስከ $40,000 የሚያወጡ 2024 Amazon Future Engineer ስኮላርሺፕ አግኝተዋል።
ይበልጥ ያንብቡ / en español

ተማሪዎች ለኮሌጅ እና ለሙያ ዝግጁነት እንቅስቃሴዎች እና ፕሮግራሞች ላይ ይሳተፋሉ

ተማሪዎች ለኮሌጅ እና ለሙያ ዝግጁነት እንቅስቃሴዎች እና ፕሮግራሞች ላይ ይሳተፋሉ

9ኛ ክፍል ተማሪዎች ሁሉም በዚህ ስፕሪንግ ወቅት በአካል ወይም በቨርቹዋል የኮሌጅ ጉብኝት የማድረግ እድል አላቸው። የኮሌጅ ጉብኝት ልምድ ወደ 7,000 ለሚጠጉ የዘጠነኛ ክፍል ተማሪዎች እንደ ድህረ-ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት አማራጭ ለኮሌጅ ቅድመ እይታን ይሰጣል፣ ምርጫዎቻቸውን በማጥራት እና ስለኮሌጅ ህይወት፣ ስለ ኮሌጅ ፕሮግራሞች እና ስለ ኮሌጅ መግቢያ ሂደቶች የበለጠ ግንዛቤ እንዲያገኙ ያግዛቸዋል።
ይበልጥ ያንብቡ / en español

ተማሪዎች በኮሌጅ እና ለሙያ ዝግጁነት እንቅስቃሴዎች እና ፕሮግራሞች ላይ ይሳተፋሉ

የሮቤርቶ ክሌሜንቴ መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት የኮሌጅ እና የስራ ማህበረሰብ ቀንን ኤፕሪል 11 አካሂዷል። የትምህርት ቤት መሪዎች ተማሪዎችን ስለወደፊታቸው ጊዜ ለማስተማር እና ለማነሳሳት የትምህርት ቀኑን ለኮሌጅ እና ለስራ ዝግጁነት ተግባራት መድበዋል።
ይበልጥ ያንብቡ / en español

የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ተማሪዎች ስለ ኦቲዝም ግንዛቤን ለማስፋፋት "እህት" የህፃናት መጽሔት አሳትመዋል

MCPS ተማሪዎች "እህት" የተሰኘ የልጆች መጽሔት አሳትመዋል
ስለ ኦቲዝም ግንዛቤን ለማሰራጨት

ኔዮ ኦዩሌጋ (Neeyo Ouelega)፣ በአርጋየል መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት የስድስተኛ ክፍል ተማሪ፣ እና በዋትኪንስ ሚል ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ጁኒየር እና በሞንትጎመሪ ኮሌጅ የመጀመሪያ አመት ተማሪ የሆነችው ሴቲ ኦውሌጋ (Seti Ouelega) እህቶች “ድንቅ ታላቋ እህታችን ሜጋን “Marvelous Meghan: Our Big Sister.” የተሰኘ የህጻናት መጽሃፍ በጋራ አዘጋጅተው አሳትመዋል። መጽሐፉ በአራት ዓመቷ ኦቲዝም እንዳለባት ስለታወቀው ታላቅ እህታቸው ህይወት ይዘግባል።
ይበልጥ ያንብቡ / en español



ኢሜል ይላኩልን፦ ASKMCPS@mcpsmd.org

የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS)