እውቅ ተናጋሪዎችን በመጋበዝ የምረቃ ሥነ-ሥርዓቶች ሜይ 29 ይጀመራሉ።
ከ 12,000 በላይ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ተማሪዎች ረቡዕ፣ ሜይ 29 እና ረቡዕ፣ ጁን 12 ባለው ጊዜ ውስጥ በተዘጋጁት የምረቃ ሥነ ሥርዓት መርኃግብሮች የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ዲፕሎማቸውን እንደሚያገኙ ይጠበቃል።
ንግግር ከሚያደርጉት መካከል፦ በቶማስ ኤስ ውተን ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የሚናገሩት ካሪን ዣን ፒየር ( Karine Jean-Pierre)፣ የዋይት ሀውስ ፕሬስ ሰክረተሪ፣ አረና ሚለር (Aruna Miller, Lt.)፣ የሜሪላንድ ሌተናት ገቨርነር በኖርዝዌስት ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ንግግር የሚያደርጉ ሲሆን፥ ዴቪድ ቫንተርፑል ( David Vanterpool)፣ የዋሽንግተን ዊዛርድስ ረዳት አሰልጣኝ፣ በሞንትጎመሪ ብሌር ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ንግግር ያደርጋሉ። ይበልጥ ያንብቡ.
ለሪጅናል እና ሴንትራል የሁለተኛ ደረጃ የሠመር ትምህርት የመጀመሪያ ዙር ምዝገባ ሜይ 31 ሜይ 31 ይዘጋል።
የሪጅናል የሠመር ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ፕሮግራም (በአካል) እና የሴንትራል ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የሠመር ፕሮግራም (ቨርቹዋል) የመጀመሪያው ዙር ምዝገባ ዓርብ፣ ሜይ 31 ይዘጋል። በሁለቱም ፕሮግራሞች ውስጥ የመጀመሪያው ክፍለ ጊዜ ከጁን 26 እስከ ጁላይ 16 (ጁላይ 4 ትምህርት የለም) ሁለተኛው ክፍለ ጊዜ ከጁላይ 18 እስከ ኦገስት 6. 2ኛ ዙር ምዝገባ እሁድ፣ ጁን 30 ይዘጋል። ወላጆች ተማሪዎቻቸውን ParentVue አካውንታቸው ላይ ማስመዝገብ ይችላሉ። ይበልጥ ያንብቡ.
ሜይ 31 የተማሪ አገልግሎት ትምህርት ሰአት ቅጾች የሚመለሱበት ቀን ነው
የተማሪ አገልግሎት ትምህርት (SSL) ቅፆች የሚመለሱበት የመጨረሻ ቀን አርብ፣ ሜይ 31 ነው። SSL ቅጾች በሙሉ ከጁን 1, 2023 በኋላ ለተጠናቀቀ ማንኛውም የተማሪ SSL አገልግሎት የመካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አስተባባሪ ወይም የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አስተባባሪ የት/ቤቶች ስርአት አቀፍ የመጨረሻ ቀን አርብ፣ ሜይ 31 መቅረብ አለባቸው። 2023–2024 የትምህርት አመት ወይም ከሠመር ወቅት በፊት ለተጠናቀቁ የተማሪ አገልግሎት ትምህርት SSL ቅጾች ከሜይ 31 በኋላ ተቀባይነት አይኖራቸውም። ተማሪዎች ከሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ለመመረቅ 75 የተማሪ አገልግሎት ትምህርት SSL ሰዓቶች ማግኘት አለባቸው።
ስለሚያስፈልጉት ሰነዶች የበለጠ ይወቁ እና ከሠመር ወራት በፊት SSL የተማሪ አገልግሎት ትምህርት ዕድሎችን ለማግኘት ይሞክሩ።
ጁን 1 የኩሩ ማህበረሰብ ቀን ይካሄዳል።
ቅዳሜ፣ ጁን 1 ከሠአት በኋላ 1:30–5 p.m. የኩሩ ማህበረሰብ ቀን በቤተስዳ-ቼቪ ቼዝ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ይካሄዳል። ይህ ለቤተሰብ ተስማሚ የሆነ ዝግጅት ችሎታ የሚታይባቸው ትርኢቶች፣ ጨዋታዎች፣ ዲጄ እና ዳንስ፣ የእጅ ስራዎች፣ የትረካ ጊዜ፣ በመኪናዎች የሚቀርብ ምግብ፣ እና ሽልማቶችን ያካትታል። እንዲሁም ለእንክብካቤ ሰጪዎች እና ለሰራተኞች ጠቃሚ የሆኑ የሪሶርሶች ትርኢት እና አውደ ጥናቶች ይኖራሉ። ይበልጥ ያንብቡ
2024 ፎል ወቅት "Girls’ Flag Football" እግር ኳስ ግጥሚያ ወደ MCPS እየመጣ ነው!
የክህሎት ክሊኒኮች ይኖራሉ በጁን ወር የመጀመሪያ ሳምንት በፎል ወቅት "girls’ flag football team" የልጃገረዶች እግር ኳስ ቡድን መቀላቀል ለሚፈልጉ የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች MCPS ኤፕሪል ላይ በታወጀው መሠረት በመጪው ፎል 2024 የውድድር ወቅት በሁሉም 25 የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የሴት ልጆችን "flag football" እግር ኳስ ከባልቲሞር ሬቫንስ እና አንደር አርሞር ጋር በመተባበር ያካሄዳል።
ክፍለ-ጊዜዎቹ ጁን 4፣ 5 እና 6 በዋልተር ጆንሰን፣ ጆን ኤፍ ኬኔዲ፣ እና በሴኔካ ቫሊ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የስፖርት ሜዳዎች ይካሄዳሉ።
ፍላጎት ያላቸው ተማሪዎች እዚህ መመዝገብ ይችላሉ።
ተጨማሪ መረጃ እዚህ ይገኛል።
የኬንሲንግተን ፓርክዉድ ተማሪ "Doodle for Google" በተሰኘ የተማሪዎች ውድድር የስቴት አሸናፊ በመሆን ተመርጣለች።
በኬንሲንግተን ፓርክዉድ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የሁለተኛ ክፍል ተማሪ የሆነችው የሶፊያ የቅርብ ጊዜ የጥበብ ችሎታ "Google homepage" ጉግል መነሻ ገጽ ላይ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎች እንዲመለከቱት ይደረጋል። ሶፊያ " Doodle in the Doodle" የጉግል ውድድር ላይ ከአሜሪካ ስቴቶች ከተሳተፉት 55 አሸናፊዎች አንዷ ነች። ይበልጥ ያንብቡ
ወደ 300 የሚጠጉ ጣምራ ኮርስ ተመዝጋቢ ተማሪዎች በተዘጋጀላቸው ሥነ ስርአት ላይ እውቅና ተሰጥቷቸዋል።
ረቡዕ፣ ሜይ 15 በሼዲ ግሮቭ ዩኒቨርሲቲዎች በተካሄደ ሥነ ሥርዓት ላይ ወደ 300 የሚጠጉ ሲንየር ተማሪዎች የጣምራ ኮርስ ምዝገባ ፕሮግራማቸውን በማጠናቀቃቸው እውቅና ተሰጥቷቸዋል። ከሞንትጎመሪ ኮሌጅ (MC) ጋር በመተባበር ፕሮግራሙ ለሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች በፎል (መጸው)፣ በዊንተር (ክረምት)፣ እና በስፕሪንግ (ጸደይ) ወቅት የኮሌጅ ኮርሶችን እንዲወስዱ የሚያስችላቸው ሲሆን እስከ ሁለት አመት ያለ ምንም ወጪ ኮሌጅ የማጠናቀቅ እድል ይኖራቸዋል። አብዛኛዎቹ ተማሪዎች ከኮሌጁ አሶሽዬት ዲግሪ ያገኛሉ።
የኪነጥበብ ተማሪዎች በሽልማት አከባበር ላይ አንፀባራቂ ሆነዋል
በደርዘን የሚቆጠሩ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ሲንየር ተማሪዎች በዳንስ፣ በቲያትር ትወና፣ በቲያትር ቴክኒክ፣ መዘምራን እና የሙዚቃ መሳሪያ ጨዋታ፣የሚዲያ ጥበብ፣ እና 2D እና 3D የምስል ቅንብር 23ኛው አመታዊ የሱፐርኢንተንደንት "All-County Fine Arts Awards" የተሰኘ የስነጥበብ ሽልማት ሜይ 20 በሴኔካ ቫሊ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እውቅና ተሰጥቷቸዋል። የፎተግራፎችን ክምችት ይመልከቱ።
የጌትስበርግ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አመታዊ የልዩ ትምህርት ፕሮም አስተናግዷል።
ከዋትኪንስ ሚል፣ አልበርት አንስታይን እና ዊተን ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የተውጣጡ ከ100 በላይ ተማሪዎች በጌትስበርግ ትምህርት ቤት ካፌ በተካሄደው ዓመታዊ የልዩ ትምህርት ፕሮም ተሳትፈዋል። ሁነቱ (DJ) ዲጄ እና ዳንስ የታጀበ ዝግጅት ነው። አመታዊ ዝግጅቱ ላይ ለፓራዱካተሮች እና ለወላጆች “Trojan Royalty” ኮርት አቀባበል ተደርጓል። ፕሮሙ የተደገፈው በትምህርት ቤቱ የተማሪ አመራር ማህበር ሲሆን በፎቶግራፍ እና በኮስሞቶሎጂ/የማስዋብ ትምህር ክፍሎች ድጋፍ ተደርጓል።
ነፃ የእንግሊዝኛ ትምህርት በሞንትጎመሪ ኮሌጅ
የሞንትጎመሪ ካውንቲ ነዋሪዎች ያለምንም ወጪ እንግሊዝኛ መማር ይችላሉ። ሞንትጎመሪ ኮሌጅ በአካል እና ቨርቹዋል የእንግሊዝኛ ትምህርት ይሰጣል። በአዲሱ «Comunicandonos» ኤማ ዊልሰን፣ የጎልማሶች እንግሊዝኛ ትምህርት እና የትምህርት አስተዳዳር፣ በኮሌጁ ስለሚሰጥ ነጻ ትምህርት መረጃ አጋርተዋል።
ስፓንሽኛ፦
የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) መዘምራን እና የሙዚቃ መሳሪያ ጨዋታ ፕሮግራሞችን ይመልከቱ፦
በዚህ ትዕይንት ላይ፣ MCPS ለሁሉም ተማሪዎች ስለሚሰጣቸው ጠንካራ የሙዚቃ ትምህርት ፕሮግራሞች፣ በአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የሚሰጡ ከአጠቃላይ የሙዚቃ ትምህርቶች እስከ የሙዚቃ መሳሪያ መጫወት እና የመዘምራን ፕሮግራሞች፣ እንዲሁም ከስትራትሞር ት/ቤት ጋር ስላለው አጋርነት ግንዛቤ ይውሰዱ።
መታወስ ያለባቸዉ ቀኖች፦
ሜይ 24 ተማሪዎች ቀደም ብለው የሚለቀቁበት ቀን (ኢኖቬቲቭ የቀን መቁጠሪያ ለሚከተሉ ትምህርት ቤቶች ብቻ)
ሜይ 27 ሜሞሪያል ዴይ — ትምህርት ቤቶች እና ቢሮዎች ዝግ ናቸው
ጁን 13 ለተማሪዎች የመጨረሻ የትምህርት ቀን፣ ተማሪዎች ቀደም ብለው የሚለቀቁበት ቀን (ሁሉም ትምህርት ቤቶች)
ጁን 14* ውጤት የሚሰጥበት እና የተርሙ ማብቂያ እቅድ የሚዘጋጅበት ቀን
ጁን 19 ስርዓት አቀፍ ት/ቤቶች ዝግ የሚሆኑበት ቀን—ትምህርት ቤቶች እና ቢሮዎች ዝግ ናቸውተጨማሪ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) መረጃዎች
ኢሜል ይላኩልን፦ ASKMCPS@mcpsmd.org