8ኛ ክፍል፥ ቤተሰቦች፣ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችን ይቃኙ! 8ኛ ክፍል ቤተሰቦች፥ የመካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የሚያጠናቅቁበት ዓመት ላይ ናቸው - እና ስለ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች አማራጮችን ማሰብ ለመጀመር ጊዜው አሁን ነው!
የሞንትጎመሪ ካውንቲ የህዝብ ትምህርት ቤቶች በትምሕርት ዓመት 2027–2028 ወደ 9ኛ ክፍል ለሚገቡ ተማሪዎች አዲሱን MCPS የመግቢያ ሂደት ማዕከላት ይከፍታሉ።
በእያንዳንዱ ተማሪ የአካባቢ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ከሚገኙት ድንቅ የትምህርት፣ ከመደበኛ ትምህርት ውጭ የሚከናወኑ እንቅስቃሴዎች፣ የአትሌቲክስ እና የማህበራዊ መስተጋብር እድሎች በተጨማሪ፣ ቤተሰቦች በሪጅናቸው የሚሰጡ ልዩ የአራት ዓመት ፕሮግራሞች ማዕከላትን መቃኘት ይችላሉ። ፕሮግራሞቹ በአምስት አጓጊ ሙያዎች ዙርያ የተደራጁ ናቸው፡-
በማዕከል ፕሮግራም ለመግባት ማመልከት ከፈለጉ የሚወስዱት አማራጭ ስለሆነ፣ ተማሪዎች በፍላጎታቸው መሰረት እስከ ስምንት ፕሮግራሞችን ሊመርጡ ይችላሉ። 8ኛ ክፍል ተማሪዎች እና ቤተሰቦቻቸው በመጸው/fall ወቅት የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች በሚያዘጋጓቸው ትርኢቶች ላይ እንዲገኙ እና ሰራተኞችን እና ተማሪዎችን እንዲያገኙ እና በክልላቸው/በሪጅናቸው ውስጥ ስላሉት ፕሮግራሞች የበለጠ ግንዛቤ እንዲያገኙ ይበረታታሉ። የማዕከል ፕሮግራሞች ከፈለጉ የሚወስዱት አማራጭ ናቸው።
ተጨማሪ ለማወቅ የሚፈልጉ ከሆነ
ሴፕቴምበር
ኦክቶበር
-
ከኦክቶበር ወር መጀመሪያ ጀምሮ፣ ቤተሰቦች ParentVUE እና StudentVUE ላይ በየግላቸው የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ዕድሎችን ሪፖርት ያገኛሉ። ሪፖርቱ ለእያንዳንዱ ተማሪ በቤታቸው አድራሻ በመመስረት ያሉትን የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እና የማዕከል ፕሮግራም አማራጮችን ይዘረዝራል።
-
በእያንዳንዱ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የመኸር ወቅት/Fall ዝግጅት (ቀናት ጋር የሚያገናኝ) ተማሪዎች እና ቤተሰቦች በትምህርት ቤቶቻቸው ውስጥ ያሉትን የተወሰኑ ኮርሶች፣ እድሎች፣ የማዕከል ፕሮግራሞች እና አቅርቦቶችን የመቃኘት እንዲሁም ከሠራተኞች ጋር የመገናኘት እና ከትምህርት ውጭ ስለሚሰጡ እንቅስቃሴዎች የማወቅ እድል ይኖራቸዋል።
የመጀመሪያ ዙር ማመልከቻ መቅረብ ያለበት የመጨረሻ ቀን ኖቨምበር 6, 2026 ነው።
አሁን የሚከተሉትን ለማከናወን በጣም ጥሩ ጊዜ ነው፦
-
ParentVUE አካውንትዎ እየሠራ እንደሆን ያረጋግጡ።
-
ከተማሪዎ ጋር ስለ ፍላጎቶቹ(ቿ) እና ስለ ግቦቹ(ቿ) ተነጋገሩ።
-
መጪዎቹን የሁ/ደ/ት/ቤት ጉብኝት ቀናት ይመልከቱ።
-
የአካባቢዎን የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እና የማዕከል ፕሮግራም እድሎችን መቃኘት ይጀምሩ።
የተማሪዎ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ጉዞ በበርካታ እድሎች የታጀበ ነው። በሚቀጥሉት ሳምንታት፣ እርስዎ እና ተማሪዎ ያሉትን በርካታ እድሎች እንድትቃኙ፣ ወደፊት ስለሚሆነው ነገር ለመጓጓት እና ስለወደፊታቸው በእውቀት ላይ የተመሰረተ ውሳኔ እንዲያደርጉ የሚያግዝ ተጨማሪ መረጃ እናጋራለን። |