Is this email not displaying correctly? View it in your browser Date: June 14, 2020


mcps logo

English | español | 中文 | français | tiếng Việt | 한국어| አማርኛ


የተወደዳችሁ ወላጆች፣ ሞግዚቶች፣ ተማሪዎች እና ሰራተኞ፡-

ነገ፣ ጁን 15/2020 የ 2019-2020 የትምህርት ዓመት የሚያበቃበት ቀን ነው። እንዴት ከባድ አመት ነበር። ያለፉት ሦስት ወራት በማይታመንት ደረጃ ልዩ እና ከባድ ቢሆኑም፣ ማህበረሰባችን አስገራሚ ነገሮችን አከናውኗል። ስላደረጋችሁት አስደናቂ ሥራ፣ ትብብር፣ ለአሠራር አመቺ ሁኔታን መፍጠር እና ለመማር ማስተማር ስላሳያችሁት ትጋትና ጥረት አመሰብናለሁ።

መደበኛው የትምህርት ዓመት የተጠናቀቀ ቢሆንም፣ የሥራ ባልደረቦቻችን፣ ከማህበረሰቡ አባላት እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር፣ የሠመር ትምህርት ፕሮግራሞችን በማስጀመር እና አገር አቀፋዊ፣ የስቴት እና የአካባቢ የጤና  ሃላፊዎች በወቅቱ ባመኑበት መሠረት የፎል ትምህርት ወቅት ከመደበኛው የትምህርት አሠጣጥ በተለየ ሁኔታ መሆን እንዳለበት ስትራቴጂዎችን በማዘጋጀት ላይ ጠንክረው እየሠሩ ናቸው። ይህ በትብብር የሚሠራ ሥራ የሚመራው በምርምር፣ ተማሪዎች በሚያስፈልጓቸው ነገሮች እገዛ በማድረግ፣ እና ተማሪዎችን በግል በአካል እና በርቀት በመድረስ በርካታ የመማር ማስተማር ዘዴዎችን በመጠቀም ላይ ያተኩራል። በወረርሽኙ ወቅት የራሳችን ተሞክሮዎች እና የሌሎች የትምህርት ዲስትሪክቶች ተሞክሮዎችን፣ እንዲሁም በሜሪላንድ የትምህርት ማገገሚያ እቅድ ላይ በመመስረት፣ Maryland’s Recovery Plan for Education፣ የሚከተሉትን በእቅዳችን .ላይ መካተት እንዳለባቸው እናውቃለን፦

  • የተማሪዎችን እና የትምህርት ቤት ማህበረሰብን ተሳትፎ የማጠናከር ስትራቴጂዎችን ማሳደግ።
  • አካደሚያዊ ምጡቅነትን ማሳደግ።
  • ለተማሪዎች እና ለሠራተኞች በርካታ የተለያዩ አይነት ድጋፎችን መስጠት።
  • ለሠራተኞች ግላዊ እና ገቢራዊ የሙያ እድገትን ማዳበር።
  • ተማሪዎች እና ሠራተኞች ለርቀት ትምህርት፣ እና ለአካላዊ እና ጥምር የትምህርት ሞዴሎችን ለማስተማር እና ለመማር ዲጂታል መገልገያዎች እና የመገናኛ አውታር ተደራሽነት እንዳላቸው ማረጋገጥ፣ እና
  • ለማህበረሰባችን ወቅታዊ እና ተከታታይነት/ቀጣይነት ያለው የግንኙነት እና የግብረመልስ ሃሳቦችን የመለዋወጥ እድሎችን መስጠት።

ስለ ትምህርት ዲስትሪክታችን እንደገና የመከፈት እቅድ በርካታ ጥያቄዎች እንደሚኖሯችሁ እና አንዳንድ ትክክለኛ ያልሆኑ መረጃዎችን እንደምትሰሙ እናውቃለን። ስለፎል እቅድ ገና ምንም አይነት ውሳኔ ያልሰጠን መሆኑን ላረጋግጥላችሁ እፈልጋለሁ። ተማሪዎችን እና ሠራተኞችን ወደ ህንጻዎቻችን እንደገና ከመቀበላችን አስቀድመን ግልጽ የሆነ አቅጣጫ ስለሚሰጡን ስለጤንነት እና ደህንነት የሚወሰዱ እርምጃዎችን በሚመለከት ከስቴ እና የአካባቢ ኃላፊዎች ጋር በቅርበት መስራታችንን እንቀጥላለን።

ሰፊ እና ብዝሃነት ባለበት የትምህርት ዲስትሪክት፥ተማሪዎች ወደ ትምህርት ቤቶቻችን ህንጻዎች በሠላም እና በጤና መመለስ የሚችሉበትን እቅድ ለማዘጋጀት በተቻለ መጠን ከብዙ የማህበረሰባችን አባላት ለመስማት ቁርጠኞች ነን። በሚቀጥለው የትምህርት ዓመት ተማሪዎች እንዴት ትምህርት ላይ መሣተፍ እንዳለባቸው የእናንተን አስተያየት እና ምርጫ የመግለጽ እድል እንዲኖራችሁ በመጪዎቹ ሣምንታት ዳሰሳ እንጀምራለን። ከዳሰሳው በተጨማሪ፣ የማህበረሰብ አስተያየት ግብአቶችን ለማግኘት ሌሎች ዘዴዎችንም እንጠቀማለን። ማናችንም ባልገመትነው መንገድ የትምህርት ዓመቱ  የተጠናቀቀ ቢሆንንም፣ የሚቀጥለው የትምህርት ዓመት የሚጀመረው በተለመደው ሁኔታ ላይሆን ስለሚችል፣ በመጪዎቹ ወራት እንዴት በጋራ እንደምናከናውናቸው በተስፋ እጠብቃለሁ።

ከዚህ ቀጥሎ የስቴት መመሪያን ጨምሮ የካውንቲ አስተዳደር በ Phase II እንደገና የመክፈት እቅዶች፣ የሠመር ትምህርት ቤት ፕሮግራሞች፣ ከቤት ውጭ ሥፍራዎችን የማህበረሰብ አጠቃቀም፣ እና የአካላዊ ጤንነት ሪሶርሶች ስለ ተማሪ አእምሮአዊ ጤንነት መደገፍ በርካታ ወቅታዊ ጉዳዮች ተዘርዝረዋል።

ደስታ፣ ጤንነት እና እርፍት የሰፈነበት ሠመር እንዲሆንላችሁ እመኛለሁ።

ከአክብሮት ጋር

Jack R. Smith, Ph.D. 
Superintendent of Schools



የካውንቲ አስተዳደር መመሪያ መከተል

ጁን 10፣ የስቴት ትምህርት ቤቶች ሱፐርኢንተንደንት "Karen Salmon" እና "Governor Larry Hogan" ስለስቴት ሁለተኛ ምዕራፍ-Phase II ማገገሚያ የሽግግር መመሪያ ትእዛዝ ሰጥተዋል። የሆነ ሆኖ፣ የሞንትጎመሪ ካውንቲ እስካሁንም በመጀመሪያው ምዕራፍ-Phase I ላይ እንገኛለን። ከካውንቲው የሽግግር ምእራፍ በመቀጠል፣ MCPS አንዳንድ እንቅስቃሴዎችን እና ፕሮግራሞችን (ለምሳሌ፦ የመስክ አትሌቲክስ ልምምዶች፣ በአካል ተገኝቶ የምረቃ ስነ ስርአቶችን ማካሄድ፣ እና በአካል ተገኝቶ የሠመር ትምህርት ቤት ማካሄድ የመሣሰሉትን) ለመጀመር እንችል እንደሆነ ስለመወሰን ከአካባቢያችን የጤና ሃላፊዎች ጋር በቅርበት እየሠራን ነው። በተዘጋጀ ጊዜ በተቻለ ፍጥነት ወቅታዊ መረጃ እንሰጣለን።

በዚህ ጊዜ፣ የአመቱ የመዝጊያ ሂደት እየተካሄደ ባለበት ወቅት የ MCPS የህፃናት እንክብካቤ ፋሲሊቲዎች አይከፈቱም። የስቴት እና የአካባቢ የጤና መስፈርቶችን እየተከተልን፣MCPS እንዴት በጤናማ ሁኔታ የህፃናት እንክብካቤ ፋሲሊቲዎችን በቀጣይ ምእራፍ -next phase እንደገና ለመክፈት እና ለማካሄድ እንደሚቻል ውሳኔ ላይ ለመድረስ ከስቴት እና ከአካባቢያችን የጤና ሃላፊዎች ጋር በቅርበት እየሠራን ነው።


የሠመር ፕሮግራሞች

በተጨማሪም MCPS የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የክሬዲት ኮርሶችን ቨርቹወል የሠመር ትምህርት የኤለመንተሪ፣ የመካከለኛ እና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የተለያዩ በርካታ የሠመር ፕሮግራም ተሞክሮዎችን በኦንላይን ሞዴል ይሰጣል። የእነዚህ ፕሮግራሞች ግብ ተማሪዎች በሠመር ወራት በትምህርት ላይ እንዲጠመዱ እና እንዲሣተፉ ማድረግ፣ በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ወቅት ሳይማሩ ያለፋባቸውን ትምህርት ማካካስ፣ እና ለተማሪዎች የሚያስፈልጋቸውን በርካታ ልዩ- እድሎችን መስጠት ነው። ስለሠመር ፕሮግራሞች የእኛ ራዕይ በዚህ ሠመር የ MCPS ተማሪዎች በሙሉ በትምህርት ማበልፀግ ፕሮግራሞች የመሣተፍ እድል እንዲኖራቸው ማድረግ ነው። በአጠቃላይ፣ ከጁላይ 13 ጀምሮ፣ እንደየፕሮግራሞቹ ከአንድ እስከ ሦስት ሣምንት ይካሄዳል። ወላጆች በትምህርት ቤቶቻቸው የትኞቹ ፕሮግራሞች እንደሚገኙ በርእሰመምህር አማካይነት ይገለጽላቸዋል፣ እና ስለፕሮግራም ምዝገባ ዝርዝር ከአካባቢ ትምህርት ቤት ያገኛሉ። ጁን 23/2020 የምዝገባ መረቦቹ በየትምህርት ቤት ድረ-ገጾች ላይ ይገኛሉ። ስለ ሠመር ፕሮግራሞች ይበልጥ ለማወቅ፣ ይህንን ድረ-ገጽ ይጎብኙ


ሪፖርት ካርዶች

የኤለመንተሪ ሪፖርት ካርዶች
ሪፖርት ካርዶች ጁን 17/2020 ወደ ቤት በፖስታ ይላካሉ። የሪፖርት ካርዱ የመጀመሪያ፣ የሁለተኛ እና የሦስተኛ ማርክ መስጫ ክፍለጊዜዎችን ውጤቶች፣ እና የአጠቃላይ አማካይ ውጤት የያዘ ነው።

የሞንትጎመሪ ካውንቲ የትምህርት ቦርድ ስለ 2019-2020 የትምህርት ዓመት አራተኛው የማርክ ውጤት መስጫ ክፍለጊዜ ክለሳ የተደረገበትን የውጤት አሠጣጥ ፖሊሲ አፅድቋል። በኤለመንተሪ ደረጃ ለ 4ኛው የማርክ መስጫ ክፍለጊዜ በፊደል ማርክ አልተሰጠም። በዚህ ምክንያት፣ የእርስዎ ልጅ ሪፖርት ካርድ የ4ኛው ማርክ መስጫ ክፍለጊዜ ሠንጠረዥ ላይ ማርክ አይጻፍበትም። ከዚህ ቀጥሎ ያለው መግለጫ በእርስዎ ልጅ ሪፖርት ካርድ ላይ ይገኛል።

የሞንትጎመሪ ካውንቲ የትምህርት ቦርድ ለ 2019-20 የትምህርት ዓመት ክለሳ የተደረገበትን የውጤት አሠጣጥ ፖሊሲ አፅድቋል። በኤለመንተሪ ደረጃ ለ4ኛው የውጤት መስጫ ክፍለጊዜ ማርኮች በፊደል አልተሰጡም።
የሁለተኛ ደረጃ ሪፖርት ካርዶች
የሁለተኛ ደረጃ ሪፖርት ካርዶች ጁን 23/2020 በፖስታ የሚላኩ ሲሆን በትምህርት ቦርድ የፀደቀውን ክለሳ የተደረገ የውጤት አሰጣጥ ፖሊሲ ያንፀባርቃሉ። ለሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ክሬዲት የሴሚስተር ኮርሶች፣ የመጨረሻ ሴሚስተር ውጤት ለመምረጥ የቻሉ ተማሪዎች/ቤተሰቦች የፊደል ማርክ ወይም አልፏል-አልፋለች/አላጠናቀቀ(ች)ም (a letter grade or Pass/Incomplete)፣ በሪፖርት ካርዱ ላይ ይገለጻል። በ "online portal" ላይ ለመምረጥ ያልቻሉ ከሆነ ወይም የመረጡትን እንደገና ለማየት ከፈለጉ፣ እባክዎ የእርስዎን ልጅ ትምህርት ቤት ካውንስለር ያነጋግሩ።

ስለተማሪዎች እና ስለሠራተኞች የቴክኖሎጂ መገልገያ

የርቀት ትምህርት በተጀመረበት ወቅት Chromebooks እና MiFi መገልገያዎችን ያገኙ ተማሪዎች የሠመር ቀጣይ ትምህርታቸውን ለመከታተል እነዚያኑ ዲቫይሶች ለሠመር የመማር - ማስተማር እድሎች መጠቀም ይችላሉ። በሠመር ፕሮግራሞች የሚሳተፉ ተማሪዎች device ወይም mobile hotspot የሚፈልጉ ከሆነ፣ ወይም የተበላሸ-የማይሠራ device ለመቀየር ከፈለጉ ከሰኞ እስከ ዓርብ 10 a.m.–12 p.m ወደ 45 W. Gude Dr in Rockville ለመሄድ ይችላሉ። የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ስለ 2020–2021 የትምህርት ዓመት ስናስብ፣ ከተማሪዎች፣ ከወላጆች፣ ከመምህራን እና ከ ርእሰመምህራን በተገኘ ግብረመልስ በመመርኮዝ፣ (myMCPS Classroom) የተሰኘ ተናጠል የመማር- ማስተማር ትምህርት ገበታ-single platform እያቀድን መሆናችንን እንዲገነዘቡ እንፈልጋለን። በሚመጡት ሣምንቶች ስለዚህ እቅድ ዝርዝር ይገለጻል።


የትምህርት ቦርድ ለ2021 የባጀት ዓመት $2.76 ቢሊዮን የሥራ ማስኬጃ ባጀት አጽድቋል።

የትምህርት ቦርድ ለ2021 የባጀት ዓመት (FY) $2.76 ቢሊዮን የሥራ ማስኬጃ ባጀት ያፀደቀው ጁን 11 ነው። ባጀቱ ከአሁኑ የባጀት ዓመት የሥራ ማስኬጃ በጀት ጋር ሲነፃጸር የ $74.9 ሚሊዮን ወይም 2.8 ፐርሰንት ጭማሪ አለው። ይህ የባጀት ምደባ በኮቪድ-19 ወረርሽኝ (COVID-19 pandemic) ምክንያት ኢኮኖሚ ስለተቀዛቀዘ የካውንቲ ካውንስሉ የትምህርት ዲስትሪክቱን በስቴት ህግ መሠረት ከሚጠበቀው አነስተኛ መጠን መወሰኑን ያመለክታል። ባጀቱ የቀጣይ ትምህርት እቅድን እና የተመዝጋቢዎች ብዛት መጨመርን፣ የዋጋ ጭማሪ እና በ MCPS አቅማቸውን በመጠቀም ስኬታማ ለመሆን የሚፈልጉ ተማሪዎች ሊኖራቸው የሚገባ የተደራሽነት፣ እና የስኬት ክፍተቶችን፣ ለማጥበብ ስለማገዝ ያለንን ከፍተኛ ፍላጎት እና ለአካደሚያዊ ምጡቅነት የሚያስፈልጉ ኢንቨስትመንቶችን ያካትታል። ስለባጀት ይበልጥ ለማወቅ እዚህ ይመልከቱ።


ከቤት ውጭ የማህበረሰብ ቦታዎች አጠቃቀም

ከረቡዕ፣ ጁላይ 1 ጀምሮ የ MCPS ከቤት ውጭ ቦታዎች ለህዝብ አገልግሎት ክፍት ይሆናሉ። ከቤት ውጭ ሥፍራዎች አጠቃቀም እና ተመዝግቦ ቦታ የመያዝ አሠራር Community Use of Public Facilities-በህዝብ ንብረት ላይ የማህበረሰብ አጠቃቀም ስርአትን ይከተላል። ከስቴት እና ከካውንቲ እንቅስቃሴ መመሪያዎች ጋር የሚጣጣም ይሆናል። ከቤት ውጭ ቦታዎች አጠቃቀም ጅምናዚየሞችን-gyms፣ የሣጥን መቆለፊያ ክፍሎችን-locker rooms ወይም ሌላ የቤት ውስጥ አትሌቲክ ፋሲሊቲዎችን አይጨምርም። MCPS ስለ ቤት ውስጥ የማህበረሰብ መጠቀሚያዎችን የሚፈቀድበትን ጊዜ ለመወሰን የህዝብ ጤንነት መመሪያዎችን ይከተላል። የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መተላለፊያ መንገዶች ለህዝብ የእግር ጉዞ መናፈሻነት ከጁን 15 ጀምሮ ክፍት ይሆናሉ። መስኮች እስከ ጁላይ 1 ተዘግተው የሚቆዩ ሲሆን የማህበረሰብ ፋሲሊቲዎችን የመጠቀም ፈቃድ አሰጣጥ ሒደትን በመከተል ብቻ ፈቃድ ለማግኘት ይቻላል።


የጤና እንቅስቃሴ ሪሶርሶች

የተማሪዎቻችን ጤንነት እና ደህንነት ሁልጊዜም ቀዳሚ ትኩረታችን ይሆናል። ከዚህ ቀጥሎ የሚገኙት የማህበረሰባችንን አካላዊ፣ ማህበራዊ እና ስነልቦናዊ ደህንነት ለመደገፍ የሚረዱ ሪሶርሶች ናቸው። የእርስዎ ልጅ ቀውስ ውስጥ ገብቷል/ገብታለች ብለው የሚያምኑ ከሆነ፣ እባክዎ የሞንትጎመሪ ካውንቲ የከባድ ችግር-ቀውስ ማእከልን "Montgomery County Crisis Center" በስልክ ቁጥር 240-777-4000 ያነጋግሩ። ተማሪዎችም ካውንስለሮቻቸውን እና የትምህርት ቤት ሳይኮሎጂስቶችን በምስጢር ቀጠሮ ይዘው ሊያገኟቸው ይችላሉ።

Waymaking Video Series - በቅደምተከተል የሚቀርብ-ቪድኦ

ራስን ስለማጥፋት ግንዛቤ
ስለ ተማሪዎች ጭንቀት እና ፍርሃት አያያዝ
በማህበራዊ መራራቅ ወቅት የሚያጋጥም ጭንቀት እና ፍርሃት አያያዝ
መስተዋል ያለባቸው ጊዜያት የቪድኦ ቅደምተከተሎች-Mindful Moments Video Series
የተማሪ ሀዘንን ለመቅረፍ የሚረዱ ፍንጮች-Tips on Addressing Student Grief
ስለ ወጣት ራስን ማጥፋት መከላከል የሚረዱ ፍንጮች- Tips for Preventing Youth Suicide


የሠመር የምግብ አገልግሎት ፕሮግራም ለውጦች

ማክሰኞ፣ ጁን 16 ጀምሮ የትምህርት ቤት፣ የአውቶቡስ እና ተንቀሳቃሽ የምግብ ጣቢያዎች የአገልግሎት ሠዓቶች ይለወጣል። ተማሪዎች የቁርስ፣ የምሣ እና እራት ምግቦችን ከትምህርት ቤት እና ከተንቀሳቃሽ ማጓጓዣ 10 a.m. to 12 p.m. መውሰድ ይችላሉ። በአውቶቡስ ስርጭቱ ከ 9 a.m. እስከ 10 a.m. ይካሄዳል። የጣቢያዎቹን ሙሉ ዝርዝር ከድረ-ገጽ ይመልከቱ።


ሁላችን በአንድ ላይ፦ የ2020 ተመራቂዎች የዚህን አዳጋችና አስቸጋሪ ዓመት ስሜታቸውን ያጋራሉ

በቅርቡ All In-ሁሉም በአንድነት በ Dr. Smith ጦማር ከ2020 ተመራቂዎች የተሰጡ አስተያየቶች ተገልፀዋል። ፖስት የተደረገውን ጦማር እዚህ ይመለከቷል። ምናልባት ያመለጠዎት ከሆነ፣ እዚህ ሊመለከቱ ይችላሉ MCPS Graduates 2020፣ በ Chef Jose Andres ዋነኛ ተናጋሪነት የእኛን የ 2020 ተመራቂዎች ቨርቹወል የምረቃ ስነስርአት ሊመለከቱ ይችላሉ። እያንዳንዱን የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የምረቃ ስነስርአቶች እዚህ መመልከት ይችላሉ።


ለተመራቂዎቻችን አክብሮት መስጠት

የ2020 ተመራቂዎች ልዩ የስፓንሽ ቨርቹወል የምረቃ ሥርዓት-special Spanish virtual commencement celebration ለሚካሄድበት ቀን ቀጠሮ ይያዙ። ይህ ሁነት ጁን 20 6 p.m. ላይ በ Telemundo 44 የሚካሄድ ሲሆን በ MCPSTV en Español YouTube ቻነል እና በ MCPS ድረ-ገጽ ይተላለፋል።  ከ NBC ጋር በመተባበር የተዘጋጀው ሁነት፣ "Mario Lopez, chef José Andrés, Montgomery County councilmember Nancy Navarro, and grammy-nominated singer Verny Varela" የመሣሰሉ ታዋቂና ዝነኛ ግለሰቦች እና ተመራጭ ባለሥልጣኖችን አስተያየቶችን ያካትታል።  በተጨማሪም ከ2020 ተመራቂዎች አስተያየቶቻቸውን ያካትታል። የምረቃ ስነስርአቱ በቴለሙንዶ መልህቅ አማካይነት-Telemundo anchor Alban Zamora አስተናጋጅነት-አስተዋዋቂነት ይካሄዳል።  የ "Hispanic and Latinx" ተማሪዎቻችንን አስደሳች የምረቃ ሥነስርአት እንደምትከታተሉ ተስፋ እናደርጋለን።


Important Online Resources: