የትምህርት ቦርድ የ 2023 ዓ.ም ካፒታል በጀት እና ከ 2023-2028 የካፒታል ማሻሻያዎች ፕሮግራም በድምሩ $1.767 ቢሊዮን ዶላር አፀደቀ።

November 19, 2021

ለተከበራችሁ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ማህበረሰብ፦

የሞንትጎመሪ ካውንቲ የትምህርት ቦርድ ለ 2023–2028 የካፒታል ማሻሻያ ፕሮግራም የ $1.767 ቢሊዮን ዶላር ጥያቄ እና የ 2023 በጀት ዓመት የካፒታል በጀት ተግባር ላይ የሚውል የበጀት ጥያቄ በድምሩ $551.289 ሚሊዮን ዶላር በአንድ ድምፅ አጽድቋል።

የ $1.767 ቢሊዮን ዶላር ሪኮመንዴሽን ቀደም ሲል ከፀደቀው CIP የ $148.3 ሚሊዮን ዶላር ብልጫ አለው ማለት ነው።

የስድስት ዓመቱ እቅድ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስን (MCPS) መገልገያዎች/ፋሲሊቲ፣ አቅም እና የመሠረተ ልማት ፍላጎቶችን ይመለከታል። ጁላይ 1፣ 2022 ተጀምሮ ጁን 30፣ 2023 የሚያበቃውን የበጀት ዓመት የ CIP ን ተግባር ለማከናወን የተጠየቀውን የ 2023 በጀት ዓመት የካፒታል በጀት ፈንድ የመጠቀም ፈቃድና ለ 2023-2028 ወጪ የሚደረጉ እቅዶችን/ሪኮመንዴሽኖችን ያካትታል።

ጊዜያዊ ሱፐርኢንቴንደንት ሞኒፋ ማክኒት (Interim Superintendent Monifa McKnight) “ተማሪዎች ደህንነቱ የተጠበቀ እና ሳይሳቀቁ ተመችቷቸው የሚማሩበት ቦታ እንዲኖራቸው ለማድረግ MCPS የአቅም ግንባታ እና ያረጁ መሠረተ ልማቶችን ማሻሻል መቀጠል ይኖርበታል ብለዋል።

የኮቪድ-19 ተፅዕኖ፦ በወረርሽኙ ምክንያት የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪው የቁሳቁስ ዋጋ ጨምሯል፣ የአቅርቦት ሰንሰለት መስተጓጎል እና የሰው ሃይል እጥረት፣ በግንባታ ወጪ ላይ ከፍተኛ ጭማሪ አስከትሏል። እነዚህ ያልተጠበቁ ሁኔታዎች በብዙ የካፒታል ፕሮጀክቶች ላይ በታቀዱ ወጪዎች እና በተጨባጭ የበጀት ወጪዎች መካከል ከፍተኛ የገንዘብ እጥረት ፈጥረዋል። ቀደም ሲል የፀደቁትን የማጠናቀቂያ ቀናት ለመጠበቅ ጠቅላላ የፕሮጀክት ወጪዎቹ ጨምረዋል።

ምዝገባ ይጨምራል ተብሎ ይጠበቃል፦ MCPS ከ 2007-2008 የትምህርት ዓመት ጀምሮ በተከታታይ የተማሪ ምዝገባ እድገት አይቷል። ነገር ግን በወረርሽኙ ምክንያት በተማሪዎች ምዝገባ ላይ ተፅዕኖ አሳድሯል። ለበጀት ዓመት 2022 ቀደም ሲል የተካሄደው የሰፕቴምበር 30 ምዝገባ 158,232 ሲሆን ይህም በበጀት ዓመት 2021 ተመዝግበው ከነበሩት 160,564 የተማሪዎች ቁጥር በአንድ አመት 2,332 የተማሪዎች ቁጥር ቀንሷል ማለት ነው። በ 2027-2028 የትምህርት ዓመት አጠቃላይ ምዝገባ ወደ 166,160 የተማሪዎች ቁጥር እንደሚጨምር ይጠበቃል። ማንኛውም ምዝገባ ሲቀንስ ሁኔታው ጊዜያዊ ስለሚሆን፣ ቀደም ሲል በታቀደው CIP የፀደቁት የአቅም ግንባታ ፕሮጀክቶች በታቀደላቸው መርሃ ግብሮች መሠረት መቀጠል አለባቸው።

አጠቃላይ ፍንጮች፦ በ CIP ውስጥ የተካተቱትን ሁሉንም የካፒታል ፕሮጀክቶች የማጠናቀቂያ ቀናት እና እንዲሁም ለሚከተሉት ተጨማሪ የገንዘብ ድጋፍ በፀደቀው መሠረት ይቀጥላል፦

  • የናረ የግንባታ ወጪዎችን እና የሥራ ዋጋ/ዌጅ መጠን የተንፀባረቀባቸው ከዚህ ቀደም የፀደቁ ሰባት ፕሮጀክቶች፣
  • በበርተንስቪል እና በግሪንካስል (Burtonsville and Greencastle) የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤቶች አዲስ ትምህርት ቤት መጨመሪያ ፕሮጀክቶች፣
  • በፓይኒ ብራንች አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እና ኢስተርን መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት (Piney Branch Elementary School and Eastern Middle School) ለዋና ፕሮጀክቶች የፕላን ዝግጅት ገንዘብ፣ እና
  • የካውንቲ አቀፍ መሠረተ ልማት እና ፕሮጀክቶች ያረጁ መሠረተ ልማቶችን የማስተካከል ሥርዓት አቀፍ ተነሳሽነት።

በተጨማሪም፣ ለሱፐርኢንተንደንት  የቀረቡ በ 2023 ካፒታል በጀት እና በ 2023-2028 የካፒታል ማሻሻያ መርሃ ግብር መካተት ያለባቸው ሁለት የማካለል ጥናት ማሟያዎች፦

በ CIP የተመከረበት ስለ አዲሱ ክላርክስበርግ ክላስተር አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት #9 የአገልግሎት ክልል ለመፍጠር አንድ አዲስ የማካለል ጥናት ያካትታል። የማካለል ጥናቱ የሚካሄደው በ 2022 የስፕሪንግ ወቅት ሲሆን ቦርድ እርምጃ የሚወስደው በኖቬምበር 2022 ይሆናል። አዲሱ የክላርክስበርግ ክላስተር አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት #9 (Clarksburg Cluster Elementary School #9) በኦገስት 2023 ይከፈታል።

የጊዜ ማእቀፍ፦ ከሱፐርኢንተንደንት የቀረበው የ 2023 ዓ.ም የካፒታል በጀት እና የ 2023-2028 የካፒታል ማሻሻያ መርሃ ግብር ለቦርዱ ኦክቶበር 25 ቀርቧል። ቦርዱ በኦክቶበር 28 የስራ ክፍለ ጊዜ የቀረበውን ከተመለከተ በኋላ የማህበረሰብ ተሳታፊዎች በተገኙበት ኖቨምበር 2፣ 4፣ እና 8 ቀርቧል።

 

 

Montgomery County Public Schools
የሞንጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ



Email us: ASKMCPS@mcpsmd.org

Montgomery County Public Schools