ቦርዱ በ 2021-2022 የትምህርት ዓመት ካላንደር ላይ ማሻሻያዎችን አጽድቋል

December 2, 2021

በዲሴምበር 2 የቢዝነስ ስብሰባ፣ የሞንትጎመሪ ካውንቲ የትምህርት ቦርድ ለቀሪው 2021-2022 የትምህርት ዓመት የቀን መቁጠሪያ ማሻሻያ አጽድቋል።

የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) በየእለቱ ለተማሪዎች ትርጉም ያለው እና አሳታፊ ትምህርቶችን ለማዘጋጀት ለአስተማሪዎች እቅድ የማዘጋጀት ጊዜ ወሳኝ መሆኑን ይገነዘባል። ይህንን ለመደገፍ፣ ለሰራተኞች አስፈላጊ የስራ ጊዜ ለማመቻቸት እንዲቻል ሶስት በቅድሚያ የመልቀቂያ ቀናት በዚህ የትምህርት አመት የቀን መቁጠሪያ ላይ ተጨምረዋል። በዚህ መሠረት እሮብ፣ ጃኑወሪ 12፣ ሐሙስ ማርች 24፣ እና እሮብ፣ ሜይ 18፣ 2022 ለመደበኛ እና ኢኖቬቲቭ ካላንደር ትምህርት ቤቶች በቅድሚያ የሚለቀቁበት ቀናት ናቸው። የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ቀደም ባሉት ጊዜያት ከትምህርት ሰአት በኋላ ለተማሪዎች አሳታፊ ተግባራትን ከትምህርት-ቤት-ሠዓት ውጪ የተለያዩ እድሎችን ከማህበረሰብ አጋሮች ጋር ለማመቻቸት እየሞከረ ይገኛል።

ዲስትሪክቱ በተጨማሪም በዊንተር ዕረፍት ወቅት ዲሴምበር 23 እና ዲሴምበር 27 እስከ ዲሴምበር 30፣ 2021በስፕሪንግ ዕረፍት ወቅት ኤፕሪል 13 እና ኤፕሪል 14፣ 2022 ዲስትሪክት አቀፍ ዝግ እንደሚሆን ተወስኗል። የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ፋሲሊቲዎች በ “Montgomery County Community Use of Public Facilities (CUPF)” ፅህፈት ቤት አማካይነት ለህጻናት እንክብካቤ እና የመሣሰሉትን ሌሎች የህዝብ አገልግሎት ዝግጅቶ ለማካሄድ ክፍት ይሆናሉ።

"Juneteenth" ከፌዴራል እና የክልል በዓላት ጋር በማጣመር ሰኞ፣ ጁን 20/2022 የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ስርዓት አቀፍ ይዘጋል

እነዚህ ለውጦች የተደረጉት የ 181 የትምህርት ቀናትን እና ሰኔ 15/2022 የመጨረሻውን የትምህርት ቀን ያካተቱና ያገናዘቡ ናቸው። በዚህም የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) በስቴቱ ከሚፈለገው ዝቅተኛው የትምህርት ሰአታት እንደሚበልጥ ልብ ማለት ያስፈልጋል። በኤለመንተሪ ትምህርት ቤት ደረጃ፣ MCPS ከሚፈለገው ዝቅተኛው የትምህርት ሰአታት ብዛት ከ 60 ሰዓት በላይ ያልፋል። በመካከለኛ ት/ቤት ደረጃ፣ MCPS የሚፈለገውን ዝቅተኛውን የትምህርት ሰአታት ከ120 ሰዓት በላይ ያልፋል። እንዲሁም በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የሚፈለገውን ዝቅተኛውን የትምህርት ሰአት ብዛት MCPS ከ 30 ሰዓት በላይ ያልፋል።



Email us: ASKMCPS@mcpsmd.org

Montgomery County Public Schools