December 7, 2021
ለተከበራችሁ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ማህበረሰብ፦
ማሳሰቢያ፦ በከባድ የአየር ሁኔታዎች እና ሌሎች ድንገተኛ አደጋዎች ምክንያት የትምህርት ቤት ቀናት መሰረዛቸውን፣ መዘግየታቸውን ወይም ቀደም ብለው ሲዘጉ መረጃዎች/መግለጫዎች የሚለጠፉባቸው ቦታዎች የሚከተሉት ናቸው።
ሁሉም ማስታወቂያዎች በተቻለ መጠን ከባድ የአየር ሁኔታ በተፈጠረበት ቀን ወይም ምሽት ላይ በቅድሚያ ይገለፃሉ። የሳምንቱ መጨረሻ (Weekend) የህዝብ መገልገያዎችን ስለመጠቀም ውሳኔዎች በካውንቲው የኤጀንሲዎች አስተባባሪ ቦርድ (Interagency Coordinating Board) አማካይነት የሚሰጡ ሲሆን ውሳኔዎቹ በተመሳሳይ የሚዲያ መስመሮች ይገለጻሉ።
ዝግ የሚሆኑ ትምህርት ቤቶች፣ ዘግይተው የሚከፈቱ፣ እና ቀደም ብሎ የሚዘጉ ስለሚለው መግለጫ ፕሮቶኮል እነሆ።
የሚዘጉ ትምህርት ቤቶች፡ ትምህርት ቤቶች ሲዘጉ፣ የአትሌቲክስ ልምምዶችን እና ዝግጅቶችን ጨምሮ ሁሉም የትምህርት ቤት እና የማህበረሰብ እንቅስቃሴዎች ይሰረዛሉ። በትምህርት ቤቶች ውስጥ የሚካሄዱ የግል ዴይኬር እንክብካቤ ሰጪዎች የአስተዳደር ቢሮዎች ክፍት ከሆኑ - ክፍት ሆነው መቆየትን/መቀጠልን ሊመርጡ ይችላሉ። ነገር ግን በአስቸጋሪ ሁኔታዎች ወቅት የአስተዳደር ቢሮዎች ሊዘጉ ይችላሉ።
ዘግይተው የሚከፈቱ፡ ትምህርት ቤቶች ለሁለት ሰዓታት ዘግይተው ሊከፈቱ ይችላሉ፣ እና የአውቶብስ መጓጓዣን ጨምሮ ሁሉም ስራዎች ከመደበኛ መርሃ ግብሩ በሁለት ሰአት ይዘገያሉ። የማለዳ ኪንደርጋርደን፣ Head Start፣ EEEP ክፍሎች፣ ሌሎች የህጻናት ፕሮግራሞች እና የመስክ ጉዞዎች ይሰረዛሉ። በ 10፡30 a.m. ወይም ከዚያ በፊት የሚጀምሩ ሌሎች ተግባራት እና ፕሮግራሞች (እንደ ቶማስ ኤዲሰን ከፍተኛ የቴክኖሎጂ ትምህርት ቤት የመሳሰሉት) እንዲሁ ይሰረዛሉ።
ቀደም ብሎ መዘጋት፡ ትምህርት ቤቶች በሁለት ተኩል (2.5) ሰአታት ቀደም ብለው ሊዘጉ ይችላሉ፣ እና የአውቶቡስ ትራንስፖርትን ጨምሮ ተማሪዎችን ማሰናበት የመሣሰሉ ስራዎች በሙሉ ከመደበኛው የትምህርት ቤት መዝጊያ ጊዜ በሁለት ሠዓት ተኩል (2.5) ቀደም ብለው ተግባራዊ ይሆናሉ። የከሰአት በኋላ ኪንደርጋርደን፣ Head Start፣ EEEP ክፍሎች እና ሌሎች የልጆች ፕሮግራሞች ይሠረዛሉ። የከሰአት እና የማታ የትምህርት ቤት እና የማህበረሰብ እንቅስቃሴዎች ይሠረዛሉ።
ጠቃሚ ሊንኮች፦
የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ
Montgomery County Public Schools
Email us: ASKMCPS@mcpsmd.org