ከሐሙስ ፌብሩዋሪ 17 መልእክት መታወቅ ያለባቸው ነገሮች

ለዛሬ፣ ሐሙስ፣ ፌብሩዋሪ 17፣ መታወቅ የሚገባቸው ሰባት ጉዳዮችን እነሆ! እነርሱም የቀረበው የ 2023 በጀት ዓመት የስራ ማስኬጃ በጀት ላይ የተደረጉ ማሻሻያዎችን፣ ስለ ኮቪድ-19 ፈጣን መመርመሪያ መሳሪያዎች መረጃ፣ መጥፎ የአየር ሁኔታ የማካካሻ ዕቅዶች፣ የደህንነት እና ማህበራዊ-ስሜታዊ ድጋፎች እና ሌሎችንም ያካትታሉ።

  1. በ 2023 በጀት ዓመት የሥራ ማስኬጃ በጀት ላይ ስልታዊ የባጀት ጭማሪን በተመለከተ በትምህርት ቦርድ ውይይት ተደርጓል

ፌብሩዋሪ 14፤ስለ በጀት ዓመት 2023 የሚከተሉትን ያካተተ የሥራ ማስኬጃ በጀት ለትምህርት ቦርድ ቀርቧል።

    • ተጨማሪ ኢንቨስትመንቶች የ ትምህርት ቤቶችን ደህንነት ለመደገፍ፤
    • ቴሌ የጤና አገልግሎቶችን ጨምሮ ለተማሪዎች እና ለሰራተኞች ማህበራዊ-ስሜታዊ ደህንነት እና የአእምሮ ጤና ድጋፍ ለመስጠት፣
    • የግንኙነት እና የማህበረሰብ ተሳትፎ ለማሻሻል፣
    • እና ሌሎች ጉዳዮችንም ያካትታል።

ውይይቱን በኦንላይን ማየት እና አቀራረቡን መገምገም ይችላሉ። እነዚህ ኢንቨስትመንቶች ከ... ድጋፍ ይኖራቸዋል።

  1. አሁንም በ MCPS ትምህርት ቤቶች እና ቢሮዎች ጭምብል/ማስክ ማድረግ አስፈላጊ ነው

ምንም እንኳን ሞንትጎመሪ ካውንቲ የጭንብል መጠቀም መመሪያ ከፌብሩዋሪ 21 በኋላ ሊያነሳ ቢችልም MCPS በአሁኑ ጊዜ ለተማሪዎች እና ለሰራተኞች ጭምብል/ማስክ የመጠቀም ግዴታ እንደጠበቀ ነው። የትምህርት ስርዓቱ በመጪዎቹ ቀናት በዚህ መመሪያ ላይ ስለሚደረጉ ለውጦች ያሉትን መረጃዎች በሙሉ ይገመግማል፥ እና ከአካባቢው የጤና ባለስልጣናት ጋር ምክክር ያደርጋል። ማንኛውም በመመሪያው ላይ የተደረጉ ለውጦች ወዲያውኑ ይገለጻሉ።

  1.  የኮቪድ-19 በቤት ውስጥ ፈጣን መመርመሪያዎች እየተከፋፈሉ ነው።

MCPS በየ3 ሳምንቱ እስከ ማርች ወር ድረስ ፈጣን የመመርመርያ ዕቃዎችን ለሁሉም ተማሪዎች እና ሰራተኞች ማከፋፈሉን ቀጥሏል። እነዚህ መሳሪያዎች የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት እየተደረጉ ላሉት ጥረቶች ወሳኝ ናቸው።
ቪዲዮ፦ የኮቪድ-19 ፈጣን መመርመሪያ ኪት አጠቃቀም መመሪያ
ሰራተኞች እና የተማሪ ወላጆች ፖዚቲቭ የምርመራ ውጤቶችን በ MCPS የኮቪድ-19 ሪፖርት ማድረጊያ ላይ ሪፖርት እንዲያደርጉ እናሳስባለን። (ማሳሰቢያ፦ እነዚህ የአፍንጫ ፈሳሽ ፈጣን መመርመሪያ ናቸው። እባክዎ ከመጠቀምዎ በፊት በመመርመሪያዎቹ ውስጥ የተካተቱትን መግለጫዎች ይመልከቱ)
4. ተጨማሪ የአየር ሁኔታ ቀን የትምህርት ማካካሻ እቅድ በሚቀጥለው ሳምንት ይለቀቃል
ጃኑወሪ 3፣ 4፣ 7 እና 20 በአስቸጋሪ የአየር ሁኔታ ምክንያት MCPS ትምህርት ቤቶችን ዘግቷል፣ ይህ ማለት እሮብ፣ ኖቬምበር 24፣ 2021 ስርአት አቀፍ የት/ቤት መዘጋት በተጨማሪ ነውህ መዘጋት ማለት MCPS ይህንን ለማሟላት ሶስት የትምህርት ቀናትን መመደብ አለበት ማለት ነው። 180 የትምርት ቀናት ማሟላት ስለሚያስፈልግ. ቀኖቹን የማካካሻ እቅድ በሚቀጥለው ሳምንት ለቤተሰቦች ይላካል።

  1. ስለ ሠላም እና ደህንነት የወላጅ ድምጽ የሚደመጥባቸው መድረኮች

በሁሉም የ MCPS ትምህርት ቤቶች ቀጣይነት ያለው የሠላም እና ደህንነት ግምገማ አካል በመሆኑ፣ የዲስትሪክቱ ሰራተኞች በሚቀጥሉት ሳምንታት ከተለያዩ የትምህርት ቤት ማህበረሰቦች በወላጅ ፍላጎት መድረኮች ላይ ወላጆችን ያሳትፋሉ።
ንግግሮቹ የሚከተሉትን ያካትታሉ:

    • የአእምሮ ጤና እና ማህበራዊ-ስሜታዊ ደህንነት
    • ደህንነቱ የተጠበቀ እና ፍትሃዊ የትምህርት ቤት አካባቢን መጠበቅ
    • የሠላም፣ የደህንነት እና የማህበረሰብ ተሳትፎ ኦፊሰር ፕሮግራም ማሻሻያዎች

መድረኮቹ ሲዘጋጁ ተጨማሪ መረጃዎችን እናጋራለን። ስለ ስራው የበለጠ ግንዛቤ ያግኙ።

  1. በቅርቡ ስለሚመጣ የፀረ-ዘረኝነት ኦዲት ዳሰሳ ማሳሰቢያ

ከ 4ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ያሉ ተማሪዎች ሁሉም ከማርች 1 እስከ ማርች 31 ባለው ጊዜ ውስጥ በትምህርት ቤት ከዕድሜአቸው ጋር የሚመጥን ማንነታቸውን ይፋ በማይደረግ የዳሰሳ ጥናት ይሳተፋሉ። እያንዳንዱ ትምህርት ቤት የዳሰሳ ጥናቱ የሚካሄድበትን ቀን ይወስናል።

በተደጋጋሚ የሚነሱ ጥያቄዎች (español / 中文 / français / Português / 한국어 / tiếng Việt / አማርኛ)

  1. በዚህ ወቅት ወደ 10 ቀን ቨርቹወል የትምህርት ጊዜ የተሸጋገሩ የ MCPS ትምህርት ቤቶች የሉም

ማናቸውም ትምህርት ቤቶች በሚቀጥለው ሳምንት ወደ ቨርቹወል ትምህርት አይሸጋገሩም። MCPS ኮቪድ-19 በት/ቤት ስራዎች እና በአካል በመማር ላይ የሚያስከትለውን ተፅእኖ መከታተል እና አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ በጊዜያዊነት ወደ ቨርቹወል ትምህርት መሸጋገር ያለባቸውን ትምህርት ቤቶች መለየታችን ይቀጥላል።



Email us: ASKMCPS@mcpsmd.org

Montgomery County Public Schools