የተማሪዎች ደህንነት ድስትሪክቱ ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ ነው። ወረርሽኙ በተከሰተበት ወቅት እና በዚህ የትምህርት ዓመት የተማሪዎችን የአእምሮ ጤንነት ፍላጎቶችን ለመደገፍ ተጨማሪ ጥረት የማድረግ አስፈላጊነት በጣም አሳሳቢ እየሆነ መጥቷል። ተማሪዎች በአካል፣ በአእምሮ እና በመንፈስ ጤነኛ ሲሆኑ፣ በትምህርት የተሻለ እንደሚሠሩ እናውቃለን።
MCPS ትምህርት ቤቶች ጤናማ የደህንነት ቁመና ባህልን ለማዳበር እና በችግር ውስጥ ላሉት ውጤታማ ምላሽ ለመስጠት የሚያስችሉ ግብዓቶች እና ፕሮግራሞች እንዲኖራቸው ለማድረግ ቁርጠኛ ነው።ትምህርት ቤቶች ለተማሪዎች ከፍተኛ ፍላጎት ያላቸውን ሁኔታዎች በመለየት መርዳት እንዲያስችላቸው የተማሪ ዳሰሳ ጥናት ተዘጋጅቷል።
ከመዋዕለ ሕፃናት እስከ 11ኛ ክፍል ያሉ ሁሉም ተማሪዎች ከሜይ 26 እስከ ጁን 17 ባለው ጊዜ ውስጥ ስለ ደህንነታቸው አስተያየቶችን ለመሰብሰብ ከእድሜ ጋር የሚስማማ ዳሰሳ ይወስዳሉ።
ማንኛውም ወላጅ ልጃቸው የዳሰሳ ጥናቱን እንዲወስድ የማይፈልጉ ከሆነ ይህንን ካልፈለጉ የመውጫ ቅጽ እስከ ሜይ 25 ሞልተው ማቅረብ አለባቸው።
ናሙና የዳሰሳ ጥናት ጥያቄዎች እዚህ ይገኛሉ።
የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ
Montgomery County Public Schools
Email us: ASKMCPS@mcpsmd.org