ከሞንትጎመሪ ካውንቲ የትምህርት ቦርድ እና ሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ በቴክሳስ ትምህርት ቤት ስለተፈጠረው ክስተት የተሰጠ መግለጫ

May 24, 2022

ውድ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ማህበረሰብ፦

በሞንትጎመሪ ካውንቲ የትምህርት ቦርድ እና በሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ ስም በኡቫልዴ ቴክሳስ፣ሮብ አንደኛ ደረጃ ት/ቤት ውስጥ (Robb Elementary School in Uvalde, Texas) በደረሰው ትርጉም የለሽ እና አሳዛኝ የህይወት መጥፋት እናዝናለን። ብጥብጥ በማንኛውም መልኩ መታገሥ የማንችለው ክስተት ነው።በልጆች ላይ እና እነርሱን ለማስተማር፣ ለማገልገል እና ለመጠበቅ በተጠሩት ላይ የሚፈጸም ጥቃት፣ ደህንነታቸው በጣም መጠበቅ ባለበት ቦታ ላይ የሚደርሰውን ጥቃት መታገስ/መቋቋም አይቻልም። ትርጉም የለሽ የጠመንጃ ጥቃትን ለማስቆም እና መላው የትምህርት ቤቶቻችን ማህበረሰቦች ሠላም እና ደህንነታቸውን ለማስጠበቅ ዛሬ ልጆቻችንን በእቅፋችን ይዘን ያለንን የማያወላዳ ቁርጠኝነታችንን ማረጋገጥ እንወዳለን። ሁላችንም አብረን በጋራ የሁሉንም ተማሪዎች እና ሰራተኞች ደህንነት እና ሠላም ለመጠበቅ ቁርጠኞች ነን። ሰላማችንን የሰረቀውንና የወጣቶችን እና የንጹሃንን ህይወት የቀጠፈ ሁከት ለማስቆም እያንዳንዳችን መወጣት ያለብን ሚናና ድርሻ አለን።

የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ



Email us: ASKMCPS@mcpsmd.org

Montgomery County Public Schools