ለተከበራችሁ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ማህበረሰብ፦
ሰኞ፣ ሜይ 30 የሜሞሪያል ቀን እናከብራለን። ትምህርት ቤቶች እና ቢሮዎች ይዘጋሉ።
በዚህ ቀን፣ ለነፃነታችን የመጨረሻውን መስዋዕትነት የከፈሉትን የ ዩ. ኤስ አገልግሎት አባላት እናከብራለን፣ እናስታውሳቸዋለን፣ እና ለወዳጅ ዘመዶቻቸው ልባዊ አድናቆታችንን እናቀርባለን። ቤተሰብ ወይም ጓደኞቻቸውን ያጡ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ ማህበረሰብ አባላት አሉ። ለእነርሱ ሀዘናችንን እንገልፃለን።
MCPS እና የጤና ጥበቃ እና የሰብአዊ አገልግሎቶች መምሪያ (DHHS) በሜሞርያል ቀን ቅዳሜና እሁድ ጉዞ የሚያደርጉ ወይም በርካታ ሰዎች በሚገኙባቸው ትላልቅ ስብሰባዎች የሚሳተፉ ሰራተኞች እና ተማሪዎች ወደ ትምህርት ቤት ከመመለሳቸው በፊት የኮቪድ-19 ምርመራ እንዲወስዱ ይመከራሉ። ለሚያስፈልጋቸው ቤተሰቦች ፈጣን መመርመሪያዎች በሁሉም ትምህርት ቤቶች ይገኛሉ። የሜሞርያል ቀን በዓልን ተከትሎ ትምህርት ቤቶች እንደ አስፈላጊነቱ መመርመርያዎችን ያከፋፍላሉ። ሰራተኞች እና ተማሪዎች ፖዚቲቭ የኮቪድ-19 ሁኔታዎችን በዚህ አገናኝ/ሊንክ ሪፖርት እንዲያደርጉ እናበረታታለን።
MCPS ደህንነቱ የተጠበቀ እና ጤናማ የበዓል ቅዳሜና እሁድ ይመኛል።
የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ
Montgomery County Public Schools
Email us: ASKMCPS@mcpsmd.org