ሐሙስ፣ ጁን 23 ማወቅ ያለብዎት ጉዳዮች

ሐሙስ ሰኔ 23 መታወቅ የሚገባቸው ስምንት ጉዳዮችን እነሆ!
ዕድሜያቸው 5 እና ከዚያ በታች ለሆኑ ህጻናት ስለ ክትባት መረጃ፣ ለሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ አትሌቶች የክትባት መስፈርቶች ማሻሻያ፣ ስለ ኮቪድ-19 ወቅታዊ መረጃ፣ የሠመር የምግብ ቦታዎች እና ሌሎችንም ይካተታሉ።

  1. ከ 6 ወር እስከ 5 አመት እድሜ ላላቸው ህጻናት በትምህርት ቤት የኮቪድ-19 ክትባት በዚህ ሳምንት መጨረሻ ይጀመራል
    MCPS ከ 6 ወር እስከ 5 አመት እድሜ ያሉ ህጻናትን ቅዳሜ፣ ጁን 25 እና እሁድ፣ ጁን 26 በቀጠሮ ብቻ መከተብ ለመጀመር ከሞንትጎመሪ ካውንቲ የጤና ጥበቃ እና ሰብአዊ አገልግሎት (DHHS) ጋር በመተባበር ላይ ነው። በሞንትጎመሪ ካውንቲ አብዛኛዎቹ ክትባቶች ለግሉ ሴክተር (ሐኪሞች እና ፋርማሲዎች) በመድረሳቸው የሕፃናት ሐኪም ዘንድ የክትባት አቅርቦት ማግኘት መቻላቸውን ወላጆች እንዲያረጋግጡ ይበረታታሉ። በካውንቲው በሚተዳደሩ በእያንዳንዱ ክሊኒክ የሚሰጠው አንድ አይነት ክትባት ይሆናል። ቀጠሮ በሚይዙበት ጊዜ ክሊኒኩ የሚፈልጉትን ክትባት እንደሚሰጥ ያረጋግጡ።
    የበለጠ ለማወቅ እና ቀጠሮ ለመያዝ፣ ይህን በይነመረብ ይጎብኙ
  2. ለተማሪ-አትሌት የኮቪድ-19 ክትባት መስፈርት ማሻሻያ
    የኮቪድ-19 ክትባት ለተማሪ-አትሌቶች በጥብቅ የሚመከር ቢሆንም ከአሁን በኋላ ግን አያስፈልግም። ይህ የክትባት መስፈርት ለውጥ ለሠመር ወቅት እና በመጪው ፎል ወቅትም ይሠራል። ለውጡ በማህበረሰብ ውስጥ የሚታየውን የስርጭት ሁኔታ፣ የተሰጠ የክትባት መጠን/ብዛት እና (በአብዛኛው ከቤት ውጭ) በሚደረጉ በእንቅስቃሴዎች ትንተና ላይ በመመርኮዝ የተደረገ ለውጥ ነው። DHHS ጋር በመተባበር የተማሪ-አትሌት የህክምና አማካሪ ኮሚቴ MCPS አትሌቲክስ የሚሰጠውን ወቅታዊ መመሪያ በመከተል የክትባት መስፈርቶች ሊለወጡ ይችላሉ። በዚህ ወቅት ለትምህርት ቤት ሰራተኞች እና በጎ ፈቃደኞች በክትባት መስፈርቶች ላይ ምንም ለውጥ አልተደረገም።
    የማህበረሰብን መልእክት ከፍ ለማድረግ በሙሉ ያንብቡ።
  3. MCPS የሠመር ፕሮግራሞች ውስጥ እየተሳተፉ ከሆነ ፖዚቲቭ የኮቪድ-19 ሁኔታዎችን ሪፖርት ማድረግዎን ይቀጥሉ
    MCPS የሠመር ፕሮግራም ውስጥ ልጅ ካለዎት፣ እባክዎ ፖዚቲቭ የኮቪድ-19 ሁኔታዎችን በዚህ ቅጽ ሪፖርት ማድረግዎን ይቀጥሉ። በሠመር ወቅት የሚሠሩ ሠራተኞችም ፖዚቲቭ የኮቪድ ሁኔታዎችን ሪፖርት ማድረግ አለባቸው። DHHS የመረጃ ሠሌዳ/ዳሽቦርድ እንዲሁም የበሽታ መቆጣጠሪያ እና መከላከያ ማዕከላት (CDC)፣ በማህበረሰባችን ውስጥ የቫይረስ ስርጭት የተፅዕኖው "መካከለኛ" ደረጃ መሆኑን ያመለክታል።
  4. ስለ Synergy ParentVUE System ጠቃሚ ማሳሰቢያ፦
    ከጁን 24 እኩለ ሌሊት ጀምሮ ቀኑን ሙሉ እስከ ዓመቱ መገባደጃ ድረስ በእድሳት ምክንያት የ Synergy አገልግሎት አይኖርም። በዚህ ክፍት ጊዜ Synergy SIS፣ StudentVUE፣ TeacherVUE፣ እና ParentVUE አገልግሎት አይሰጥም። ሲስተሙ ጁን 27 .ከ 6 a.m ጀምሮ አገልግሎት የሚሰጥ ሲሆን ሪፖርት ካርዶች በ ParentVUE ይገኛሉ፥ በተጨማሪም ጁን 27 በፖስታ ቤት ይላካሉ።
  1. MCPS በተለያዩ ቦታዎች የሠመር ትምህርት ቤት ምሳ በነጻ ያቀርባል።
    በበርካታ የሰመር ት/ቤት ወይም የመዝናኛ ፕሮግራሞች የሚገኙ ተማሪዎች የሞንትጎመሪ ካውንቲ የሰመር ምግብ ፕሮግራም ምግቦችን ያገኛሉ። ነፃ ምግብ ከጁን 27 ጀምሮ በየሳምንቱ በካውንቲው ውስጥ በግምት 175 ጣቢያዎች ላይ ይቀርባል (የሚጀመርባቸው ቀናት በየቦታው ይለያያሉ)። 18 እና ከዚያ በታች ያሉ ልጆች ሁሉም እና የአካል እና የአዕምሮ እክል ያለባቸው እስከ 21 አመት የሆኑ ወጣቶች ምግብ መቀበል ይችላሉ። ለእግር ጉዞ ቅርብ ከሆኑ ቦታዎች ለምግብ አገልግሎት ወደ ተከፈቱ ቦታዎች መሄድ ይችላሉ። የትምህርት ቤት ምሳ ቦታዎችን እና የጊዜ ሠሌዳዎችን ዝርዝር ይመልከቱ
  2. ማሳሰቢያ፦ Innovative Schools/የፈጠራ ክህሎት ማበልፀጊያ ትምህርት ቤቶች ጁላይ 6 ይጀምራሉ
    የአርኮላ እና የሮስኮ ር.ኒክስ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች (Arcola and Roscoe R. Nix elementary schools) የ 2022-2023 የትምህርት አመት እሮብ፣ ጁላይ 6 ይጀመራል። Arcola 9:25 a.m. እና Roscoe R. Nix 9 am ይጀምራሉ። MCPS የፈጠራ ክህሎት ማበልፀጊያ ትምህርት ቤቶች ኢንሽዬቲቭ የተራዘመ የትምህርት ዓመት ላላቸው ተማሪዎች እየሠሩ የሚማሩት ትምህርት፣የአእምሮ ማጎልበት እና ማህበራዊ-ስሜታዊ እድገት የመሣሠሉትን አዲስ ትምህርቶች የት/ቤት ማህበረሰቦችን ይፈጥራሉ። የፈጠራ ክህሎት ማበልፀጊያ ትምህርት ቤቶች የተጀመሩት በ 2019-2020 የትምህርት ዓመት ነው።
    አርኮላ ኤለመንተሪ/Arcola Elementary
    ሮስኮ ር. ኒክስ ኤለመንተሪ/Roscoe R. Nix Elementary  
  3. ለዓመታዊ "GIVE Backpacks" ዘመቻ በመለገስ የተቸገሩ ተማሪዎችን እርዷቸው
    በ MCPS ትምህርት ቤቶች ላሉ ተማሪዎች የትምህርት እቃ መያዣ ቦርሳዎችን እና የት/ቤት አቅርቦቶችን ለማከፋፈል ለ11ኛው አመታዊ "GIVE Backpacks" ዘመቻ ለመለገስ ያስቡበት። በአቅርቦት ሰንሰለት መስተጓጎል እና በዋጋ ንረት ምክንያት ለአንድ ቦርሳ የሚከፈለው ወጪ ወደ $15 በማደጉ እና በዚህ ፎል ወቅት የትምህርት ቁሳቁስ ለማግኘት እርዳታ የሚፈልጉ በርካታ ተማሪዎች ስላሉን ድጋፍዎን ከመቼውም ጊዜ በላይ አሁን እንፈልጋለን። MCPS በሠመር ወራት ቦርሳዎችን ለግዢ በማዘዝ በተቻለ መጠን ብዙ ተማሪዎችን በትምህርት አመቱ መጀመሪያ ላይ ከት/ቤት አቅርቦቶች ጋር ቦርሳዎችን የማቅረብ ግብ አለው።
    የበለጠ ግንዛቤ ያግኙ እና ልገሳ ያድርጉ
  4. ተማሪዎች ከትምህርት ቤት ውጭ የሚያሳልፉበትን ጊዜ በተመለከተ የዳሰሳ ጥናት እስከ ጁን 30 ድረስ ክፍት ነው።
    ተማሪዎች በትምህርት ላይ ባልሆኑ ቀናት አስደሳች እንቅስቃሴዎች እና እድሎች እንዳሉ ያውቃሉ? ከ 4ኛ እስከ 11ኛ ክፍል ተማሪ ያላቸው ወላጆች እና አሳዳጊዎች የሚቀጥለውን አመት ፕሮግራም ለማሻሻል እንዲረዳን ይህን የዳሰሳ ጥናት ሞልተው እንዲመልሱ ተጋብዘዋል። ጥናቱ እስከ ጁን 30 ድረስ ክፍት ነው።

MCPS ትምህርት በሌላቸው ቀናት ተማሪዎችን እና ቤተሰቦችን የሚያሳትፉ አማራጮችን ለመስጠት ከትምህርት ውጭ በሆኑ ጊዜያት ፕሮግራሞችን ያዘጋጃል። እነዚህ በአካል እና/ወይም ቨርቹወል የሚከናወኑ እንቅስቃሴዎች አካዴሚያዊ ክህሎትን፣ አካላዊ እና ስሜታዊ ደህንነትን፣ የስነ ጥበብ እና ዲጂታል የመማር ችሎታን ያዳብራሉ።
ከትምህርት ቤት ውጪ በሚሆኑበት ጊዜ ስላለው ፕሮግራም ይበልጥ ይወቁ

የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ
Montgomery County Public Schools 




Email us: ASKMCPS@mcpsmd.org

Montgomery County Public Schools