የ MCPS የአትሌቲክስ ደህንነት እቅድ

ወደ MCPS የአትሌቲክስ ዝግጅቶች ለሚመጡ የተሻሻሉ የደህንነት እርምጃዎች፣ አርብ ሴፕቴምበር 23 ይጀመራል

ለተከበራችሁ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ማህበረሰብ፦

የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ከዚህ አርብ ሴፕቴምበር 23 ጀምሮ በአትሌቲክስ ዝግጅቶች ላይ በርካታ የተሻሻሉ የደህንነት እርምጃዎችን ይተገብራል።

እርምጃ መውሰድ ያስፈለገበት ምክንያት በኖርዝዌስት እና በጌትስበርግ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች መካከል ሴፕቴምበር 16 በተደረገው ግጥሚያ ወቅት ከሜዳ ውጪ የተፈጠሩ ምክንያት የሌላቸው ግጭቶችን ጨምሮ በቅርብ ጊዜ በተካሄደው የቫርሲቲ የእግር ኳስ ጨዋታ ተቀባይነት የሌለው እና አጸያፊ ባህሪን ተከትሎ የመጣ ነው።

MCPS በተለያዩ የአትሌቲክስ ውድድሮች ለመደሰት ለሚፈልጉ ተማሪዎች፣ ቤተሰቦች እና የማህበረሰብ አባላት ሠላም እና ደህንነት ቁርጠኛ ነው፣በዚህ የፎል ወቅት የመክፈቻ ሳምንታት የተከሰቱትን አይነት የጥቃት ባህሪ እና ድርጊቶችን አይታገስም።

የሁሉንም ተመልካቾች እና የጨዋታ ተሳታፊዎችን ደኅንነት ለማረጋገጥ ከሴፕቴምበር 23 ጀምሮ፣ የሚከተሉት እርምጃዎች በሁሉም የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ጨዋታዎች ላይ ተግባራዊ ይሆናሉ።

  • የተሣታፊ ትምህርት ቤቶች ተማሪዎች ትክክለኛ ትኬት ይዘው እና የተማሪ መታወቂያቸውን ወይም የፕሮግራማቸውን የሲነርጂ ማረጋገጫ ይዘው እንዲገኙ ይፈቀድላቸዋል። ሌሎች እድሜያቸው ለትምህርት የደረሱ ተመልካቾች ሁሉም ከጎልማሳ ቻፐሮን ጋር መምጣት አለባቸው - ይህ ሁሉንም የአንደኛ ደረጃ እና መካከለኛ ደረጃ ተማሪዎችን እና ከሌሎች ትምህርት ቤቶች የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎችን ያጠቃልላል። አዋቂዎች ቻፕሮኖች በጨዋታው ለሚቆዩበት ጊዜ ተማሪዎቻቸውን ማየት መቆጣጠር እና መከታተል አለባቸው። ተመልካቾች በር ላይ ሲገቡ ተጨማሪ የመግቢያ ጊዜ ሊወስድ ስለሚችል እንዲታገሱ ይጠየቃሉ።
  • በጨዋታው ወቅት ተማሪዎች እና ተመልካቾች በቆሙበት ቦታ መቀመጥ አለባቸው። በግማሽ ሰአት እና በድህረ ጨዋታ መሰባሰብ ያለ ቢሆንም በጨዋታው ወቅት በብዛት መሰባሰብ አይፈቀድም።
  • ከእረፍት በኋላ ዳግም መግባት ስለማይኖር ተመልካቾች ከወጡ በኋላ ተመልሰው አይገቡም።
  • ቦርሳዎችን መያዝ አይፈቀድም።
  • ተማሪ-አትሌቶች፣ አሰልጣኞች፣ የጨዋታ ኃላፊዎች፣ የአትሌቲክስ ክፍል ሰራተኞች፣ እና እውቅና ያላቸው ባለሙያዎች እና ሚዲያዎች ብቻ ይፈቀድላቸዋል።
  • የዝግጅቱ ደህንነት ሰራተኞች ልዩ ልዩ መግቢያዎች፣ የተጨናነቁ መውጫዎች እና ከፍተኛ የትራፊክ ፍሰት ባለባቸው አካባቢዎች ተጨማሪ ድጋፍ ይጠቀማሉ።
  • ተገቢ ያልሆነ እና ያልተገራ ባህሪ ከ MCPS የአትሌቲክስ እንቅስቃሴዎች በተከታታይ መታገድን ሊያስከትል ይችላል።

እነዚህ ለውጦች በሁሉም የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የአትሌቲክስ ዝግጅቶች ለቀሪው ወቅት ተፈጻሚ ይሆናሉ።

ሌሎች ሁኔታዎች ከተከሰቱ ተጨማሪ የደህንነት እርምጃዎች ተግባራዊ ይሆናሉ። ይኼውም የተመልካቾችን ቁጥር መወሰን እና የጨዋታ ጊዜ/ቀን ማስተካከያዎችን ሊያካትቱ ይችላሉ። ተጨማሪ እርምጃዎች በሚከተሉት መመዘኛዎች ወይም መመሪያዎች ላይ ይመሰረታሉ፡

  • የሚጠበቀው ያህል የተመልካቾች ብዛት።
  • በትምህርት ቤቶች መካከል ያለው ታሪካዊ ፉክክር።
  • ይህን አመት እና ያለፉትን አመታት ጨምሮ የተከሰቱ ሁኔታዎች።
  • የመገልገያ አቀማመጥ፣ መብራት፣ የተመልካቾች መቀመጫ እና የመኪና ማቆሚያ ቦታን ጨምሮ።
  • ከፖሊስ አጋሮች ጋር በትብብር የሚተላለፉት በትምህርት ቤት እና በአትሌቲክስ ክንውኖች ላይ ተጽዕኖ ሊያሳርፉ የሚችሉ በማህበረሰቡ ውስጥ ያሉ ክስተቶች።

ማንኛውም ቡድን ከባድ ወይም ተገቢ ያልሆነ ባህሪን ካሳየ ከድህረ ውድድር ወይም ለብዙ ጨዋታዎች ሊገለል/ሊታገድ ይችላል።

የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ
Montgomery County Public Schools 



Email us: ASKMCPS@mcpsmd.org

Montgomery County Public Schools