የምስጋና በዓል መልእክት ከሱፐርኢንተንደንት ዶ/ር ሞኒፋ ቢ. ማክኒት

November 22, 2022

ለተከበራችሁ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ማህበረሰብ፦

የምስጋና በዓል የሚከበርበት ጊዜ የማሰላሰል እና ምስጋና የሚቀርብበት ጊዜ ነው - እንዲሁም በህይወታችን እና በማህበረሰባችን መልካም ነገሮች ላይ የምናተኩርበት ጊዜ ነው። በትምህርት ዲስትሪክታችን፣ ከተማሪዎች፣ ከሰራተኞች እና ከማህበረሰቡ አባላት ጋር ባደረኩት ጉብኝቶች፣ በየቀኑ በእያንዳንዱ ክፍል ላሉ ተማሪዎች ሁሉ ለታላቅ መማር ማስተማር ልዩ ትኩረት መሰጠቴን ስመሰክር ቆይቻለሁ። በእናንተ ምክንያት ለካውንቲያችን ትምህርት ቤቶች የወደፊት አሠራርና አፈፃጸም ትልቅ ተስፋ አለኝ።

ለ --- ምስጋናዬን በአክብሮት አቀርባለሁ!

  1. አስደናቂ ተማሪዎቻችንን፡እናመሰግናለን መመሪያ ብርሃናችን ስለሆናችሁ፣ ተሰጥኦአችሁን ለእኛ ስላካፈላችሁን እና እድገታችሁን የመመስከር እድል ስላገኘን።
  2. ሁሉም ወላጆች፣ ተንከባካቢዎች፣ ከትምህርት በኋላ እና በፊት በሚካሄዱ ፕሮግራሞች ላይ የምትሠሩ ሰራተኞች፡ እናንተ ከትምህርት ቤት በፊት እና በኋላ በምታደርጉት እንክብካቤ ከመደበኛ የትምህርት ሰአታት በላይ ትምህርትን ማራዘም ተችሏል።
  3. መምህራኖቻችንን እናመሰግናቸዋለን፡ ለተማሪዎቻችን በየእለቱ ሁለንተናችሁን በመስጠት "ተማሪዎችን በማስቀደም" ተልዕኮ ወደ መልካም ህይወት ታመጧቸዋላችሁ።
  4. ለሙያ እና የቴክኖሎጂ አስተማሪዎች፣ የልዩ ትምህርት አስተማሪዎች፣ የትምህርት ቤት ሳይኮሎጂስቶች፣ ካውንስለሮች/አማካሪዎች እና ማህበራዊ ሰራተኞች እናመሰግናችኋለን። የተማሪዎቻችንን ፍላጎቶቻቸውን በሙሉ ለማሟላት የእለት ተእለት ልምዶቻቸውን ለየግላቸው ታዘጋጁላቸዋላችሁ።
  5. የምግብ አገልግሎት ሰራተኞችን፣ የትራንስፖርት ሰራተኞችን፣ የአትሌቲክስ ሰራተኞችን እና ክለቦችን እና ሌሎች ከትምህርት በኋላ እንቅስቃሴዎችን የሚደግፉ ባለሙያዎችን እናመሰግናለን! ልጆቻችን ምግብ፣ መጓጓዣ እና ልምምዶቻቸውን የሚያሟሉበት እንቅስቃሴዎች እንዲኖራቸው በእርግጠንነት ስለምታከናውኑ።
  6. ርዕሰ መምህራን እና የትምህርት ቤት አስተዳዳሪዎችእናመሰግናለን! በትምህርት ቤቶቻችን ውስጥ ላሉ ሁሉ ያደረጋችሁት አበረታች ድጋፍ የተማሪዎችን እንቅስቃሴና ልምድ አንድ ላይ የሚያያይዝ ማጣበቂያ ነው።
  7. በዋና ጽሕፈት ቤት፣ የሥርዓተ ትምህርት ሰራተኞች፣ የወላጅ ማህበረሰብ አስተባባሪዎች፣ የተማሪ ሥራ ሰራተኞች፣ የስራ አስፈፃሚ እና የቢዝነስ ሰራተኞች፣ ጸሃፊዎች እና የአስተዳደር ረዳቶች እንዲሁም የደህንነት ጥበቃ ሰራተኞች እናመሰግናለን! ለብዙ ባለድርሻ አካላት የምትሰጡት አገልግሎት ታላቅ ነው።
  8. ስለምትሰጡት አመራር እና ለምታገለግሉት ማህበረሰብ ድምጽ ስለሆናችሁ የኛን የትምህርት ቦርድ አባላት እናመሰግናለን!

በእርግጥ ዝርዝሩ ይቀጥላል። የሥራ ቦታቸው ላልተዘረዘረ የ MCPS ሰራተኞች በሙሉ፣ እናንተም ተማሪዎች ለኮሌጅ፣ ለስራ እና ለማህበረሰብ አገልግሎት ዝግጁ መሆናቸውን በማረጋገጥ ለእኛ ተልእኮ መፈፀም እኩል አስፈላጊ እና ወሳኝ አካል መሆናችሁን እወቁ። በዲስትሪክታችን ውስጥ ያለዎት ሚና ምንም ይሁን ምን፥ ዋጋ እንዳለዎት እና እንደምናደንቅዎት ይወቁ። ጠንካራ፣አስደሳች እና ምላሽ ሰጭ ባህል ያለው ትምህርት ለማስረፅ ያለን ራእያችን በእያንዳንዱ ክፍል ውስጥ ላሉ ተማሪዎች በየእለቱ እውን መሆኑን ለማረጋገጥ ከፈለግን ብዙ አጣዳፊ ስራ ይጠብቀናል። ይህንን "ሁሉንም አሁን፥ ሁላችንም ለተማሪዎቻችን" እናደርጋለን!

እናንተን በሱፐርኢንተንደንትነት በማገልገሌ ኩራት ይሰማኛል። ለሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ ተማሪዎች የሚያደርጉትን ሁሉ አክብሮት መስጠት አስፈላጊ ነው፤ ለዚህም ጥልቅ ምስጋና አቀርባለሁ። መልካም የእረፍት ጊዜ እና ሰላማዊ የምስጋና በዓል ይሁንላችሁ። ባለፈው አርብ ከትምህርት ቤቶቻችን የጤና መኮንን የተላኩትን ጠቃሚ የምስጋና በዓል ሰሞን የጤና አጠባበቅ ምክሮችን እንዳይዘነጉ ያስታውሱ።

ከአድናቆት ጋር

Dr. Monifa B. McKnight
Superintendent of Schools



Email us: ASKMCPS@mcpsmd.org

Montgomery County Public Schools