ከሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) የጤና መኮንን የተላለፈ መልእክት

February 14, 2023

ለተከበራችሁ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ማህበረሰብ፦

ቅዳሜ፣ ጃንዋሪ 28 ስለ ፋንታንይል/Fantanyl ግንዛቤ ለማስጨበጥ በክላርክስበርግ (Clarksburg) 2ኛ ደረጃ ት/ቤት በተዘጋጀው የቤተሰብ ፎረም ላይ 1,500 በላይ ሰዎች ተሳትፈዋል።ተማሪዎች፣የቤተሰብ አባላት እና ሰራተኞች፤ ወጣቶቻችንን እና ማህበረሰባችንን የተከለከለ/ህገ-ወጥ ፈንታንይል/fentanyl ከሚያስከትላቸው አደጋዎች መጠበቅ አስፈላጊ መሆኑን እና ለመከላከል መነሳሳታቸውን ገልፀዋል።

የማህበረሰብ አጋሮቻችን Montgomery Goes Purple እና Downcounty Consortium ስለ ፋንታንይል/Fantanyl አደገኛነት ሁለተኛውን ዙር የቤተሰብ ፎረም የሚያስተናግዱ ሲሆን፥ በኖርዝዉድ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት (Northwood High School) ቅዳሜ፣ ፌብሩዋሪ 25 ይካሄዳል። ቤተሰቦች እና የማህበረሰብ አባላት ከካውንቲው የጤና ዲፓርትመንት እና ከሞንትጎመሪ ካውንቲ ፖሊስ ዲፓርትመንት ተወካዮችና ከኤክስፐርቶች ስለ ፈንታንይል/Fantanyl አደገኛነት የመስማትና የማወቅ እድል ይኖራቸዋል። የት/ቤት መሪዎች ስለ ት/ቤት የደህንነት ጥበቃ ሂደቶች እና የጤና ትምህርት ስርአተ-ትምህርትን የሚመለከቱ ጥያቄዎችን ይመልሳሉ። ለግለሰብ ጥያቄዎች ጊዜ ለመስጠት የስፓኒሽ ቋንቋ ክፍለ ጊዜን ጨምሮ ለተማሪዎች እና ለቤተሰብ አባላት/ለሰራተኞች ልዩ ልዩ ክፍለ ጊዜዎች ይካሄዳሉ።

ህገወጥ ፈንታንይል/fentanyl በወጣቶች ላይ የሚያደርሰውን ጉዳት ለመቀነስ በጋራ መስራት እና ችግሩን በተለያዩ ደረጃዎች ልንቀርፈው ይገባል።የምናዘጋጃቸው ዲስትሪክት አቀፍ መድረኮች ለተማሪዎቻችን፣ ለሰራተኞቻችን እና ለቤተሰቦቻችን እውቀትን እና የመረጃ ሪሶርሶችን የሚሰጡ ከመሆኑም በላይ ንቁ ውይይት ለማድረግ እድሎችን ይፈጥራሉ። ተማሪዎች፣ ወላጆች/ተንከባካቢዎች፣ ሰራተኞች፣እና የት/ቤት መሪዎች የጤና እና የደህንነት እርምጃዎች ለህብረተሰባችን በጣም አስፈላጊ እንደሆኑ እና እንዴት በጋራ መተግበር እንዳለባቸው ለመረዳት አብረው እየሰሩ ናቸው።

ይህን ጠቃሚ ስራ በጋራ ለማከናወን እና አብረን ለመቀጠል በጉጉት እንጠባበቃለን።

ከልብ

Patricia Kapunan, M.D., M.P.H.
MCPS Medical Officer

https://www2.montgomeryschoolsmd.org/departments/medical-officer/
በራሪ ጽሑፍ የሚገኝበት ሊንክ፦ Link to flier https://twitter.com/MCPS/status/1623837902953402368/photo/1



Email us: ASKMCPS@mcpsmd.org

Montgomery County Public Schools