ከስፕሪንግ እረፍት እንኳን በደህና ተመለሣችሁ፡ ከሱፐርኢንተንደንት ዶ/ር ሞኒፋ ቢ. መክነይት/Superintendent Dr. Monifa B. McKnight የተላለፈ መልእክት

ኤፕሪል 10

ውድ ተማሪዎች፣ ሰራተኞች እና ቤተሰቦች

ይህ ደብዳቤ በጥሩ ሁኔታ እንደሚያገኛችሁ እና የሚያስደንቅ እና እረፍት ያገኛችሁበት የስፕሪንግ ዕረፍት ጊዜ እንዳሳለፋችሁ ተስፋ አደርጋለሁ። ወደ ትምህርት ቤት ስንመለስ፣ ለሁላችሁም ሞቅ ያለ "እንኳን በደህና ተመለሳችሁ" መልእክት ማስተላለፍ እፈልጋለሁ።

ወደ ትምህርት ዓመቱ መገባደጃ ስናመራ፣ ተማሪዎቻችን ጠንክረው እንዲሰሩ እና በአካዳሚክ ግባቸው ላይ እንዲያተኩሩ አበረታታቸዋለሁ፣ እና ሰራተኞቻችን በሙሉ ተማሪዎቻችን ወደ ግባቸው እንዲደርሱ ስለሚረዷቸው ማመስገን እፈልጋለሁ። እስካሁን ያገኘነውን እንቅስቃሴ አጠናክረን በመቀጠል የትምህርት አመቱን በታላቅ ስኬት ማጠናቀቅ አለብን።

ሠላማዊ እና ደህንነታቸው የተጠበቀ ምቹ ትምህርት ቤቶች፡ የኛ ኃላፊነት

የስፕሪንግ ወቅት ሲደርስ፣ ይዞት የሚመጣው ሞቃታማ የአየር ሁኔታ በትምህርት ቤቶች እና ማህበረሰቦች ውስጥ ለየት ያሉ ክስተቶችን ሊያስከትል ይችላል። ወደ ዕለታዊ ተግባራችን ስንመለስ፣ ለሁሉም ሠላምና ደህንነት ቅድሚያ መስጠታችንን እንድንቀጥል እንድትረዱን እንፈልጋለን። በጋራ በመስራት ከጦር መሳሪያ፣ ከፈንጂዎች፣ ከህገወጥ የአደንዛዥ እፅ አጠቃቀም፣ ከቫፒንግ ጎጂ መሳሪያዎች እና ከትንባሆ ምርቶች እና ከአካላዊ ንዴት አዘል ጭቅጭቅና ፍጥጫዎች ነፃ ለመሆን ለሚጥሩ ተማሪዎቻችን እና ሰራተኞቻችን ደህንነቱ የተጠበቀ እና ጤናማ የመማሪያ አካባቢን ለመጠበቅ አስተዋፅዖ ማድረግ እንችላለን። እነዚህን የመሳሰሉ መጥፎ ድርጊቶች በማንኛውም ሁኔታ በትምህርት ቤቶች ግቢ ውስጥ አይፈቀዱም ወይም መከሰት የለባቸውም/አይፈቀድም። የትምህርት ቤቶቻችንን ደህንነት ለመጠበቅ እንዲረዳን፣ ሁሉንም የውጪ በሮች እንዲዘጉ ይደረጋል፣ እና ሁሉም ጎብኚዎች ዋና መግቢያዎችን ብቻ እንዲጠቀሙ እና በደህንነት ፍተሻ ማሽኖች ውስጥ ተፈትሸው እንደሚገቡ ማስታወስ አለባቸው።

እንዲሁም፣ ሁሉም ተማሪዎች፣ ሰራተኞች እና ጎብኝዎች እርስ በርስ፣ በአክብሮት እንድንስተናገድ እናሳስባለን። በቅርብ ጊዜ የተከሰተው አይነት ጭፍን ጥላቻ በትምህርት ቤትም ሆነ ከትምህርት ቤት ውጭ ተቀባይነት እንደሌለው መምከር እና መወገድ አለበት። የትምክህተኛነት ቋንቋ መጠቀም ወይም የትምህርት ቤትን ንብረት በጥላቻ ምልክቶች ማበላሸት የማይፈቀድ ከመሆኑም ባላይ እነዚህ አይነት ድርጊቶች ፍጹም መወገድ አለባቸው።

የማክበር ወቅት ነው

በአጠቃላይ፣ የካውንቲው ትምህርት ቤቶቻችን፣ ለመማር እና ለማደግ ከሚሰጡት በርካታ እድሎች አንስቶ ብዝሃነትን እና አካታችነትን በመቀበል በሚያደርጉት የምናከብረው እና የምንወደው ብዙ ነገር አለ። ይህን በሚመለከት ብዙ ታታሪ ሰራተኞች እነዚህን እድሎች ለመስጠት እጅግ ብዙ አስተዋፅዖ ያደርጋሉ። ከዕረፍት ስንመለስ፣ እባካችሁ ረዳት ርእሰመምህራኖቻችንን፣ ረዳት የት/ቤት አስተዳዳሪዎችን፣ እና ፓራኢዱኬተሮችን - ስለታታሪነታቸው እና ስለትጋታቸው አድናቆታችንን ለመግለጽ ትንሽ ጊዜ ወስደን ምስጋናችንን እንግለጽላቸው። ያለፈው ሳምንት ብሔራዊ የረዳት ርእሰ መምህራን ሳምንት ነበር፣ እና ኤፕሪል 5 የፓራፕሮፌሽናል አድናቆት ቀን ነበር። ተማሪዎቻችንን እና ሰራተኞቻችንን የትምህርት ቤቶች ማህበረሰብ ወሳኝ አካል በመሆን ለመደገፍ ላደረጉት ያላሰለሰ ጥረት ልባዊ አድናቆቴን ላቀርብ እፈልጋለሁ።

ትምህርት ቤቶች ያቀዱት በርካታ የስፕሪንግ ወቅት ዝግጅቶች ስለሚኖራቸው የልጆቻችሁን ትምህርት ቤት ልዩ ልዩ ዝግጅቶች መርኃ ግብር እና ወደ ቤት የሚላኩ መልዕክቶችን መፈተሽዎን ያረጋግጡ። በየትምህርት ክፍሎቻቸው የሚከሩት ዝግጅት፣የስፕሪንግ ቲያትር፣ አትሌቲክስ እና ሌሎችም ተማሪዎቻችን በትምህርት ቤት ያገኟቸውን ልምዶች እና የተማሩትን፣ የቀሰሙትን እውቀት ሁሉ ያንፀባርቃል።

መጪዎቹ ሁለት ጠቃሚ በዓላት የሚከተሉትን ያካትታሉ፦

  • ኤፕሪል 19፣ የሩት እና የኖርማን ራልስ-ፓትሪሺያ ኦኔል "Ruth and Norman Rales-Patricia O’Neill" የነጻ ትምህርት እድል ያገኙ ተማሪዎች ምረቃ ፕሮግራም ይከበራል። እያንዳንዱ የስኮላርሺፕ እድል ያገኘ(ች) ተማሪ $10,000 የሚያገኝ ተመራቂ ነው።
  • ኤፕሪል 24፣ የዘንድሮውን የህፃናት ሻምፒዮን ተሸላሚዎች እውቅና በመስጠት እናከብራለን፣ የአመቱ ምርጥ የድጋፍ አገልግሎት ባለሙያ፣ የከፍተኛ ብቃት ያለው/ያላት አስተዳደር አሸናፊ፣ ማህበረሰብ አቀፍ የህጻናት አገልግሎት ሻምፒዮን፣ አትሌቲክስ R.A.I.S.E እውቅና የሚሰጣቸው ሲሆን ከአመቱ መጨረሻ የምርጥ መምህራን እጩዎች አንደኛው 2023 የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) የአመቱ ምርጥ መምህር ተብሎ የሚሰየምበት/የምትሰየምበት ቀን ይሆናል። በዚህ አመት የበዓሉ አከባበር በአካል ወደ ነበረበት ሁኔታ የሚመለስ ስለሆነ፣ ዳግም እንድንሰባሰብ እና በተማሪዎቻችን ሕይወት ውስጥ አንዳንድ ከፍተኛ ልዩነት ፈጣሪዎችን ስላበረከቱት አስተዋጾ እውቅና ለመስጠት ያስችለናል።

የዘንድሮውን አስደሳች የምረቃ እና የከፍታ ወቅት ላይ ስንደርስ ሌሎችም የምናከብራቸው በርካታ ዝግጅቶችና ፕሮግራሞች ይኖራሉ።
ለአካዳሚክ ልህቀት እና ደህንነቱ የተጠበቀ እና ምቹ የመማሪያ አካባቢን ለማጎልበት ጥረት ስናደርግ ከእያንዳንዳችሁ ጋር በጋራ ለመስራት በጉጉት እጠብቃለሁ። ስለቀጣይ ትብብራችሁ እና ድጋፋችሁ ሁላችሁንም አመሰግናለሁ። ቀሪው የትምህርት ዓመት ምርጥ እና ውጤታማ እንዲሆን "አሁን ሁላችንም በአንድነት ተባብረን" መስራታችንን እንቀጥል።

ከአክብሮት ጋር

Dr. Monifa B. McKnight
ዶ/ር ሞኒፋ ቢ. ማክናይት
MCPS Superintendent of Schools
የት/ቤቶች ሱፐርኢንተንደንት



Email us: ASKMCPS@mcpsmd.org

Montgomery County Public Schools