WATCH LIVE:

ሱፐርኢንቴንደንት ዶ/ር ሞኒፋ ቢ.ማክኒት በሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ የዘረኝነት እና የጥላቻ ክስተቶች የመስፋፋትን ጉዳይ ያነሳሉ


ሱፐርኢንተንደንቷ የማህበረሰብን ጥሪን በሚመለከት ዲስትሪክት አቀፍ እርምጃዎችን እና ለማህበረሰቡ ያሳውቃሉ።

ሱፐርኢንተንደንቷ የማህበረሰብን ጥሪን በሚመለከት ዲስትሪክት አቀፍ እርምጃዎችን እና ለማህበረሰቡ ያሳውቃሉ።

ለተከበራችሁ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ማህበረሰብ፦

ከቅርብ ወራት ወዲህ የጥላቻ፣ አድሏዊ፣ ዘረኝነት፣ ፀረ-ሴማዊነት እና LGBTQ + ጭፍን ጥላቻ ክስተቶች በከፍተኛ ሁኔታ ጨምሯል። ሱፐርኢንተንደንት ዶ/ር መክንየት (Superintendent Dr. McKnight) ሐሙስ፣ ኤፕሪል 27ይህንን ጉዳይ በተመለከተ እና በካውንቲው ልጆች እና በትምህርት ቤቶች ላይ ስለሚያስከትለው ሥርዓት አቀፍ አሉታዊ ተጽእኖ መግለጫ ይሰጣሉ። ሱፐርኢንተንደንቷ የችግሩን ገጽታ በማመላከት፣ በጋራ የመከላከል ጥሪ የሚያቀርቡ ሲሆን የትምህርት ቤቶች ዲስትሪክት ወደፊት የሚወስዳቸውን እርምጃዎችም ያሳውቃሉ።

የቀጥታ ስርጭት፡ መግለጫው MCPS-TV YouTube ገጽ እና MCPS ድረገጽ ላይ በቀጥታ ይተላለፋል

  1. YouTube: https://www.youtube.com/watch?v=OSAyzodJyXs
  2. MCPS Website/በይነመረብ: www.montgomeryschoolsmd.org

የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ
Montgomery County Public Schools 



Email us: ASKMCPS@mcpsmd.org

Montgomery County Public Schools