የሞንትጎመሪ ካውንቲ የትምህርት ቦርድ ስብሰባዎችን ለህዝብ ተደራሽ ማድረግን የሚመለከት የደህንነት መልዕክት

ውድ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ማህበረሰብ አባላት

ማክሰኞ፣ ጁን 27, 2023 በሚካሄደው ቀጣይ የትምህርት ቦርድ ስብሰባ ላይ አስፈላጊ ከመሆኑ የተነሳ የሚከተሉት የደህንነት እርምጃዎች ተግባራዊ ይሆናሉ።

እንደተለመደው፣ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ተቀዳሚ ግብ የሚሆነው ህዝብን ወክለው በሚደረጉ የትምህርት ቦርድ ስብሰባዎች ላይ የሚገኙትን የሁሉንም ተሳታፊዎች ደህንነት እና ሠላም ማረጋገጥ ነው። "Carver Educational Services Center building at 850 Hungerford Dr. in Rockville" ህንፃ ውስጥ ለመግባት የሚኖረው እድል የሚያካትተው ቀጠሮ የተያዘላቸውን ንግግር አድራጊዎች፣ ተጋባዥ ተሳታፊዎችን እና ክፍሉ የሚችለውን ያህል ለሌሎች እንግዶችን ነው። ይሄ ውሳኔ የተላለፈው የተለያዩ ምክንያቶች በጥንቃቄ ከታዩ በኋላ በመሆኑ፣ እነዚህም የሚያካትቱት በቅርቡ ከፍተኛ ህዝብ የተገኘባቸው ዝግጅቶች በትምህርት ተቋሙ ማዕከላዊ ቢሮ የስራ ሂደት ላይ የፈጠረው ተፅዕኖ፣ እና የትምህርት ቦርድ የህዝብ ስብሰባዎችን በውጤታማነት የመምራት አስፈላጊነትን መሠረት በማድረግ ነው። ወደ ህንጻው/ፋሲሊቲው የሚገቡትን ግለሰቦች ቁጥር በመቆጣጠር፣ የስብሰባውን ሂደት በተሻለ ስኬታማነት መምራትና ደህንነታቸውን መጠበቅ እንዲሁም የስብሰባውን የተመቻቸ አሠራር ቅድሚያ ትኩረት መስጠት እንችላለን። ከማህበረሰብ እና ከመንግስት አጋሮች ጋር በመስራት፣ ደህንነቱ እና ስርዓቱ የተጠበቀ ስብሰባ ለማካሄድ የሚከተሉትን ደረጃዎች/እርምጃዎች አስቀምጠናል።

በምስርቅ በኩል የሚገኘው የመኪና ማቆሚያ የህዝብ ሰላማዊ ሰልፎችን ለመሳሰሉ ማንኛውም ትልቅ ቡድን መሰብሰቢያነት ተለይቶ የተመደበ አካባቢ ይሆናል። የመናገር ነፃነትን አስፈላጊነት እንገነዘባለን፤ እና ግለሰቦች መብታቸውን ሰላማዊ እና መከባበር በሰፈነበት መንገድ እንዲተገብሩ እናበረታታለን። ነዋሪዎችን እና የማህበረሰብ አባላትን አንድ የተወሰነ ቦታ ላይ እንዲቆዩ በመጠየቅ፣ የስብሰባ መበጥበጥ እንዳይኖር ለመከላከል/ለመቀነስ እና የሁሉንም ተሳታፊዎች ደህንነት ለማረጋገጥ አላማ እናደርጋለን።

ስለተረዳችሁን እና እነዚህን የደህንነት ፕሮቶኮሎች/አሰራሮች ለማክበር ስለምታደርጉልን ትብብር ምስጋና እናቀርባለን። ይሄንን ማድረግ በሁሉም ተሳታፊዎች መካከል ገንቢ ንግግር/ውይይት ለማካሄድ እና በስብሰባው ለሚገኙ የቦርድ አባላት እና ለሰራተኞች ውጤታማ ውሳኔ ለማድረግ ምቹ የሆነ አካባቢን/ሁኔታን ለመፍጠር ይረዳል።

በተመሳሳይ ምክንያቶች እና በቦታ ውስንነት የተነሳ፣ ለተሳታፊዎች ምንም ትርፍ ክፍል አይኖርም። በዚህ ምክንያት ስለሚፈጠረው ማንኛውም አይነት ያለመመቸት ይቅርታ እንጠይቃለን። ሁሉንም የትምህርት ቦርድ ስብሰባዎች በዲስትሪክቱ ድረ-ገፅ፣ www.montgomerschoolsmd.org፣MCPS-TV YouTube ቻናል ላይ እና Comcast Channel 34 (HD 1071), Verizon Channel 36, RCN Channel 89 ላይ በሚገኘው MCPS-TV በመጠቀም በኦንላይን መመልከት እንደሚቻል ማስታወስ እንወዳለን።

አስፈላጊነቱ እየታየ ወደ ፊት ለሚካሄዱ የትምህርት ቦርድ ስብሰባዎች ተመሳሳይ አሰራሮች ተግባራዊ ሊደረጉ ይችላሉ፤እነዚህ ውሳኔዎች የሚሰጡ ሲሆን ለማህበረሰቡ ይገለጻል።

በሁሉም የትምህርት ቦርድ ስብሰባዎች ላይ የህዝብ ደህንነትን እና ስርዓትን መጠበቅ እንድንችል እንዲረዳን ለምታደርጉልን ትብብር እና ድጋፍ ከልብ የመነጨ ምስጋናችንን እናቀርባለን። የማህበረሰብ አባላቶቻችን ደህንነት ከምንም በላይ ቅድሚያ የምንሰጠው ጉዳይ ነው፣ እና በሁሉም እንቅስቃሴዎቻችን ላይ ለደህንነታቸው ቅድሚያ በመስጠት መስራታችንን እንቀጥላለን። በማህበረሰባችን ውስጥ ደህንነቱ የተጠበቀ እና መከባበር የሰፈነበት አካባቢን ማጎልበት ላይ ለምታሳዩት ትብብር እና ቀጣይነት ያለው ቁርጠኝነት ምስጋና እናቀርባለን።

የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS)



Email us: ASKMCPS@mcpsmd.org

Montgomery County Public Schools