ሐሙስ፣ ኦክቶበር 6 መታወቅ ያለባቸው ጉዳዮች

ለሐሙስ፣ ኦክቶበር 6 መታወቅ ያለባቸው ሰባት ነገሮች እነሆ! በትምህርት ቤት የቀን መቁጠሪያ ላይ ከተማሪዎች የግብአት ጥያቄ፣ ለሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ፕሮግራሞች የስምንተኛ ክፍል መደበኛ ማመልከቻ፣ የአትሌቲክስ አሰልጣኝ ወቅታዊ መረጃ፣ ስለ አዕምሮ ጤንነት የግንዛቤ ሳምንት ማሳሰቢያ እና ሌሎችም ወደፊት የሚመጡ ጉዳዮችን ያካትታሉ።

  1. mental health weekከኦክቶበር 10–15 ስለ አእምሮ ጤንነት የግንዛቤ ሳምንትን እንደሚከታተሉ እርግጠኛ ይሁኑ

MCPS እና የሞንትጎመሪ ካውንቲ ትምህርት ቤት ሳይኮሎጂስቶች ማህበር ኦክቶበር 10-15 ወጣቶች እና ቤተሰቦች ጠቃሚ የሆኑ ጉዳዮችን ከአእምሮ ጤና ባለሙያዎች እንዲሰሙ ነጻ ቨርቹወል ዝግጅቶችን ያስተናግዳሉ። ይህ ለአንድ ሳምንት የሚካሄድ ኤክስፖ ወቅታዊ ጭብጦችን፣ ባለሙያ ተናጋሪዎች እና መረጃ ሰጪ ቪዲዮዎችን እና ሁለት የቀጥታ ስርጭቶችን ያቀርባል፡ በተማሪ የአእምሮ ጤንነት ላይ የተደረገ ልዩ ዝግጅት እና የሪሶርስ አውደርእይ እና ቅዳሜ፣ ኦክቶበር 15 የጥያቄና መልስ ክፍለ ጊዜ ይኖራል።
ስለ አእምሮ ጤንነት ግንዛቤ ሳምንት የበለጠ ይወቁ።
ስለ አእምሮ ጤንነት መረጃ እና ሪሶርሶችን ይመልከቱ

  1. calendar2023–2024 የትምህርት ቤት የቀን መቁጠሪያ ላይ የተማሪዎች ግብአት ይፈለጋል

ለሚቀጥለው ዓመት የትምህርት ቤት የቀን መቁጠሪያ የማህበረሰብ አስተያየቶችን ግብአት የመቀበል ሂደት በመካሄድ ላይ ነው። 2023-2024 የትምህርት ዓመት የቀን መቁጠሪያ ሲዘጋጅ በዳሰሳ ጥናቱ መሰረት የማህበረሰቡን ፍላጎት ለማወቅ እንፈልጋለን። ሰራተኞች ማክሰኞ ኦክቶበር 25 በትምህርት ቦርድ ስብሰባ ላይ ሁኔታዎችን ያቀርባሉ። ፍላጎትዎን እስከ ሀሙስ ኦክቶበር 13 ይግለጹ እና ተማሪዎችዎ ድምፃቸው እንዲሰማ የዳሰሳ ጥናቱን እንዲያጠናቅቁ ያበረታቷቸው።
የዳሰሳ ጥናቱን ይመልከቱ/ይሙሉ

  1. የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ስምንተኛ ክፍል የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ፕሮግራሞች ማመልከቻ አርብ ኦክቶበር 7 ይለቀቃል

ተማሪዎች የኮሌጅ እና የስራ ግቦቻቸውን እንዲያሳኩ ለመርዳት MCPS ብዙ የአካዳሚክ ፕሮግራሞችን ያቀርባል። በአካባቢያቸው ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ከጠንካራ የኮሌጅ እና የሙያ ዝግጁነት መርሃ ግብሮች በተጨማሪ፣ የ 8ኛ ክፍል ተማሪዎች ለሪጅናል ወይም ለካውንቲ አቀፍ ፕሮግራሞች ማመልከት ይችላሉ። የስምንተኛ ክፍል ተማሪዎች ማመልከቻ ParentVue ላይ በተለያዩ ቋንቋዎች ይገኛል።በተጨማሪ የተማሪ ብቁነት ሪፖርት StudentVue እና ParentVue ፋይሎች ውስጥ ይገኛል። እንዲሁም 9-11ኛ ክፍል ተማሪዎች፣ ለከፍተኛ ደረጃ ኮሌጅ እና ለስራ ዝግጁነት የትርፍ ጊዜ ፕሮግራሞች የሚሞሉት ቅጽ አርብ ኦክቶበር 7፣ MCPS የልዩ ፕሮግራሞች ድረገፅ ላይ ይገኛል።ለሁለቱም ፕሮግራሞች ፍላጎታቸውን የሚያሳውቁበት ቀነ-ገደብ አርብ ኖቬምበር 4 ነው።
የበለጠ ለማወቅ ወላጆች እና ተማሪዎች "open houses" እንዲገኙ ይበረታታሉ። የስብሰባ ቀኖችን እና ሰዓቶችን ለማወቅ MCPS የልዩ ፕሮግራሞች ድረገጽ ይጎብኙ።

  1. በአደገኛ የበይነመረብ ተግዳሮቶች ላይ ብልህ ይሁኑ

ብዙ ወጣቶች በበይነ መረብ ወይም በማህበራዊ ሚዲያ በሚሰራጩት “ተግዳሮቶች” ላይ ይሳተፋሉ ወይም ይመለከታሉ። እነዚህ ምንም ጉዳት የሌላቸው፣ ሞኝ ወይም አዝናኝ ተብለው ሊወሰዱ ቢችሉም፣ አንዳንዶቹ ወደ ከፍተኛ ጉዳት ሊያደርሱ የሚችሉ እንቅስቃሴዎችን ያካትታሉ።Common Sense Media እናየአሜሪካ የሕፃናት ሕክምና አካዳሚ/American Academy of Pediatrics እነዚህ ተግዳሮቶች ልጆችን ለምን እንደሚማርኩ እና አስተማማኝ ውሳኔዎችን ሲያደርጉ እንዴት ሊረዷቸው እንደሚችሉ ጠቃሚ ምክር ይሰጣሉ።

  1. ወቅታዊ ማስታወቂያ፡ የአትሌቲክስ አሰልጣኝ ቦታዎችን ስለመሙላት የወጣ ማስታወቂያ

በሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) እና በስቴቱ በሚገኙ የትምህርት ቤቶች ዲስትሪክቶች ላይ ተጽእኖ የሚያሳድር የአትሌቲክስ አሰልጣኞች እጥረት መኖሩ እንደቀጠለ ነው። የሙሉ ጊዜ የአትሌቲክስ አሠልጣኝ የሌላቸው ትምህርት ቤቶች በትርፍ ሰዓት በአካል ተገኝተው የሚሸፍኑ፣ እንዲሁም ሌሎች ግብዓቶችን እና ድጋፎችን እንደ telehealth፣ የአሰልጣኝ ምክር፣ ጉዳት የደረሰባቸውን አያያዝ እና በስልጠና ክፍል ቢሮ የሚገኙበት ሰዓቶችን ይሰጣሉ። ብቃት ያላቸው እጩዎችን ለመጠቆም የሚፈልጉ የማህበረሰብ አባላት ዶር. ጄፍሪ ሱሊቫን፣ ስርአት አቀፍ የአትሌቲክስ ዳይሬክተር፣ ወይም ወይዘሮ አንጄላ ማኪንቶሽ-ዴቪስ፣ የፕሮኩረመንት ዳይሬክተር ማነጋገር ይችላሉ።

  1. የትምህርት ቦርድ በማህበረሰብ ተሳትፎ ፖሊሲ ላይ የአስተያየት መስጫ ጊዜን አራዝሟል

የሞንትጎመሪ ካውንቲ የትምህርት ቦርድ ከቦርድ ውሳኔዎች ጋር በተገናኘ የተሳትፎ መመሪያዎችን እና ልምዶችን ለማዘመን የቦርድ ፖሊሲ ABA፣ የማህበረሰብ ተሳትፎ አስተያየት መስጫ ጊዜውን አራዝሟል። መመሪያው ከማርች 30, 2022 ጀምሮ ለአስተያየት ቀርቧል። የህዝብ አስተያየት መስጫ ጊዜው እስከ አርብ፣ ኖቨምበር 4 ድረስ ክፍት ይሆናል።

  1. ስለ መጪ ጊዜያት ጠቃሚ መረጃ፦
    1. የትምህርት ቦርድ ስለ ፀረ-ዘረኝነት የኦዲት ሪፖርት ይቀበላል

ማክሰኞ፣ ኦክቶበር 11 እኩለቀን ላይ የትምህርት ቦርድን መደበኛ ስብሰባ ይመልከቱ። ስርጭቱ፦ Comcast 34, (1071 HD), Verizon 36, RCN 88, MCPS ድረገጽ፣ እና  MCPS YouTube ገጾች ላይ ይተላለፋል።
ስለ ፀረ ዘረኝነት ኦዲት ይወቁ

የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ
Email us: ASKMCPS@mcpsmd.org

Montgomery County Public Schools