አምስት መታወቅ ያለባቸው ነገሮች

MCPS Things to Know

ሐሙስ፣ ፌብ. 16

 

  1. ስለ Fantanyl እና ህይወት አድን ናርካን ማሰልጠኛ የሚቀጥለው የቤተሰብ ፎረም ፌብሩዋሪ 25 ይካሄዳል።

Montgomery Goes Purple ጋር በመተባበር የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) በሚያዘጋጀው ስለ fentanyl ጎጂነት የውይይት ዝግጅት ላይ ቅዳሜ፥ ፌብሩዋሪ 25 ቤተሰቦች እንዲገኙ ተጋዘዋል። የመድረክ ውይይት አቅራቢዎቹ በህገወጥ መንገድ የተሰራውን የፈንታኒል/fentanyl አደጋ እና ስርጭት፣የመከላከያ መሳሪያዎች እና የተማሪዎች የመከላከል ዘዴዎችን እና አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ለህክምና ግብአት የሚውሉ ጠቃሚ መረጃዎችን ያካፍላሉ። ዝግጅቱ በኖርዝዉድ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አዳራሽ/Northwood High School auditorium 919 University Blvd West በ Silver Spring ከጠዋቱ 9፡30–11፡30 a.m. ይካሄዳል። ለተማሪዎች እና ለወላጆች/ለተንከባካቢዎች እና ለተማሪዎች ልዩ ልዩ የውይይት ክፍለጊዜዎች የሚኖሩ ሲሆን፣ የሪሶርስ ትርኢት፣ የኮቪድ-19 ክትባቶች እና መዝናኛዎች ይኖራሉ። የመድረክ ውይይት እና የቡድን ክፍለ ጊዜዎች በእንግሊዝኛ እና በስፓኒሽኛ ቋንቋዎች ይካሄዳሉ።
ይመዝገቡ/RSVP
ስለ ፈንታንይል ጠቃሚ ሪሶርሶች/Fentanyl Resources

  1.  
  2. ለህዝባዊ ትምህርት የላቀ አስተዋጽኦ ያበረከቱትን ለሽልማት ጥቆማ ለማቅረብ ክፍት ተደርጓል።

 

የሞንትጎመሪ ካውንቲ የትምህርት ቦርድ ለ 26ኛው አመታዊ የላቀ ህዝባዊ ትምህርት አገልግሎት ሽልማቶች እጩዎችን ይፈልጋል። በሞንትጎመሪ ካውንቲ ህዝባዊ ትምህርት ላይ አርአያነት ያለው አስተዋጾ ላደረጉ ግለሰቦች፣ ቡድኖች እና ድርጅቶች እውቅና ለመስጠት እና አድናቆት ለማሳየት ሽልማቶቹ በቦርዱ የተደገፉ ናቸው። ስልማት ስለሚሰጥባቸው ምድቦች እና አንድን ሰው እንዴት እንደሚጠቁሙ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት የቦርዱን የላቀ አገልግሎት ሽልማቶች  በይነመረብ/ድረገጽ ይጎብኙ። የተሞሉ የእጩነት ጥቆማ ቅጾች ሐሙስ፣ ማርች 16 ቀን እስከ 5 p.m መድረስ አለባቸው።

  1. የትምህርት ቦርድ በሁለት ፖሊሲዎች ላይ አስተያየት ይፈልጋል

የሞንትጎመሪ ካውንቲ የትምህርት ቦርድ በሁለት ፖሊሲዎች ላይ አስተያየቶችን ይፈልጋል—Policy ABC፣ የወላጅ እና የቤተሰብ ተሳትፎ እና ፖሊሲ BBB፣ ሥነምግባር።
በፖሊሲ/Policy ABC፣ በተማሪዎቻቸው ትምህርት ቤቶች ላይ በሚደረጉ ውሳኔዎች ላይ የወላጅ/አሳዳጊ ተሳትፎ ሂደቶችን ለማሻሻል በታቀዱ ማሻሻያዎች ላይ ቦርዱ አስተያየቶችን ይፈልጋል። ፖሊሲው ከፌብሩዋሪ 9, 2023 ጀምሮ አስተያየት እንዲሰጥበት ይፋ ተደርጓል። የሕዝብ አስተያየት መስጫ ጊዜ እስከ ሐሙስ፣ ኤፕሪል 20 ድረስ ይዘልቃል። ረቂቅ ማሻሻያዎች ላይ የቀረበ ሀሳብ—

  1. ከተሻሻለው ብሔራዊ የቤተሰብ-ትምህርት ቤት አጋርነት ደረጃዎች እና ከሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) የፀረ-ዘረኝነት ኦዲት የመጨረሻ ሪፖርት ግኝቶች ጋር ለማጣጣም የተደረጉ ክለሳዎች ናቸው።
  2. ወላጅ/አሳዳጊ ተማሪዎቻቸውን እና የተማሪዎቻቸውን ትምህርት ቤቶች በሚመለከቱ ውሳኔዎች ላይ እንዲሳተፉ ሁሉን አቀፍ፣ ባህላዊ ምላሽ ሰጪ እና ፀረ-ዘረኝነት የአፈጻፀም ሂደቶችን ለማቋቋም ፖሊሲ ABC፣ የቤተሰብና-የትምህርት ቤት አጋርነት የተሰኘ የስም ለውጥ ተደርጓል።

የቋንቋ ትርጉሞች እንደተዘጁ ወዲያውኑ ይለጠፋሉ።
"Policy ABC" ረቂቅ ፖሊሲ ያንብቡ
ስለ Policy ABC አስተያየትዎን ያቅርቡ
በቅርብ ጊዜ በሜሪላንድ የተደረጉ የፖሊሲ ለውጦች ጋር ለማሳለጥ ቦርዱ የቴክኒክ ማሻሻያዎችን አቅርቧልፖሊሲ/Policy BBB፣ ሥነምግባር የስነምግባር ህግ እና የስቴት የስነ-ምግባር ኮሚሽን ሞዴል ፖሊሲ በተጨማሪም፣ ቦርዱ ስጦታዎችን በሚመለከት፦ የአስተማሪ ስጦታዎች እና የማግባባትና ተፅእኖ የመፍጠር/lobbying እንቅስቃሴን በተመለከተ ማብራሪያ በሚሰጡየቦርድ የስነ-ምግባር ፓነል አማካይነት በተጠቆሙ ተጨማሪ ማሻሻያዎች ላይ አስተያየቶችን ይፈልጋል። ረቂቅ ፖሊሲው ከፌብሩዋሪ 8፣ 2023 ጀምሮ አስተያየት እንዲሰጥበት ይፋ ተደርጓል። የሕዝብ አስተያየት መስጫ ጊዜ እስከ ማርች 4፣ 2023 ድረስ ይቀጥላል።
ፖሊሲ/Policy BBB ላይ አስተያየት ያቅርቡ
በፖሊሲዎች ላይ የህዝብ አስተያየት መስጫ ድረገጽ

  1. የጥቁሮች ታሪክ የሚዘከርበት ወር የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ታሪኮች፡ ማርጋሬት ሲሞን/Margaret Simons

 

በዚህ የጥቁሮች ታሪክ የሚዘከርበት ወር የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ታሪኮችን እናጋራለን። በዚህ ሳምንት፣ የቀድሞ ተማሪ ማርጋሬት ሲሞን/Margaret Simons ስለ ትምህርት ቤት በዘር መለያየት/መነጠል እና የውህደት ዘመን ያካፈለችውን ልምዷን MCPS ያቀርባል። ወደ ጌትስበርግ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ከመዋሃዱ በፊት ሲሞንስ/Simons በካርቨር ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት (Carver High School) ገብታ ተምራለች። ታሪኳን እዚህ ይመልከቱ.

  1. ለእኛ ታላላቅ ተማሪዎች እና ሰራተኞች ትኩረት መስጠት

 

ቅርጫት ኳስ በማይጫወቱበት ጊዜ ወይም በጨዋታዎች ላይ ትርኢት በማያሳዩበት ጊዜ፣ የቶማስ ኤስ. ዎቶን ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የቅርጫት ኳስ ቡድን ተማሪዎች እና የፖም ቡድኑ በፎልስሜድ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ጊዜያቸውን በፈቃደኝነት አገልግሎት ላይ ይሳተፋሉ። Wootton Cares የንባብ እና የማማከር ፕሮግራም እንዴት ለውጥ እያመጡ እንዳሉ ይመልከቱ

  1. ከ100 በላይ ከ6ኛ እስከ11ኛ ክፍል ያሉ ተማሪዎች በት/ቤት የምግብ ዝርዝሮች የጣዕም ሙከራ በማድረግ ላይ ተሳትፈዋል። MCPS የምግብ ጣእም ቅምሻ በሚደረግበት ወቅት፣ ተማሪዎች እና ሰራተኞች የፈጠራ ሀሳቦችን በማመንጨት አዳዲስ ጣዕሞችን ፈጥረዋል። የእነርሱ አስተያየት ለቀጣዩ የትምህርት ዘመን በምግብ ዝርዝር አዘገጃጀት ውስጥ ይካተታል።


Email us: ASKMCPS@mcpsmd.org

Montgomery County Public Schools