አምስት መታወቅ ያለባቸው ነገሮች

MCPS Things to Know

ሀሙስ፣ ማርች 2

1. የቅድመ መዋለ ህፃናት/ሄድ ስታርት ምዝገባ አሁን ተጀምሯል።

ለ 2023-2024 የትምህርት ዓመት የቅድመ መዋዕለ ሕፃናት እና ሄድ ስታርት ምዝገባ አሁን ክፍት ነው። ልጆች በሴፕቴምበር 1, 2023 ወይም ከዚያ በፊት 4 አመት እድሜ የሚሞሉ መሆን አለባቸው፣ እንዲሁም ቤተሰቦች ለማመልከት በገቢ አቅም ረገድ ብቁ መሆን አለባቸው። ቤተሰቦች ልጆቻቸውን በኦንላይን ወይም በአካል ማስመዝገብ ይችላሉ። በአካል ማስመዝገብ ለሚፈልጉ ቤተሰቦች፣የማስመዝገቢያ ቦታዎች እስከ ማርች 31 ድረስ በሳምንቱ የሥራ ቀናት እና የሳምንት መጨረሻ ቀን ክፍት ናቸው። ለአሁኑ 2022-2023 የትምህርት ዓመትም ለማስመዝገብ እስካሁን ክፍት ነው።

ስለ ብቁነት መመሪያዎች፣ አስፈላጊ ሰነዶች እና በኦንላይን እንዴት ማስመዝገብ እንደሚቻል የበለጠ መረጃ ለማግኘት ከፈለጉ 240-740-4530 ይደውሉ ወይም MCPS ድረገጽ ይጎብኙ።

መቼ እና የት እንደሚመዘገቡ፣ 2023-2024


 

2. ለሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች ነፃ SAT መሰናዶ ይሰጣል።

MCPS ተማሪዎችን እንደፍላጎታቸው ግላዊ በማድረግ ከፍተኛ ጥራት ያላቸውን ቨርቹዋል የማጠናከሪያ ክፍለ ጊዜዎችን ለማቅረብ ከ FEV Tutor ጋር በመተባበር ስለሚሠራ ደስተኛ ነው። የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች ከአሁን ጀምሮ እስከ ሜይ ወር ድረስ ለነጻ የስድስት ሳምንት ኮርስ መመዝገብ ይችላሉ። የምዝገባው ጊዜ አርብ ማርች 10 ይዘጋል። ጥያቄ ካለዎት FEV Tutor mcps@fevtutor.com ወይም 855-763-2607 ማግኘት ይችላሉ።
ክፍለ-ጊዜዎቹ የሚኖሩበት ጊዜ፦

  • ከሰኞ - አርብ ፣7 a.m እስከ 10 p.m
  • ቅዳሜ 8 a.m. እስከ 4 p.m.
  • እሑድ 11 a.m. እስከ 10 p.m

3. ሠመር ራይዝ 2023 የተማሪዎች ምዝገባ ማርች 7 ያበቃል

ተማሪዎች ዛሬውኑ Summer RISE 2023 አካል ለመሆን እንዲመዘገቡ ይበረታታሉ። Summer RISE ለመጀመሪያ አመት እና ለመጨረሻ አመት ተማሪዎች ተግባራዊ፣ በሙያ ላይ የሚያተኩሩ የትምህርት ልምዶችን ይሰጣል፤ ይኼውም አሰሪዎች ዝንባሌ ያላቸውን በመለየት በስልጠና እንዲያዳብሩ ይረዳል። ፕሮግራሙ ከጁን 26 እስከ ጁላይ 28 ድረስ ለአምስት ሳምንታት ይካሄዳል። የተማሪዎች ምዝገባ እዚህ ይገኛል። የሞንትጎመሪ ካውንቲ ቢዝነስ ድርጅቶች፣ የመንግስት ኤጀንሲዎች እና የበጎ አድራጎት ድርጅቶች የፕሮግራሙ አስተናጋጅ ሆነው እንዲሳተፉ ምዝገባው ክፍት ነው። ተቀባዮች የሚመመዘገቡበት/Host registration ቀን የሚዘጋው አርብ፣ አፕሪል 14 ነው።


4. የአቅርቦት አገልግሎት አስተባባሪ የአመቱ ምርጥ የድጋፍ ሰጪ አገልግሎት ሰራተኛ በመሆን አሸንፏል

ኪማኒ ግሬይ/Kimani Gray  በ SEIU Local 500 የሚሰጠው አመታዊ ሽልማት የዚህ አመት የድጋፍ ሰጪ አገልግሎት ሰራተኛ በመሆን ተመርጧል። ግሬይ/Gray ለንብረት አስተዳደር እና አቅርቦት ክፍል የአቅርቦት አገልግሎት አስተባባሪ ሲሆን፣የሚሠራው ሥራ ሁልጊዜ ቀላል አይደለም። ምንም እንኳን የሥራው ጠባይ ሁልጊዜ ወደ ብዙ አቅጣጫዎች ቢጎትተውም፣ ሁልጊዜም የተረጋጋ እና ትኩረት አድርጎ ሥራውን ያከናውናል። ባልደረቦቹ የትምህርት ቤቶች እና የቢሮዎች ሥራ ሳይደናቀፍ እንዲከናወን በማድረግ ረገድ የሚያደርገውን ጥረት እያዩ “behind-the-scenes glue” ይሉታል።

ለምን እንደተመረጠ በዚህ ሳምንት የሰራተኞች ማስታወቂያ ሠሌዳ ላይ የበለጠ ያንብቡ

5. ለምርጥ ተማሪዎች እና ሰራተኞች ትኩረት መስጠት

  • ባለፈው ወር፣ Montgomery County Regional Student Government እና የሞንትጎመሪ ካውንቲ ጁኒየር ካውንስል፣ የካውንቲ አቀፍ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች መማክርት ማህበራት፣ 51 የተማሪ መሪዎች የሞንጎመሪ ካውንቲን ከሚወክሉ ህግ አውጪዎች ጋር ለመገናኘት ወደ አናፖሊስ ተጉዘዋል። ተማሪዎቹ ስለ ክፍያ ሂሳቦች የተከራከሩ ሲሆን እነዚያ የክፍያ ሂሳቦች በእነሱ እና በእኩዮቻቸው ላይ እንዴት ተጽእኖ እንደሚኖራቸው አስረድተዋል።
  • ካርል ሄምብክ/Karl Heimbach፣ በኮ/ል ዛዶክ ማግሩደር/Zadok Magruder ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት፣ የቀድሞ የአትሌቲክስ ዳይሬክተር በዚህ ወር በኦርላንዶ፣ ፍሎሪዳ/Orlando, Fl., ብሔራዊ የኢንተርስኮላስቲክ አትሌቲክስ አስተዳዳሪዎች ማህበርየ2023 ታዋቂ ዝነኞች በሚገቡበት ይሳተፋል።
  • የኩዊንስ ኦርቻርድ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የሴቶች እግር ኳስ አሰልጣኝ Peg Keiller/ፔግ ኬለር "Pigskin Club of Washington, Inc" አማካይነት 2022 ከሁሉም ሜትሮፖሊታን ሴት ልጆች ቡድን የዓመቱ ምርጥ አሰልጣኝ በመሆን ተመርጧል/ተመርጣለች።

ተጨማሪ መልካም ዜናዎችን ያንብቡ



Email us: ASKMCPS@mcpsmd.org

Montgomery County Public Schools