አምስት መታወቅ ያለባቸው ጉዳዮች

MCPS Things to Know

ሀሙስ፣ ማርች 23

  1. ለሚቀጥለው የትምህርት ዓመት የመዋዕለ ሕፃናት ምዝገባ ማርች 27 ይከፈታል፥ (ለፎተግራፍ የቪዲዮ ሊንክ/አገናኙን ያስገቡ)/

2023-2024 የትምህርት ዓመት ልጃቸውን ለመዋዕለ ሕፃናት ማስመዝገብ ለሚፈልጉ ወላጆች ማርች 27 ይከፈታል። በሴፕቴምበር 1፣ 2023 ልጆቹ 5 ዓመት ዕድሜ መሆን አለባቸው። ስለ ብቁነት፣ማመልከቻ ስለመሙላት መመሪያዎች፣ ለምዝገባ አስፈላጊ ሰነዶችን ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ከፈለጉ 240-740-4006 ይደውሉ ወይም የመዋዕለ ሕፃናት ምዝገባ ድረ ገጽ ይጎብኙ። ስለ ኦንላይን ምዝገባ ሂደት የበለጠ ይወቁ


story

 

  1. ስለ Fentanyl ቀጣዩ የቤተሰብ ውይይት መድረክ/ፎረም ቅዳሜ ማርች 25 ይካሄዳል።

Montgomery Goes Purple ከሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ጋር በመተባበር Fantanyl በልጆች ላይ ስለሚያስከትለው ጉዳት ሶስተኛውን የቤተሰብ ውይይት መድረክ/ፎረም ማርች 25 ከጠዋቱ 9 a.m.–noon እስከ እኩለ ቀን ድረስ በፓይንት ብራንች ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት (Paint Branch High School) ያስተናግዳል። ይህ የቤተሰብ ውይይት መድረክ የሚያተኩረው በደርዘን የሚቆጠሩ ጥልቅ ግንዝቤ የሚገኝባቸው ክፍለ ጊዜዎች፣ እንዲሁም ስለ ናርካን አጠቃቀም ስልጠና/Narcan training፣ የመርጃ ሰንጠረዦች እና የአካል ብቃት እድሎች ያሉበት ነው። የውይይት መድረኩ ለወጣቶች እና ለአዋቂዎች በየግል እና በጋራ በእንግሊዝኛ እና በስፓኒሽኛ ቋንቋዎች ክፍለ ጊዜዎች ይኖሩታል። የውይይት ርዕሶች የሚከተሉትን ያካትታሉ፦

  • ከልጅዎ ጋር ውይይት መጀመር
  • ከወላጅ ጋር ውይይት መጀመር
  • የአእምሮ ጤና እንክብካቤ
  • ሪሶርሶችን መፈለግ እና ማግኘት
  • ከጓደኞች ጋር ጤናማ ድንበር መጠበቅ

አድራሻ፦ Paint Branch is located at 14121 Old Columbia Pike in Burtonsville.
ይመዝገቡ/RSVP

 


  1. አካታች ጽሑፎችን አጠቃቀም በሚመለከት የተሻሻለ መልእክት

የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ሁሉም የመማሪያ ክፍሎች ለተማሪዎች ሁሉን አቀፍ እና ደህንነቱ የተጠበቀ ቦታ እንዲሆን ይጠብቃል፣ ይኼውም LGBTQ+ ተብለው የሚለዩትን ወይም LGBTQ+ ማህበረሰብ ውስጥ የቤተሰብ አባላት ያሏቸውን ጨምሮ ማለት ነው። በስርአተ ትምህርቱ ወይም በማስተማሪያ ቁሳቁሶች ውስጥ እንደዚህ ያሉ የግል ባህሪያትን ሰፋ አድርጎ ማቅረብ አካታች እንዲሆን የተፈለገውን ውጤት ያበረታታል። ስለዚህ፣ ልክ እንደ ሁሉም የስርዓተ ትምህርት ግብዓቶች፣ መምህራን እነዚህን አካታች ትምህርቶች እና ጽሑፎች ከሁሉም ተማሪዎች ጋር እንዲጠቀሙበት ይጠበቃል።
እንደ መደበኛው ልምድ፣ መምህራን/ትምህርት ቤቶች የትምህርት እቅድ ሲያወጡ በሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ዋና እሴቶች እና የቦርድ ፖሊሲ ላይ በተገለጸው መሰረት አካታች ሁኔታና የትምህርት አካባቢን ማስተዋወቅ እንዲቀጥሉ የተለያዩ መገልገያዎችን እንዲጠቀሙ ይበረታታሉ። በተለይ በሜሪላንድ ህግ ከተፈቀደው “የቤተሰብ ህይወት እና ሰብአዊ  ጾታዊ  ግንኙነት ትምህርት ክፍል” ካልሆነ በስተቀር ተማሪዎች እና ቤተሰቦች በማናቸውም የማስተማሪያ ቁሳቁሶች ከመሳተፍ መርጠው መውጣት አይችሉም። ስለዚህ፣ ወደፊት አካታች መጽሃፍት እንደሚነበቡ ለቤተሰቦች ለማሳወቅ አስተማሪዎች ወደቤት ደብዳቤ አይልኩም።


story

 

  1. ስለ SSL ሰአት ማስረጃ መቅረብ ያለበት የመጨረሻው ቀን ማርች 30 ነው።

የሜሪቶሪየስ አገልግሎት ሰርተፍኬት "Certificate of Meritorious Service" ለማግኘት የሚፈልጉ ተማሪዎች (240 ወይም ከዚያ በላይ SSL ሰዓቶችን ያስመዘገቡ ሲንየሮች) ወይም የሱፐርኢንቴንደንት SSL ሽልማት ያገኙ(ይህም በመካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት 75 ሰአት መመረቂያ መስፈርትን ላሟሉ ተማሪዎች አንድ ጊዜ የሚሰጥ) ሁሉንም SSL forms ለት/ቤታቸው SSL አስተባባሪ እስከ ማርች 30 ድረስ ማቅረብ አለባቸው።

የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ተማሪዎች ከሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ለመመረቅ ቢያንስ 75 የተማሪ አገልግሎት ትምህርት SSL ሰዓቶችን ማግኘት አለባቸው፣ ይህንን ለማሟላት የስፕሪንግ እረፍት ተማሪዎች SSL እድሎች ላይ የሚሳተፉበት አመቺ ጊዜ ነው! ሁሉም ሌሎች SSL ቅጾች/ፎርሞች በተከታታይ መቅረብ አለባቸው፣ ነገር ግን ከጁን 2 የመጨረሻ ቀን በኋላ መሆን የለበትም።


story

 

  1. የእኛን ምርጥ ተማሪዎች እና ሰራተኞቻችንን ትኩረት የሚሻ

ለካርሰን ስኮላርስ የተሰየሙ ተማሪዎች

ለኮሌጅ ስኮላርሺፕ $1,000 በማግኘት ሦስት የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ተማሪዎች በካርሰን ስኮላርስ ተሰይመዋል። ካርሰን ስኮላርስ ከ 4ኛ እስከ 11ኛ ክፍል ያሉ ተማሪዎች በአካዳሚክ የላቀ ደረጃ ላይ የሚገኙ፣ ጊዜያቸውን እና ችሎታቸውን ለሌሎች የሚለግሱ፣ እና የላቀ የአካዳሚክ ስኬት እና ሰብአዊ ባህሪያትን የተላበሱ ናቸው። ለመጀመሪያ ጊዜ የስኮላርሺፕ ተቀባዮች የሆኑት የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ተማሪዎች፡-

  1. ታይያን ቼን፣ ኖርዝዌስት ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት/Taian Chen, Northwest High School
  2. ክሌር ኪርነር፣ ኦዴሳ ሻነን መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት/Claire Kirner, Odessa Shannon Middle School
  3. አሊሰን Xu፣ ዋልተር ጆንሰን ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት/Allison Xu, Walter Johnson High School

በተጨማሪ ስድስት የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ተማሪዎች 3.75 አማካይ ውጤት ነጥብ በማስጠበቅ ለካርሰን ስኮላርስ ያላቸውን አቋም አረጋግጠዋል። እዚህ ይበልጥ ያንብቡ።

story

12ኛው አመታዊ የማይኖሪቲ ምሁራን ሪትሪት ላይ በመቶዎች የሚቆጠሩ ተማሪዎች ተሳትፈዋል

የማይኖሪቲ ምሁራን ፕሮግራም (MSP)፣ በተማሪዎች የሚመራ ተነሳሽነት ያለው፣ 12ኛውን አመታዊ ሪትሪት ፕሮግራም በኖርዝዌስት ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ማርች 18 አካሄዷል። MSP ያሉትን እድሎች ክፍተት ለመቋቋም ከ 17 ዓመታት በፊት በተማሪ-ተኮር ተነሳሽነት የተጀመረ ነው። በተማሪዎች አመራር እና እንቅስቃሴ ለውጥን ለማምጣት እንደ ሞተር ሆኖ አገልግሏል።



Email us: ASKMCPS@mcpsmd.org

Montgomery County Public Schools