አምስት መታወቅ ያለባቸው ጉዳዮች

MCPS Things to Know

ሀሙስ፣ ማርች 30

story
  1. የአመቱ አጋማሽ የትምህርት ማዕቀፍ ማስረጃ በተማሪዎች ትምህርት የመቅሰም አፈጻጸም ላይ የተገኘውን ውጤት እና መሻሻል የሚያስፈልጋቸውን ዘርፎች ያሳያል

ማርች 28 በተደረገው የትምህርት ቦርድ ስብሰባ፣ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) መሪዎች የተማሪዎችን፣ የትምህርት ቤቶችን እና የዲስትሪክቱን የትምህርት ስኬት በአጠቃላይ ለመወሰን በርካታ እርምጃዎችን በመጠቀም የክፍል ውጤት የብቃት ደረጃ ላይ ያተኮረ ትምህርት የመቅሰም ማስረጃ (EOL) የአመቱን አጋማሽ ማስረጃ አቅርበዋል።

በዚህ ረገድ ከመዋእለ ህጻናት (K)፣ 3ኛ፣ 6ኛ እና 9ኛ ክፍል ቢያንስ ግማሽ ያህሉ ተማሪዎች በሂሳብ EOL አግኝተዋል፣ በዚህ አመት ከመዋዕለ ሕፃናት EOL የወሰዱ ከፍተኛው በመቶኛ (70.8%) ውጤት አሳይተዋል፥ እና የስድስተኛ ክፍል ተማሪዎች ዝቅተኛው ውጤት በመቶኛ (48.9%) ነው።

እዚህ ይበልጥ ያንብቡ.


story
  1. የስፕሪንግ እረፍት እና የኮቪድ-19 ምርመራ

እንደቀደምት የእረፍት ጊዜያት፣ ሰራተኞች እና ተማሪዎች ከስፕሪንግ እረፍት በኋላ ሲመለሱ የኮቪድ ምርመራ የማድረግ ግዴታ አይኖርም። ሰራተኞች እና ተማሪዎች ንቁ ሆነው የበሽታውን ምልክቶች እና የግልተጋላጭነት ስጋትን፣ እና እንዲጠነቀቁ  እና ፖዚቲቭ ከሆኑ ወደ ትምህርት ቤት ከመመለሳቸው በፊት የምርመራ ውጤታቸውን ሪፖርት እንዲያደርጉ እንጠይቃለን። የምርመራ መሣሪያዎች የአገልግሎት ጊዜ ተራዝሟል፣ እባክዎ iHealth ወይምInteliSwab የቤት መመርመሪያ መሣሪያዎች አዲሱ የአገልግሎት ጊዜ የሚያበቃበትን ቀን ያረጋግጡ። ስለ ኮቪድ-19 ምርመራ የትምህርት ቤት አሠራር ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ የኮቪድ መረጃ ቋት/ዳሽቦርድ MCPS COVID-19 School Dashboardን ይመልከቱ።


story
  1. በኤፕሪል ወር ለሚካሄዱ ዝግጅቶች ቀኖቹን ያስታውሱ

ዓመታዊ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ኮሌጅ ትርኢት
ከ 300 በላይ ኮሌጆች እና ዩኒቨርሲቲዎች ተወካዮች Montgomery County National Association for College Admission Counseling (NACAC) ብሄራዊ የኮሌጅ ትርኢት ላይ ይገኛሉ። ማክሰኞ፣ ኤፕሪል 18 እና እሮብ፣ ኤፕሪል 19 ቦታው፦ Maryland Soccerplex18031 Central Park Circle in Boyds።

እዚህ ይበልጥ ያንብቡ
ለመሣተፍ ይመዝገቡ

ስለ አየር ንብረት የሚካሄድ የወጣቶች ጉባኤ
የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ ስለ አየር ንብረት ጥበቃ 2ኛውን አመታዊ የወጣቶች ስብሰባ በቲልደን መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት (Tilden Middle School) ቅዳሜ፣ ኤፕሪል 22 ያዘጋጃል። ይህ በተማሪዎች የሚመራው ዝግጅት MCPS ተማሪዎችን ስለ አየር ንብረት ለውጥ ያስተምራቸዋል፥ እንዲሁም የአየር ንብረት መተግበር ያለባቸው ፕሮጀክቶችን ወደ ማህበረሰባቸው የሚያደርሱበትን መሳሪያ ያስታጥቃቸዋል።

ይህንን በይነመረብ ይመልከቱ፦ https://www.montgomeryschoolsmd.org/YouthClimateSummit/.
ለመሣተፍ ይመዝገቡ።

ቲልደን መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የሚገኝበት አድራሻ፦ Tilden Middle School is located at 6300 Tilden Lane in Rockville።
ለወላጆችና ለማህበረሰብ ስለ ልዩ ትምህርት ሪሶርስ/መገልገያዎች አውደርዕይ
የመጀመሪያው የልዩ ትምህርት የወላጅ ማህበረሰብ ሪሶርስ አውደርዕይቅዳሜ፣ ኤፕሪል 29 በጌትስበርግ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት (Gaithersburg High School) ይካሄዳል። የመገልገያ/ሪሶርስ አውደ ርዕዩ ከጠዋቱ 9፡00 –noon እስከ እኩለ ቀን ድረስ ይካሄዳል፣ ንግግር የሚያደርግ ተጋባዥ እንግዳ፣ ለማህበረሰብ ጠቃሚ ግብዓቶች እና አቅራቢዎች፣ እዲሁም አዝናኝ የልጆች እንቅስቃሴዎች፣ moon bounce፣ የእጅ ጥበብ እና ፊት የመቀባት ትርኢቶችን ያካትታል።
እዚህ ይበልጥ ያንብቡ.
የጌትስበርግ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አድራሻ፦ Gaithersburg High School is located at 101 Education Blvd in Gaithersburg.


story
  1.  "Summer RISE Host" ተቀብሎ ለማስተናገድ ዛሬውኑ ይመዝገቡ!

የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) በሁሉም የሙያ ዘርፎች በተለይም በኪነጥበብ እና በመዝናኛ፣ በሥነ ሕንፃ፣ በባዮሳይንስ፣ በቢዝነስ አስተዳደር፣ በሳይበር ሰኩሪቲ/ደህንነት፣ በምህንድስና፣ በጤና አጠባበቅ፣ በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ፣ በሕግ እና በእንስሳት ሕክምና አገልግሎቶች “Summer RISE 2023” ፕሮግራም ተቀብለው የሚያስተናግዱትን ይፈልጋል። Summer RISE ተማሪዎችን ስለ የስራ እድሎች እንዲማሩ ለመርዳት በ MCPS የተጀመረ ፕሮግራም ነው። ጁን 26 እና ጁላይ 28 መካከል በአካል፣ ቨርቹዋል ወይም በሁለቱም የሥራ ቦታ ልምድ ለማካፈል ከፈለጉ ዛሬውኑ ይመዝገቡ። ምዝገባው አርብ ኤፕሪል 14 ይዘጋል።ለበለጠ መረጃ፣ www.MCPS-SummerRISE.org ይጎብኙ።

  1. የዚህ ሳምንት ጉልህ ክንዋኔዎች


MCPS፡ ቢዝነስ የአፍታ ቅኝት ውድድር

ወጣት የሥራ ፈጣሪዎች አመታዊ "MCPS Business Pitch Challenge" ላይ የፈጠራ ሀሳባቸውን በዳኞች ፊት አቅርበዋል። ከስድስት ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የተውጣጡ ተማሪዎች በሻርክ ታንክ "Shark Tank-like" መሰል ውድድር ላይ ተሳትፈዋል። ከኖርዝዉዉድ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ስለ ፋይናንስ መተግበሪያ ባቀረቡት የፈጠራ ሃሳባቸው በአንደኛነት አሸንፈዋል።

story
በስቴት የተማሪዎች ምክር ቤት ኮንቬንሽን ላይ የተማሪ መሪዎች ተመርጠው እውቅና አግኝተዋል

በኦሽን ሲቲ ከተማ በተካሄደው አመታዊ የሜሪላንድ ተማሪዎች ምክር ቤት (MASC) አመታዊ ስብሰባ "Maryland Association of Student Councils (MASC)" ላይ አርባ ስምንት የተማሪ መሪዎች ተሳትፈዋል። ሁለት የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ተማሪዎች ኦፊሰሮች ሆነው ተመርጠዋል፥ እንዲሁም የዊተን 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች የተማሪ አመራር ማህበር በፌብሩዋሪ የህግ አውጭ ስብሰባ/February MASC በማዘጋጀቱ እውቅና አግኝቷል።



Email us: ASKMCPS@mcpsmd.org

Montgomery County Public Schools