የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ኢጁኬሽናል ፋውንዴሽን 194 ተማሪዎች ባሳዩት አካደሚያዊ የልህቀት ደረጃ 2023 " Ruth and Norman Rales-Patricia Baier O’Neill Scholarship" የሩት እና የኖርማን ራልስ-ፓትሪሺያ ቤየር ኦኔል ስኮላርሺፕ ማግኘታቸውን አስታውቋል። እነዚህ እጅግ የላቁ ስኮላርሺፖች 25 ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ውስጥ ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ ሲንየሮች የተሰጡ ናቸው። ኮሌጅ በሚገቡበት ወቅት የሚደርስባቸውን የገንዘብ ጫና ለማቃለል ስኮላርሽፕ የተሰጣቸው እያንዳንዳቸው $10,000 ያገኛሉ።
ማክሰኞ፣ ኤፕሪል 18 እና ረቡዕ፣ ኤፕሪል 19 Montgomery County National Association for College Admission Counseling (NACAC) ከ300 በላይ የኮሌጆች እና ዩኒቨርሲቲዎች ተወካዮች ብሄራዊ የኮሌጅ ትርኢት/National College Fair ላይ ይገኛሉ።አውደርእዩ የሚካሄደው Maryland Soccerplex, 18031 Central Park Circle in Boyds. ሲሆን አውደ ርዕዩ በሁለቱም ቀናት 10 a.m. to 1 p.m. ይካሄዳል። ከትምህርት ቤታቸው ጋር ለሚካፈሉ 11ኛ ክፍል ለሚማሩ ተማሪዎች ክፍት ነው። አውደ ርዕዩ ኤፕሪል 18 ለሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች እና ለቤተሰቦቻቸው 6:30–8 p.m. ክፍት ነው።
ለመሣተፍ ይመዝገቡ
MCPS 2ኛውን ዓመታዊ የወጣቶች የአየር ንብረት ጥበቃ ጉባኤ ቅዳሜ፥ ኤፕሪል 22 ከቀኑ 8፡30 a.m. እስከ 3፡30 p.m. በቲልደን መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት/Tilden Middle School. ያስተናግዳል። ይህ በተማሪዎች የሚመራ ዝግጅት የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ተማሪዎችን ስለ አየር ንብረት ለውጥ ለማስተማር እና የአየር ንብረት ጥበቃ ፕሮጀክቶችን ወደ ማህበረሰባቸው የሚያሰርጹበትን እውቀት ለማስታጠቅ የተዘጋጀ ነው። ተማሪዎች ከአካባቢ የአየር ንብረት ጥበቃ ባለሙያዎች ጋር ይነጋገራሉ፣ ከተማሪ መሪዎች ጋር ትብብር ያደርጋሉ፣ የአካባቢ መረጃን ይወስዳሉ እና የአካባቢ አየር ንብረት ጥበቃን በተመለከተ በማቀንቀን ያድጋሉ። የሚሳተፉ ተማሪዎች የተማሪ አገልግሎት ትምህርት (SSL) ሰዓት ያገኛሉ።
ቲልደን መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የሚገኝበት አድራሻ፦ Tilden Middle School is located at 6300 Tilden Lane in Rockville።
ቤዝ ኤፍ. ቶማስ/Beth F. Thomas በሃሊ ዌልስ መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት (Hallie Wells Middle School) ረዳት ርእሰመምህርት፣ በትምህርት አስተዳደር እና ቁጥጥር 2023 የዶክተር ኤድዋርድ ሸርሊ "Dr. Edward Shirley Award" የላቀ ሽልማት ተሸላሚ ናት።
በሞንትጎመሪ ካውንቲ የአስተዳዳሪዎች እና ርእሰ መምህራን ማህበር (MCAAP) የሚሰጠው ይህ ስመጥር ሽልማት ዓላማ መር አመራር፣ ትምህርታዊ ወይም ስርዓት አቀፍ አመራር፣ የሰው ሃይል ልማት፣ የሪሶርስ ማኔጅመንት፣ ግለሰባዊ ክህሎት፣ ሙያዊ ተሳትፎ፣ የማህበረሰብ እና ባለድርሻ አካላት ተሳትፎ እና ስኬት ለሚያሳይ አስተዳዳሪ ወይም ተቆጣጣሪ ይሰጣል።
የሪቻርድ ሞንትጎመሪ ትምህርት ቤት "Richard Montgomery School Mock Trial Teams" ቡድኖች የስቴት ሻምፒዮና አሸናፊ ሆነዋል።
2023 የሜሪላንድ ስቴት ሞክ ትራያል ሻምፒዮና ላሸነፈው የሪቻርድ ሞንትጎመሪ ት/ቤት Richard Montgomery School Mock Trial team ቡድን እንኳን ደስ አላችሁ! ቡድኑ 11-0 ሲዝን ምንም ሽንፈት ሳይኖርበት በአስደናቂ ፉክክር አጠናቋል። የስቴት ሞክ ትራያል ውድድር/state mock trial competition በትምህርት አመቱ ከ 140 በላይ ትምህርት ቤቶች እርስ በርሳቸው የሚፎካከሩበት ውድድር ነው።
Email us: ASKMCPS@mcpsmd.org