
የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የፎል የስፖርት ወቅት ሊጀመር ሁለት ሳምንታት ቀርተውናል! ኦገስት 9፣ 2023 ለመጀመሪያው የሙከራ እና የልምምድ ቀን ለመዘጋጀት አንዳንድ ቁልፍ ነገሮችን እነሆ፡
የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የፎል ወቅት የስፖርት ምዝገባ
የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የፎል ወቅት የስፖርት ምዝገባ "ParentVUE" በመጠቀም ይካሄዳል። የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ሙከራዎች እና ልምምዶች ኦገስት 9, 2023 ይጀመራሉ። የሙከራ/የልምምድ ሎጅስቲክስን በተመለከተ ዝርዝሮቹ በአካባቢ ትምህርት ቤት እና በቡድን (ኖች) በኩል ይገኛሉ። ሥርዓትአቀፍ ሪሶርሶች/ግብዓቶች MCPS አትሌቲክስ ድረ-ገጽ ላይ ይገኛሉ።
የመካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የፎል ወቅት ስፖርት ምዝገባ
የመካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የፎል ወቅት ስፖርቶች ምዝገባ ኦገስት 14, 2023 እኩለ ቀን ላይ "ParentVUE" ምዝገባ ይካሄዳል። የመካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ሙከራዎችን እና ልምምዶችን ሴፕቴምበር 12, 2023 ይጀምራሉ። የሙከራ/የልምምድ ሎጂስቲክስን በተመለከተ ዝርዝሮቹ በአካባቢ ትምህርት ቤቶች እና በቡድን (ኖች) በኩል ይገኛሉ። ሥርዓትአቀፍ ሪሶርሶች/ግብዓቶች MCPS አትሌቲክስ ድረ-ገጽ ላይ ይገኛሉ።

2. አሁንም በጣም አልዘገየም፡ የሠመር ንባብ አቅምዎን ይክፈቱ
የሠመር ወቅት ከመዝናኛ ባለፈ በልጆች አእምሮ ላይ የማንበብ ፍቅርን ለማዳበር ጥሩ አጋጣሚ ጊዜ ነው። የንባብ ሳይንስእንደሚያስረዳው፣ ማንበብ ለልጅዎ የአእምሮ እድገት እና መዳበር ወሳኝ ነው። አንባቢያን የቃላት አጠቃቀማቸውን፣ የመረዳት ችሎታቸውን እና የአስተሳሰብ ችሎታቸውን የማዳበር ክህሎት መጻሕፍትን በማንበብ ይጎናፀፋሉ። በልጅነት እምሮ የመማር ችሎታን፣ ጠንካራ የማንበብ ችሎታዎችን ለማበልፀግ፣ ሁሉንም የህጻናት አካዳሚያዊ ጉዞዎች ለማጎልበት እና በጥልቀት የማሰብ እና የመተንተን ችሎታዎችን ለማስተማር ይህ ትክክለኛ ጊዜ ይሆናል።
መደበኛ የሠመር እንቅስቃሴዎችን በሚያቅዱበት ጊዜ፣ ንባብን በእለት ተዕለት እንቅስቃሴ ውስጥ ማካተት እንደሚያስፈልግ ያስቡበት። የሚማርኩ ተረኮችም ይሁኑ ትምህርታዊ ቁሳቁሶች፣ እያንዳንዱ ገጽ ሲገለጥ ለሁሉም ልጆች ብሩህ የወደፊት ጉዞ መንገዳቸውን ያሳያል።
መገልገያዎች

3. MCPS እየቀጠረ ነው!
ማክሰኞ ኦገስት 8 ከቀኑ 10 a.m.-1 p.m. ወደ MCPS የስራ ቅጥር አውደርእይ ቦታ ይምጡ። አድራሻው ይሄ ነው፦ Montgomery College’s Rockville Campus Student Services Atrium, located at 51 Mannakee Street in Rockville. ፕሮፌሽናል ሰራተኞችን፣ አስተማሪዎችን፣ አስተዳዳሪዎችን፣ የድጋፍ ሰጪ ሰራተኞችን፣ ፓራኢዱኬተሮችን፣ ተተኪ መምህራንን፣ የምግብ አገልግሎት ሠራተኞች እና ሌሎችንም እንቀጥራለን። ሌሎች መጪ የምልመላ ኩነቶችን ይመልከቱ፡
የትራንስፖርት ዲፓርትመንት የስራ አውደርእይ አርብ፣ ጁላይ 28 ከጠዋቱ 10a.m.-2p.m በዚህ አድራሻ ላይ ይካሄዳል፦ 16651 Crabbs Branch Way in Rockville.
ለልዩ ትምህርት/special education የስራ መደቦች ጁላይ 31 ወይም ኦገስት 7 ከቀኑ 6-6:30 p.m. ቨርቹዋል የመረጃ ልውውጥ ክፍለ ጊዜ ስለሚካሄድ ይቀላቀሉን።
ይመዝገቡ/RSVP

4. ቀኑን መዝግበው ይጠብቁ፡ አመታዊ ወደ ትምህርት ቤት የመመለሻ ትርኢት
MCPS ዓመታዊውን ወደ ትምህርት ቤት የመመለስ ትርዒት ቅዳሜ፣ ኦገስት 26 ከ10፡00 a.m. እስከ 1 p.m. በዊተን ዌስትፊልድ የገበያ ማዕከል/Westfield Wheaton mall ያስተናግዳል። ዝግጅቱ ቤተሰቦች ስለ ትምህርት ቤቶች ስርዓትአቀፍ መረጃ እና የካውንቲ ፕሮግራሞችን እና አገልግሎቶችን እንዲያውቁ ጥሩ አጋጣሚ ነው። ለቤተሰብ ተስማሚ የሆኑ እንቅስቃሴዎች፣ መዝናኛዎች፣ የበሽታ መከላከል ክትባት ክሊኒክ እና ሌሎችም ይኖራሉ። አድራሻ፦ Westfield Wheaton is located at 11160 Veirs Mill Road in Wheaton. በሠመር ወቅት በሙሉ ወቅታዊ ጉዳዮችን ለማግኘት ድረ-ገጻችንን ጋር ይከታተሉ።
5. የተማሪዎች ትኩረት
ተማሪዎች ELO SAIL የሠመር ፕሮግራም በኩል ተጨማሪ ድጋፍ ያገኛሉ
2023 የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) የተራዘመ የመማር ማስተማር እድሎች የሠመር አድቬንቸርስ ትምህርት (ELO SAIL) ፕሮግራም በዚህ ሳምንት ያበቃል። ይህ 17-ቀን የሠመር ነጻ ፕሮግራም Title I አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችን በሠመር የተጓደለ ትምህርት ኪሳራን ለመቀነስ እና ተማሪዎችን ለቀጣዩ የትምህርት አመት በማዘጋጀት አስደሳች የሠመር ተግባራትን ይሰጣል። በዚህ ፕሮግራም ተማሪዎች በተግባራዊ፣ አስደሳች እና የሚያበለጽግ ሊተርሲ፣ ሒሳብ እና ሳይንስ ወይም STEM ትምህርቶች፣ እንዲሁም በማህበራዊና ስሜታዊ ትምህርት ላይ ይሰማራሉ።

ተማሪዎች smART ካምፕ ላይ ይሳተፋሉ
smART የሠመር ፕሮግራም ከ1ኛ እስከ 5ኛ ክፍል ላሉ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) አንደኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች በነፃ የሚሰጥ የቪዡዋል አርት የሠመር ካምፕ ነው። ካምፑ የሚካሄደው MCPS Summer RISE ፕሮግራም ጋር በመተባበር ነው። የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ታዳጊ ጁኒየር እና ሲንየር ተማሪዎች ከአንጋፋ መምህራን ጋር የሥዕል ትምህርት መስክን እንደ አዋጭ የኮሌጅ እና የሥራ መስኮችን ለመዳሰስ እድል ይሰጣቸዋል።
ኢሜል ይላኩልን: ASKMCPS@mcpsmd.org