ባነር

ከዶክተር ቴለር ጋር ይተዋወቁ

ጁን 18, 2024

የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ ቀጣዩ ሱፐርኢንተንደንት ዶ/ር ቶማስ ቴለር፣ በማህበረሰባችን ውስጥ ያሉ ሁሉም ልጆች በፍትሃዊነት፣ በቀጥተኛ ተሳታፊነት፣ እና በመደጋገፍ ላይ የተመሠረተ አስደናቂ ትምህርት ማግኘት ይገባቸዋል ብለው ያምናሉ። በሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ውስጥ እምቅ አቅም መኖሩን በመመልከት ስራ ላይ ለመሠማራት በጣም ደስተኛ ናቸው።

ስለ ዶ/ር ቴለር ለማወቅ ይህንን አጭር ቪዲዮ ይመልከቱ።


ዶ/ር ቴለር የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ሱፐርኢንተንደንት በመሆን በጁላይ ወር ሥራ ይጀምራሉ። በማህበረሰብ ስብሰባዎች፣መደበኛ እና መደበኛ ባልሆኑ ግንኙነቶች እና ሰላምታዎች፣ እና የተለያዩ እድሎችን በመጠቀም ከተማሪዎች፣ ከቤተሰቦች፣ ከሰራተኞች እና ከማህበረሰቡ ጋር በመገናኘት ዲስትሪክቱን እና ማህበረሰቡን በማዳመጥ ይተዋወቃሉ። ከዶክተር ቴለር ጋር ለመወያየት እና ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ይከታተሉ።

Montgomery County Public Schools



ኢሜል ይላኩልን፦ ASKMCPS@mcpsmd.org