የትምህርት ቦርድ ወቅታዊ መረጃ

ሜይ 10, 2024

የሞንትጎመሪ ካውንቲ የትምህርት ቦርድ ለሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ አመራር ይሰጣል እና ክትትል ያደርጋል። የዚህ ሳምንት የትምህርት ቦርድ ዘገባዎች፦ አገልግሎትን ስለማክበር፣ እየተካሄደ ስላለው የሱፐር ኢንተንደንት ፍለጋ፣ እና ሜይ 9 የተደረገ የሥራ ስብሰባ ውይይትን ያካትታል።

2024 ዓ.ም የላቀ አገልግሎት ተሸላሚዎች እንኳን ደስ አላችሁ!

ታላቅ የህዝባዊ ትምህርት አገልግሎት ላበረከቱት ማክሰኞ፣ ሜይ 7 ቀን ቦርዱ የ 2024 ዓ.ም ሽልማት ሰጥቷል። በዝግጅቱ ላይ በሞንትጎመሪ ካውንቲ ህዝባዊ ትምህርት አርአያነት ያለው አስተዋጾ ያደረጉ አስራ ሁለት ግለሰቦችን፣ ቡድኖችን፣ እና ድርጅቶችን አክብሮት ተሰጥቷል።  

ስለ ሱፐር ኢንተንደንት ፍለጋ

የትምህርት ቦርድ ለሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) የትምህርት ቤቶች ሱፐርኢንተንደንትነት ለመወዳደር እየቀረቡ ያሉትን ማመልከቻዎች እየገመገመ ነው። 

የእጩዎችን ግላዊ መብት ለመጠበቅ ቦርዱ እስካሁን ያመለከቱትን ወይም ለእጩነት እየታሰቡ ስላሉት ግለሰቦች ለጊዜው ዝርዝር መረጃ መስጠት አልቻለም። በሂደት ወቅታዊ መረጃዎችን ለማህበረሰቡ ስለምናጋራ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ሱፐርኢንተንደንት ፍለጋ ድረ-ገጽ በመጎብኘት ህብረተሰቡ እንዲያውቅ እና እንዲሳተፍ እናበረታታለን።

ሜይ 9 የተካሄደ የሥራ ስብሰባ

ሜይ 9 በተካሄደ የቢዝነስ ስብሰባ ቦርዱ ስለ ተማሪዎች በትምህርት ላይ የመገኘትን አስፈላጊነት እና ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ የመጣውን ከት/ቤት የመቅረትን ስጋት ለመቅረፍ የተለያዩ ስልቶች ላይ ውይይት አድርጓል። MCPS ችግሮችን የሚከላከሉ፣ ችግሮችን የሚፈቱ፣ እና ሥር የሰደደ ከትምህርት ቤት የመቅረትን ችግር በሚፈታበት ጊዜ የመጥፎ ገጠመኝ ስሜት ቁስሎችን የሚመለከቱ ስልቶች ላይ ትኩረት ይሰጣል። ዲስትሪክቱ ቤተሰቦችን እና ተማሪዎችን ሁለቱንም ወገን በማሳተፍ ላይ ልዩ ትኩረት ያደርጋል።

ሜይ 9 ቀን የተካሄደው የቢዝነስ ስብሰባ በታሪካዊው የካርቨር የትምህርት አገልግሎት ማእከል ውስጥ ሲካሄድ ከነበረው የመጨረሻው የቢዝነስ ስብሰባ ነው። ቦርዱ የቢዝነስ ስብሰባዎቹን ሜይ 23 ጀምሮ "15 West Gude Drive, Rockville" በአዲሱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ላይ ያካሄዳል። 

የመሳተፍ እድሎች

ህብረተሰቡ ከቦርዱ ጋር እንዲሳተፍና እንዲተባበር እናበረታታለን። በእኛ ድረ ገጽ ላይ መሳተፍ ስለሚችሉባቸው መንገዶች ያንብቡ።

ቀጣይ ስብሰባዎች

  • ሐሙስ፥ ሜይ 16 - የፖሊሲ ማኔጅመንት ኮሚቴ
  • ሐሙስ፥ ሜይ 21 - የኮሙዩኒኬሽን እና የባለድርሻ አካላት ተሳትፎ ኮሚቴ
  • ሐሙስ፥ ሜይ 23 - የትምህርት ቦርድ መደበኛ ስብሰባ

አጀንዳዎችን እና የቀጥታ ስርጭቶችን ለማየት የኛን ድረ-ገጽ ይጎብኙ።

ግንኙነትዎን ይቀጥሉ

በፌስቡክ እና X  ላይ ይከታተሉን

በዚህ አድራሻ ኢሜል ያድርጉልን፦ boe@mcpsmd.org


ኢሜል ያድርጉልን፦ ASKMCPS@mcpsmd.org