ስለ ት/ቤት አውቶቡስ ያለበትን አካባቢ ለማወቅ ክትትል ለሚያደርጉ ቤተሰቦች ወቅታዊ መረጃ

ውድ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ቤተሰቦች እና ተንከባካቢዎች

የት/ቤት ትራንስፖርት ስርዓታችንን ለማሻሻል ባለን አላማ መሠረት፣ MCPS በዚህ አመት መጀመሪያ ላይ የት/ቤት አውቶብስ መከታተያ ሶፍትዌርን አቅም ለመገምገም የሙከራ ፕሮግራም መጀመሩ ይታወቃል።

የሙከራ ፕሮግራሙን በጥንቃቄ ክትትል ከተደረገበትና፣ በትንታኔ ከተገመገመ በኋላ ፍተሻ የተደረገበት የሞባይል መተግበሪያ የተማሪዎችን ግላዊ መረጃ ሊያስተላልፍ የሚችል ተጋላጭነት እንዳለው ተረጋግጧል። ይህንን ስላወቅን፣ ምንም እንኳን የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ተማሪ ግላዊ መረጃ በማንኛውም ጊዜ ባይጋለጥም፣ ለሙከራ ፍተሻ የተደረገበት መተግበርያ የተጠበቀውን ደረጃ እንደማያሟላ ማረጋገጥ ተችሏል። በዚህ ምክንያት ይህንን ልዩ የሙከራ መርሃ ግብር ለማቁረጥ ወስነናል።

ቤተሰቦች በፈለጉበት ጊዜ የት/ቤት አውቶቡስ የት ቦታ እንደሚገኝ በቅጽበት መከታተል እንዲችሉ ለማድረግ አማራጮችን መፈለግ እንደምንቀጥል እንድታውቁ እንፈልጋለን። ይህ ለተማሪዎቻችን አስተማማኝ እና ቀልጣፋ የትራንስፖርት አገልግሎት ለመስጠት ካለን ቁርጠኝነት ጋር የሚጣጣሙ አማራጭ መፍትሄዎችን እና ቴክኖሎጂዎችን ማሰስን፣ የተማሪዎቻችንን የመረጃ ደህንነት መጠበቅና ማረጋገጥን ያካትታል። በዚህ ጉዳይ ላይ የደረስንበትን ደረጃ በየጊዜው እናሳውቃችኋለን።

በአጭር ጊዜ ውስጥ የመከታተያ መሳሪያው በሁሉም አውቶቡሶች ላይ የሚተገበር ሲሆን ፣ አውቶቡሶች የደረሱበትን ቦታዎች፣ የሚጓዙበትን ፍጥነት፣ ምን ያህል ማይል/ርቀት እንደተጓዙ በቀላሉ ለማወቅ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስን (MCPS) የትራንስፖርት መምሪያ ሰራተኞችን የመከታተል አቅም የሚያሳድግ ከመሆኑም በላይ በዲስትሪክቱ ትልቅ የትራንስፖርት መሠረተ ልማት ተግዳሮቶችን ምላሽ ለመስጠት ያግዛቸዋል።

ወላጆችን፣ የትምህርት ቤት አስተዳዳሪዎችን፣ እና የትራንስፖርት ሰራተኞቻችንን ጭምር በሙከራ መርሃ ግብር ለተሳተፉት ሁሉ፣ ልባዊ ምስጋናዬን መግለጽ እፈልጋለሁ። በዚህ ሂደት ውስጥ የእናንተ አስተያየት እና ድጋፍ በጣም ጠቃሚ ነበር። ውጤቱ እንደጠበቅነው ባይሆንም፣ ወደፊት የምንሄድበትን አቅጣጫ ለማወቅ እንዲህ አይነት ተነሳሽነት ትምህርት/ልምድ ሰጥቶናል።

በዚህ ጉዳይ ስላለዎት ግንዛቤ እና ትብብር ዳግም እናመሰግናለን።

ከሰላምታ ጋር

Brian Hull
MCPS Chief Operating Officer


ኢሜል ያድርጉልን፦ ASKMCPS@mcpsmd.org