ማሳሰቢያ፦ መጪው የኮርስ ፍጻሜ ፈተና የመጨረሻ ውጤት ላይ ተጽእኖ ይኖረዋል

ውድ የዘጠነኛ ክፍል ተማሪ ቤተሰብ

እባክዎን ይህን በጣም ጠቃሚ መረጃ ያንብቡ። በሚቀጥለው ወር፣ተማሪዎች ከመጨረሻው ሴሚስተር B ምዘና 20% የሚቆጠር ደረጃ የጠበቀ ምዘና ሊወስዱ ይችላሉ።

ለማስታወስ ያህል፣ በአሁኑ ጊዜ በዘጠነኛ ክፍል (2027 ክፍል) የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ብሄራዊ፣ የስቴት እና የአካባቢ መንግስት (NSL) እና የባዮሎጂ ኮርሶችን እየወሰዱ ያሉ ተማሪዎች ከት/ቤት ውጤታቸው ጋር የሚካተት የሜሪላንድ አጠቃላይ ግምገማ ፕሮግራም (MCAP) ምዘናዎችን ይወስዳሉ። እነዚህ ምዘናዎች በዚህ አመት ተማሪዎች በኮርስ ስራቸው ሲማሩት ከነበረው የትምህርት ይዘት ጋር የሚጣጣሙ ናቸው።

የተማሪ የመጨረሻ ሴሚስተር B ውጤት የሶስተኛ ሩብ ክፍለጊዜ (40%)፣ የአራተኛው ሩብ ክፍለጊዜ (40%) እና MCAP ምዘና (20%) ስሌት ይሆናል። 

በዚህ የትምህርት ዓመት መጀመሪያ ላይ እንደተገለፀው

  • ይህ ከሜሪላንድ ስቴት የትምህርት ዲፓርትመንት የተሰጠአዲስ መስፈርት ነው።

  • ምዘናዎቹ ሜይ 1 እና ሜይ 15, 2024 መካከል ባለው ጊዜ ውስጥ በተማሪዎ ትምህርት ቤት ይካሄዳሉ። የልጅዎ ትምህርት ቤት ምዘና የሚሰጥባቸውን ቀናት ይገልፅልዎታል።

  • የኮርስ ማብቂያ ፈተናዎች (EOC) የስነህይወት ሳይንስ የሜሪላንድ የተቀናጀ የሳይንስ ፈተና (LS MISA) ከሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ባዮሎጂ ኮርስ ጋር የተቀናጀ እና የስነ መንግስት ምዘናው ከሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ብሄራዊ፣ የስቴት እና የአካባቢ መንግስት ትምህርት ጋር የተቀናጀ ነው።

የኮርስ መጨረሻ (EOC) ፈተና ማለፍ ለመመረቅ የግዴታ ባይሆንም፣ ተማሪዎች የኮርስ ክሬዲቶችን ለማግኘት ኮርሱን ማለፍ አለባቸው።

ልጅዎ ለእነዚህ ግምገማዎች በደንብ መዘጋጀቱ(ቷ)ን ለማረጋገጥ፣ የሚከተሉትን ማሳሰቢያዎች እንዲያጠናክሩ እንጠይቅዎታለን።

በትምህርት ቤት መገኘት፣ትምህርት መከታተል እና ጥረት ማድረግ፦ የትምህርት ምዘና በሚሰጥባቸው ቀናት ወደ ትምህርት ቤት የመምጣትን አስፈላጊነት እና በፈተና ወቅት የተቻለውን ሁሉ ጥረት ማድረግ እንዳለባቸው አጽንኦት ሰጥተው ይምከሯቸው። ተማሪዎች ምዘናውን እንደገና እንዲወስዱ አይፈቀድላቸውም። ተማሪዎች ምዘናውን ካልወሰዱ እና ያለበቂ ምክንያት ከቀሩ፣ በምዘናው ላይ ዜሮ ያገኛሉ፤ ይህም እስከ መጨረሻው ውጤታቸው ድረስ ይሰላል። ተማሪዎች የመመረቂያ መስፈርት ለማሟላት በምዘናው ላይ መሳተፍ ይኖርባቸዋል።

የኮርስ ቁሳቁሶችን/ማቴሪያሎችን ማጥናት፦ልጆቻችሁ በሴሚስተር A እና ሴሚስተር B ላይ የተሰጣቸውን የትምህርት ማስታወሻዎቻቸውን እና ክፍል ውስት የተማሩባቸውን ቁሳቁሶች በመጠቀም እንዲያጠኑ ያበረታቷቸው። LS MISA እና MCAP ሁለቱንም የስነመንግስት ምዘና የመልመጃ ፈተናዎችን ተጨማሪ የመለማመጃ ፈተናዎችን ለማግኘት እዚህ ጠቅ ያድርጉ።

የልጅዎ የመጨረሻ ሴሚስተር B የፈተና ውጤት በሪፖርት ካርዱ ላይ ይካተታል፤ ጁን 24, 2024 ወደ ቤት ይላካል።

ማናቸውም ጥያቄዎች ካሉዎት ወይም ተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለጉ፣ እባክዎ የልጅዎን መምህር ወይም ትምህርት ቤቱን ያነጋግሩ። ስለ ኮርስ ማጠናቀቂያ ፈተናዎች በተደጋጋሚ የሚቀርቡ ጥያቄዎች እና መልሶች እዚህ ይገኛሉ። ለበለጠ መረጃ እባክዎ ይህን ድረ ገጽ ይቃኙ።

አመሰግናለሁ።


ኢሜል ያድርጉልን፦ ASKMCPS@mcpsmd.org